Monday, August 9, 2010

ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 3

ኦ አበዊነ ንቡራዊነ እድ ስዩማን አለ መትልወ ሐዋርያት፡፡
አንቀጽ ተስማሚውን ያወርዳል፡፡ ናፈቅረክሙ ወነአብየክሙ ሲል ነው፡፡ ተውህበ ጳውሎስ ሙቁህ ብሎ ወአካል አንሂ መቁሃን ባለ ጊዜ ተወህቡ፡፡ አገብአ ለኤልዛቤል ወስተ ምስካባ ዘቀዳሚ ወእለሂ ዘመው ምሳሌሀ ባለ ጊዜ አገብጾሙ፡፡ ትህምክህሙ ቤተ ክርስቲያን አንተ ውስተ ባቢሎን ዘግብጽ ብሎ ወማርቆስ ባለ ጊዜ ይኤምኃ ክሙ እንዳለበት፡፡ ከሃዋርያት ቀጥላችሁ ሃዋርያትን መስላችሁ በአንብሮተ እድ የምትሾሙ አባቶቻችን እናከብራቸዋለን እናገኛቸዋለን፡፡ ከሊቀ ጳጳስ ጀምሮ እስከ ቄስ ያሉት በአንብሮተ እድ ይሾማሉ፡፡ ቅብዓት ያለበት ነው ዲያቆን በአንብሮተ እድ ይሾማል ቅብአት የለውም ከዚያ በታች ያሉትን በቃል ይሾሟቸዋል፡፡
እስመ ነሳእናከሙ አስተብቋዕያነ ለነ ለኀበ እግዚአብሔር፡፡

ወደ እግዚአብሔር ልታማልዱን፡፡ አስተበቁዐነ፤ እግዚአብሔር አግኝተን ተቀብለናችኋልና እናከብራችኋለን እናገናችኋለን ሃተታ፡- ሊቀ ጳጳሱ በሞተ ጊዜ የበቁትን ደጋጎቹን መርጠው ስማቸውን በቅፋፍ ጽፈው ያለፈው ኦ እግዞኦ አዕርፍ ነፍሰ አቡነ እገሌ ለሚመጣው ኦ እግዚኦ አንብር ለነ ዲበ መንበሩ ኖላዌ ሄረ ኢንኩን ከመ መር ኤት ዘአልቦ ኖላዊ ወኢይምስጠነ ተኩላ መሳጢ እያሉ ይፀልዩበታል፡፡ ፀሎታቸውን ሲፈጽሙ አንድ ብላቴ አምጥተው እያነሳህ ስጠን ይሉታል እያነሳ ይሰጣቸዋል ሳያይ መልሰው ይቀላቅሉታል አንዱን 3 ጊዜ መላልሶ ይሰጣቸው እንደሆነ ያሮስ ያሮስ አኪዮስ አኪዮስ ብለው ይሾሙታል ይደልዎ ይደልዎ ማለት ነው አንዱን 1 ጊዜ አንዱን 1 ጊዜ የሰጣቸው እንደሆነ ግን ከጸሎቱ ይጨምሩበታል ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣ እንደሆነ ይሁዳ በወጣ ጊዜ በይሁዳ እግር እኛ ባወቅን ማትያስ እና ባርናባስን መርጠናል አንተ እገግዚኦ ማእምረ ኩሉ ልብ አርኢ 1ደ እምአሉ ዘኃረይከ ዘይነስአ ለመልእክተ ሲመት ዘሐዋርያት፡፡ ኩላሊት ያመላለሰውን ልቡና ያሰበውን መርምረህ የምታውቅ አቤቱ ይህችን ሐዋርያተን ሹመት ገንዘብ የሚያደርጋትን ከነዚህ ከሁለቱ የመረጥከው አንዱን ግለጥልን ብለው፡፡ በአስተ አጸውዎሙ ይላል፡፡ እጻ አጣጣላቸው ወወዕአ ላእለ ማትያስ ይላል እጣ በማትያስ ወጣ መከራ የሚቀበልበት ነውና በዓለ፡፡ አንድም ለማትያስ ዋጋ የሚያገኝበት ነውና ለ አለ ወተኁለቁ ምስለ 0 ወ 1 ሐዋርያት ከ01 ሐዋርያት 02ኛ ሁኖ ተቆጥሯልና እንዲህ አለ፡፡
ወነሳእሙ በመዋእሊነ አስተሳሰብ ቋዕያነ ለነ ለህበ እግዚአብሔር እሎንተ 2 ኤተ ሊቀነ ጳጳሳት፡፡


የእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳ እለ እስክድርስና አትናቴዎስን ወደ እግዚአብሔር ሊያማልዱን ተቀብለናአዋልና አስተበቁዐነ ይላል፡፡ እግዚአብሔር አግኝተን ተቀብለናቸዋልና እናገኛቸዋለን እናከብራቸዋለን ሃተታ፡- ዕለ እስክንድሮስ አርዮስን ተከራክሮ ረትቷልና አትናትዮስም በእሱ ሃዘን በርሱ ፀሎት በዘመኑ አርዮስ ሙቶዋልና፡፡
ብጹእ ጳጳስ አባ እገሌ ዘሀገር እስክንድርያ አባይ እስክንድርያ፡፡ በእስክንድርያ በመዲናይቱ ሀገር የተሸመ አባ እገሌን፡፡
ወዲበ ርእሰ ሃገረ አበዊነ ብጹእ ከጳጳስ በመዲናይቱ በአክሱም የተሸመ ንዑድ ክቡር የሚሆን አባ ሰላማን እንወደዋለን እናከብረዋለን እንዳለፈው ተርክ፡፡
አንድም አሎንተ ክልኤተ ሊቃነ ጳጳሳተ አባ እገበሌ ዘሀገር አባይ እለ እስክንድርያ ወዲበ ርእሰ ሀገረ አበዊነ ብፁእ ጳጳስ አባ ባስሊዎእ፡፡
የእስክንድርያውያን አባ እገሌ የሀገራችን ጳጳስ አባ ባስልዮስን እናከብራቸዋለን እነወዳቸዋለን እንክንድራውያንስ ሊቀጳጳስ ይሁን የሀገራችን እለምን ሊቀጳጳስ አለው ቢሉ እስክንድሪያው ሊቀ ጳጳስ አስጠግተ ስምኦንን ከሌዊ አስጠግቶ ካህናትን ህሉፋነ ፍኖት ከበቱ ፍኖተ እግዚኦሙ እንዳለ አንድም ከሊቀ ጳጳስ ማዕርግ አድርሶ የሚሰደው እለሆነ በመንበሩ አስቀምጦ ጭራውን መቋሚያውን መስቀሉን ሰጥቶ የሚሰደው ሰለሆነ አንድም ስም ሰጥተው ግብር ነስተውታል ወያክብርዎ በስመ ሊቀናት በህቲቱ ዘንበለ ይኩን ሎሩ ስልጣነ ዝንቱ እንዲል በእእክንድር እስክንድርያ ተብላለች፡፡ ታሪክ እስክንድር የሚባል ገናና ንጉስ ነበረ ስነ ባዓል ለማየት መንግስት ለማድረስም ቢሊ ለሌላም ነበር ቢሉ አንድም ያቁመን ለመተጋት እየሩሳሌም ወጣ ከወጣ ዘንድ ሲመለስ ሰም የሚያስጠራ ልጅ የለኝ ምን ሰርቼ ስሜን ላስጠራ አለ ድልድይ ሰርተህ አስጠራ አሉት ይህች እስክድርያ ማይ ጽንፋ ማይ ሃጹራ ይላታል ውሃውን በመዘውር በልሶ የብረት አምድ እያቆመ የብረት ድልድይ እየደለደለ በኖራ እየገለበጠ በብረት እየጠረቀ የብረት ሰረገላ እያሸጋገረ የብረት መረባ ሰርቷል፡፡

ልማደ ሰብእ ልማደ እንስሳ የሚወርድበት እንደ መሽረብ ያለ ሰርቶ አዞ ጉማሬ እየወጣ እንዳያውክ ገባሬ ተአምር አመጽ ኤልሳእን ቀብሮበታል በዚያ ላይ ሶስት ድስት ሙሉ ቀብሮበት ሂዷል፤ ይህ የተደረገ በዘመነ ቡሉይ ነው ሲያያዝ ከዘመነ ሀዲስ ደርሷል ከዘመነ ሀዲስ እስከ ዘመነ ሊቃውንት ደረሰ አትናቴዎስ በእስክንድርያ ተሹሞ ሳለ በዘመኑ ረሀብ ሆነ፤ ወርቅ ተቀብሮ እያለ ነደያን እየተራቡ እመከመ ረከብኩ ሞገሰ መቅድመ አምላክየ እየሀድጎ ለዝንቱ አድራማሌቅ ሙክራበ ሰገል እያለ ሲጸልይ ተምኔቱ ሳይፈጸምለት ሞተ፡፡ ከሱ ቀጥሎ ቴዎፍሎስ ተሸመ እሱም በዘመኑ ረሀብ ሆነ ወለእመ ለከብኩ ሞገሰ በቅድመ አምላክየ እየሀድጎ ለዝንቱ አድራማሌቅ ምኩራበ ወገል እያለ ሲያዝን ይኖር ነበረ ኃላ ግን አልአርታ የምትባል የሮም ንግስት ብዙ ሰራዊት አስከትላ ሄደች ስለምን ቢሉ ለምናኔ ብዙ ሰው አስከትሎስ ምናኔ የለም ብዙ ገዳማተ ግብጽን እጅ ለመንሳት በገዳማተ ግብጽ ካቱ አበው ለመባረክ ከአበው አንዱ እሱ ነውና ወደ እሱ ሄደች አዝኖ አየችው ምነው አዝናሀል አለችው እኔ አላዝን ማን ይዘን ወርቅ ተቀብሮ እያለ ነደያን እየተራቡ አላት አታስኮሰትረውምን አለችው ባይቻለኝ ባንተ ጸሎት በእግዚአብሔር ረድኤት አስኮሰትርልሀለሁ ብላ ብታስኮሰትርለት ቴዳ ቴዳ የሚል ሶስት ድስት ሙሉ ወርቅ ተገኝቷል ቴዳ ማለት ታኦስ ማለት ነው ታኦስ የጌታ ስም የጌታ ለነደያን ይገባል ብሎ አንዱን ለነድያን መጽውቶሎታል አንዱን ቴዳ ማለት ቴዎዶስዮስ ማለት ነው ብሎ ለንጉሱ ሰዶለታል፡፡ ንጉሱም ለበረከት ያህል ከፍሎ አስቀርቶ መልሶ ሰዶለታል፡፡ በዚህ አብያተ ክርስቲያናትም ይነጽት ለነዳያንም ይመጸውተው አልታወቀም፡፡ አንዱን ቴዳ ማለት ቴዎፍሎስ ማለት ነው ይሄ የእኔ ገንዘብ ነው ብሎ በዚህ ሰባት ያህል አብያተ ክርስቲያናት አንጾበታል፡፡ ታቦተ እየሱስ ታቦተ ማርያም ታቦተ ሚካኤል ታቦተ ሩፋኤል በዘባነ አንበሪ የታነጸ በዚያ ጊዜ ነው ታቦተ ኤልሳእ ታቦተ ዮሐንስ መጥምቅ ይህ አንድ ወገን ነው፡፡

ታቦተ ኤልሳቤጥ ታቦተ መርቆሬዎስ ነው ወረቅ ስለተገኘባተ አባይ አላት ይሕስ አባ ሕርያቆስ የሚሻ መንፈሳዊ የስጋው የደሙን ነገር ነው የመንፈሳዊ የስጋው ደሙን ነገር ሲናገር መጥቶ ማሩን አምርሮ ወተቱን አጥቁሮ ወርቅ ተገኘባት ብሎ አባይ አይላትም ብሎ ወትከውን አሃቲ ሀገር ምስዋኦ ለእግዚአብሔር እንዲል በአራቱ ማዕዘን ሐይማኖት ሲጠፋ እሰከ ዕለተ ምፅሐት ወልድ ዋህድ ስትል ትኖራለችና ርእሰ አክሱም ሀገር መላ ኢትዮጵያ፡፡
01 ይ ዲ በእንተ ብፅእት፡፡
ወብጽእት አንቲ እንተ ተአምኒ ከመ ይከውን ቃል ዘነገሩኪ ተብላ በኤላሳቤት ቃል ስለተመሰገነች፡፡
ወፍስሕት፡፡
ተፈስሂ ተፈስሂ ተብላ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ስለተበሰገነች ወስብሀት ለኩሉ፡፡
ክብር በውስተ ነብያ ክቡር በውስተ ሊቃውንት እንዲል በሁሉ ዘንድ ስለተመሰገነች ወቡሩክት፡፡
ቡሩክት እንቲ እምአንስት ተብላ ስለተመሰገነች፡፡
ወቅድስት ወንጽህት እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ማርያም ድንግል ንጽህት ኩሉ ጊዜ ተብላ ስለ ተመሰገነች አምላክን ስለወለደች ስለ እመቤታችን ብለህ አንድም እሷን አማለጅ በማድረግ እጣን ቋጥረው ግብር ሰፍረው መባዕ ይዘው ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚሄዱት አስባቸው ይበል፤ እግዝእትነ እለ ከግብርናተ ዲያቢሎስ ነጻ አውጥቶ የሚገዛን ከእሷ በነሳው ስጋ ስለሆነ ነው፡፡
02 ወበእንተ ቅዱሳን ክቡራን፡፡ ጽኑዓን ክቡራን፡፡
መንፈሳውያን፡፡ ረቂቃን ስለሚሆኑ፡፡ ሊቃነ መላእክት፡፡
መዐርጋቸውን መናገር ነው፡፡ ሰማያውያን፡፡
ቦታቸውን መናገር ነው፡፡
ወኃያላን፡፡
ኃያላን ስለሚሆኑ ስለዚህ ብለህ አንድም በእነዚህ አማላጅነት፡፡ ሀተታ፡- በተፈጥሮ ኃይል ይሰጣቸዋልና አንድም በቅዳሴ በተራድኦ ምክንያት ይጨመርላቸዋልና፡፡
ሰባኪ፡፡
ነስሁ እስመ ቀረበት ምነግስተ ሰማያት እያለ፡፡
ወጸያሄ ፍኖት ዮሐንስ መጥምቅ፡፡ ጺሁአ ጸፍቶ እግዚአብሔር እያለ ስለሚያስተምር መጥምቀ መለኮት ስለሚሆን ስለዮሐንስ ብለህ አንድም በእሱ አማላጅነት፡፡
ወበእንተ ቅድሳን ስቡሃን ወላእካን ማትዮስ ወማርቆስ ሉቃስ ወዮሐንስ 4ቱ ወንጌላውያን፡፡
ንጹሀን ክቡራን ላእካነ ቃል ስለሚሆኑ ስለ 4ቱ ወንጌላውያን ስለ ማቴዎስ ስለ ማርቆስ ስለ ሉቃስ ስለ ዮሐንስ ብለህ አንድም በዚህ አማላጅነት ማቴዎስና ዮሐንስ ከቦታቸው ይተረጎማሉ፡፡
ማርቆስ ማለት አንበሳ ማለት ነው አንበሳ ለላህም ጌታው ነው ይሰብረዋል፡፡ እሱም ከግብጽ ላምህን አጥፍቷልና አንድም ንህብ ማለት ነው ንብ የማይቀስመው አበባ የለም፤ እሱም አስቀድሞ ከጌታ ኋላ ከኃዋርያት ተምሯልና አንድም ካህን ማለት ነው ወአምጽኡ ማረዜድዮስ እንዲል፡፡
ሉቃስ ማለት መስበር ማለት ነው ብስራት ማለት ነው ብስራት መልአክን ይጽፋልና አንድም ተንሳኢ ማልት ነው ለስብከተ ውንጌል ይጠናልና አንድም አቃቤ ስራይ ማለት ነው፡፡ ዘስጋ ነበረ ኃላ ግን አቃቤ ስራይ ዘነፍ ሁኗልና፡፡
03 በእንተ ቅዱሳን አግብርቲከ ክቡራን ባለሟሎችህ ስለሚሆኑ ሀተታ፡- የባለሟልነት ስማቸው ነው ዳዊት ገብርየ ሙሴ ገብርየ እንዲል፡፡
ጴጥሮስ
ጴጥሮስ ማለት መሰረት መሰረትነቱ የሀይማኖት የልጅነት ነው፡፡ ወያእቆብ ስለያዕቆብ ብለህ ያዕቆብ ማለት አእቃጼ ሰኮና አሃዜ ሰኮና ማለት ነው የቀደመው የዕቆብ ሰኮና ኤሳውን ይዞ እንደተወለደ እሱም ወንጌል ሲያስተምር በዚያው ይሞታልና አእቃጼ ሰኮና ኤሳው እንደሆነ በትምህርቱ የመናፍቃንን ትምህርት ያሰናክላልና፡፡
ወዮሐንስ
ስለ ዮሐንስ ብለህ ዮሐንስ ፍስሐ ወሐሴት ርህራሄ ወሳህል ማለት ነው ፍስሃ ወሀሴት አለ ቅብአ ትፍስህት መንፈስ ቅዱስ ያስጣልና ርህራሄ ወሳህል አለ በጸጋ ዘነሳእክሙ መጸጋ ሀቡህ በእንቱ ዘነሳእክሙ በከንቱ ሀቡ ባለው ጸንቶ ያስተምራልና፡፡
ወእንድርያስ
ስለ አንድርያስ ብለህ አንድርያስ ማለት ተባእለ ለመስቀል በኩረ ሐዋርያተ ማለት ነው ተባእ ለመስቀል አለ እስከ ሀገር በላእተ ሰብእ ሄዶ አስተምሯልና፡፡
ፊሊጶስ
ፊሊጶስ ማለት ምፍቀሬ አኅው ማለት ነው ፊልሳዳፎስ እንዲል አንድም አሃዜ ኪናት ረያጺ አፍራስ ማለት ነው አንድም ስውር ቦታ ማለት ነው ፌላሌምሎሞንም ንዑ ንህድር ብሔር ፊልሞን እንዲል፡፡
በርተለምዮስ
ስለ በርተለምዮስ ብለህ በርተለምዮስ ማለት ተክል የማጠጣት ግብር ያለው ልጅ ማለት ነው፡፡ ኩን ወልደ ኃይል ኩን ወልደ የማን እንዲል፡፡ አንድም ዕለቱን ወይን ተክሎ ለመስዋእት አድርሷልና፡፡
ቶማስ
ስለ ቶማስ ብለህ ቶማስ በለት ፀሀይ ማለት ነው ሁለቱ አስማቲሁ ለፀሀይ 1ዱ ኦርያሬስ ወካልኡ ቶማስስ እንዲል፡፡ ወማቴዎስ
ስለ ማቴዎስ ብለህ ማቶዎስ ማለት ህሩይ እመጸብሀን ማለት ነው ግብር የሚያስገብርበት መርጦታልና፡፡
ወያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
ስለ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ብለህ ወልደ እልፍዮስ ማለት ተለይቷል አንጂ ትርጓሜው እንዳለፈው ነው፡፡
ታድዮስ
ስለ ታድዮስ ብለህ ታድዮስ ማለት ዘርእ ወማእረር ማለት ነው ኦርቲን እንደዘር ወንጌልን እንደማእረር አድርጎ አስተምሯልና አንድም ዕለቱን ሰንዴ ዘርቶ ዕለቱን ለመስቀእት አድርሷልና፡፡
ወስምኦን ወማትያን
ሰለ ስምኦንና ሰለማትያን ብለህ ማትያን ማለት ምትክ ማለት ነው ማትያስ ማለት ፀሐይ ማለት ነው፡፡
0ቱ ወ2ቱ ሐዋርያት፡፡
ስለ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት ብለህ አንድም በእነዚህ አማላጅነት አስባቸው ስማቸውን አስቀድሞ ቁጥራችን ወደኋላ አመጣ
ወያዕቆብ ሐዋርያ እኁሁ ለእግዚእነ ኤጰስ ቆጰስ ዘኢየሩሳሌም፡፡ በኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስነት ስለተሸመ የጌታችን ወንደም ስለሚሆን ስለ ወንጌል ዙሮ ስለእስተማሩ ስለያእቆብ ወንጌልን ዙሮ ስለ አስተማሩ ያዕቆብ ብለህ አንድም በእሱ አማለጅነት ሀተታ መገናኛው ጉንዱ አልኣር ነውአልአዛር ቅስራንና ማትያንን ይወልዳል ቅስራ እያቄም እመቤታቸንን ጌታን ማትያን ያዕቆብ ዮሴፍን ዮሴፍ ያዕቆብን ይወልዳል፡፡ በአንፃር ያለ ነውና እኁሁ አለ፡፡
ለተዘምዶ እነ ያዕቆብ እነ ዮሐንስ ወለደ ዘብድዮስ ይቀርቡታል ብሎ እናቱ በህጻንነቱ ሙታ ከአባቱ ቤት አግኝታው ከጌታ ጋር እያጠባች አሳድጋዋለችና ኃሊብ ድንግልናዊንስ እሩቅ ብእሲ መጥባት አይቻለውም ብሎ እንደ እናት ሁና ኣድጋዋለችና ኤጲስ ቆጰስ ዘእየረሳሌም አለ ያዕቆብ መኮነ እግሩ ከመ እግረ ነጌ ይላል ከገድል ጽናት የተነሳ እግሩ እንደሙቀጫ ተድበልብሎ ነበር እና ለስበከተ ወንጌል አይፋጠንም ብለው በኢየሩሳሌም ሹመውት ሄደዋል፡፡ ከሀዋርያት አንድ አንድ ደዌ የሌለበት አለ ቅዱስ ጴጥሮስንም ወኮነ ድውየ ወድግዱገ ስጋ ይለዋል አጸናበትም አንጂ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ቀጭን ሰጥር ውጋት አዳጊት የምትባል ራስ ፍልጠት ደዌ ነበረበት በእዚያውስ ላይ ሐዋርያ ደመና ጠቅሶ ካሰበው ደርሶ ብዙ አስተምሮ አሳምኖ ብዙ አጥምቆ ይውል የለምን ቢሉ በኢየረሳሌም የነበሩ አይሁድ ምሁራነ ምፃሕፍተ ነቢያት ናቸው ከእርሱ በቀር የሚያውቅባቸው የለም ብለው ሹመውታል ያገሩን ሰርዶ ባገረ በሬ እንዲሉ፡፡ ሐዋርያ አለው ወንጌል ዙሮ አስተምሯልና
ወቅዱስ ወስቡህ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማእት፡፡
ንጹህ ክቡር ሊቀ ዲያቆናት የሰማዕታት ደገኛ አንድም የሰማእታት ፊታውራሪያቸው ስለሚሆን ስለ እስጢፋኖስ ብለህ አንድም በእሱ አማላጅነት እስጢፋኖስ ማለት ወደብ መደብ ለሆቴ ደንጊያ ማኅቶተ ቁድ ማለት ነው ንፋስ የማያስገባ ብርሃን የማይከለክል ፋና ነው ቀዳሜ ሰማዕት አለ ከጌታ ቀጥሎ ከሐዋርያት አስቀድሞ መከራተ የተቀበለ እሱ ነውና 6ቱን ዲያቆናት መርጠው 7ኛ እርሱን መደበኛ አድርገው ሹመውታልና ሊቀ ዲያቆናት አለ፡፡
04 ወኩሎሙ ቅዱሳን ወሰማእት እለ እረፉ በርትእት ሐይማኖት፡፡
ውሎ ውሎ ከቤት ኑሮ ኑሮ ከመሬ እንዲሉ ኃይማኖታችንን አንክድም ብለው ስለሞቱ ሰማእታት ብለህ አንድም በነዚህ አማላጅነት፡፡
ጳውሎስ
ስለ ጳውሎስ ብለህ አንድም በእሱ አማላጅነት ጳውሎስ ማለት ነዋየ ህሩይ ማለት ነው፡፡
ጤሞቲዎስ
ስለ ጤሞትዮስ ብለህ ጤሞትዎስ ማለት ዘአልቦቱ ጥሬት ማለት ነው፡፡
ሲላስ
ስለ ሲላስ ብለህ ሲላስ መለት ፀሐይ መለት ነው፡፡
ወበርናባስ
ስለ በርናባስ ብለህ በርናባስ ማለት ወልደ ፍስሀ ማለት ነው፡፡
ቲቶ
ስለ ቲቶ ብለህ ቲቶ መለት አርቅ ማለት ነው፡፡
ወፍልሞና
ስለ ፍልሞና ብለህ ፍልሞና ማለት ስውር ቦታ ማለት ነው፡፡
ወቀሌምንጦስ
ስለ ቀሌምንጦስ ብለህ ቀሌምንጦስ ማለት ግንብ ማለት ነው፡፡
፸ወ2ቱ አርድዕት
ነሣሣለትና ስለ ሰባሁለቱ አርድዕት ብለህ አንድም በእነዚህ አማላጅነት አስባቸው፡፡
5ቱ ፻ት ቢጽ፡፡
ስለ አምስት መቶ ቢጽ ብለህ አንድም አንዚህ አመላጅነት በማድረግ ሀተታ፡- እሊህ ከ5፻ ብቅ 6፻ ዝቅ እንደሚሉ በዕለ አርብ እንደ አሸን ፈልተው ከእግረ መስቀል የተነሱ ናቸው ቢጽ አላቸው በተፈጥሮ ከእሊህ እስከ እርገት እስከ ጰራቅሊጦስ ያስተማረ አለ ወዲያው እስከ ትንሳኤ ቆይቶ ያረፈ አለ፡፡
3፻0ወ8 ርቱዓነ ሀይማኖት፡፡
ሃማኖታቸው ስለ ቀና ስለ ሶስት መቶ አስራ ስምንቱ ሊቀውንት ብለህ አንድም እነዚህን አማለጅ በማድረግ እጣን ቋጥረው ግብር ሰፍረው መብዓ ይዘው ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱትን አስባቸው አንድም እንዚህ አማላጅ ስለአደረጉ፡፡ አንድም በእነዚህ አማላጅነት አስባቸው፡፡
05 ለእሉኒ ወለኩሎሙ ተዘከሮሙ ለከ እግዚኦ፡፡ ያለፈውን የሚያጣራውን ላንተ ማደሪያ ቤተሰብ ወገን ለሚሆኑ አቤቱ አስባቸው፡፡
ለብጹእ ወለቅዱስ ሊቃነ ጳጳስ አባ እገሌ ንዑድ ክቡር የሚሆን አባ እገሌን፡፡
ወብዑእ ወቅዱስ አባ እገሌን፡፡ ንዑድ ክቡር የሚሆን አባ እገሌን አስባቸው አንድም ለእነዚህ ብለው እጣን ቋጥረው ግብር ሰፍረው መብዐ ይዘው ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚሄዱትን አስባቸው፡፡
06 ከመ ትዕቀቦሙ በሕይወቶሙ በሕይወተ ስጋ ሳሉ ከመከራ ስጋ ትጠብቃቸው ዘንድ አንድም ማሰብ ሌላን ዓለም ጠብቃቸው፡፡
ወታድኅኖሙ፡፡
ታድናቸው ዘንድ፡፡ አንድም ማዳን ሌላን አለ አድናቸው፡፡
ወትሥረይሎሙ አጢአቶሙ፡፡
አጢአታቸው ታስተሰርይላቸው ዘንድ አንድም ማዳን ሌላን አለ ኃጢያታቸው የሚያስተርይላቸው
ወትምሀረነ ኪያነ ሂ በጸሎተ እግዚእሆሙ ለዓለን ዓለም፡፡
ትምሀረነ ካለ ለነሂ ኪያነ ካለ ትምሀር ባለ በቀና ነበረ ነገር ግን ልማደ መጽሀፍ ነው እኛንም በእሳቸው ጸሎት ይቅር ትለን ዘንድ አንድም ማሰብ መጠበቅ ማዳን ኃጢያትን ማስተሰረይ ሌላን አለ በሳቸው ጸሎት ለዘለዓለሙ ይቅር ይበለን፡፡
ይቆየን .........

ውዳሴ ማርያም አንድምታ የሰኞ ክፍል 1

ይኸነን መጽሐፍ ኤፍሬም ሶርያዊ ኤፍሬም ለብሐዊ ተናግሮታል፡፡ ሶርያዊ በሀገሩ ለብሐዊ በተግባ ያስኛል፡፡ ይህም ቅዱስ ኤፍሬም የያዕቆብ ዘንጽቢን ደቀ መዝሙር ነው፡፡ ያዕቆብ ዘንጽቢንም ቁጥሩ ከሰለስቱ ምዕት ነው፣ ለአውግዞተ አውአርዮስ ሲሄድ አስከትሎ ሂዶ ነበር፡፡ አርዮስ አውግዘው ሀይማኖት መልሰው ተመልሰው ካደሩበት ቦታ አምደ ብርሃን ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ለሊቱን በህልሙ ራዕይ ያያል፡፡ ራዕዩም እንደገለጽክልኝ ባለበኔቱንም ግለፅልኝ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ነው፡፡ለቤተ ክርስቲያን አምድ ፅንዕ ነውና በትምህርቱ የሰውን ልቦና ብሩህ ያደርጋልና እንዲህ ባለ አርአያ አየኸው አለው፡፡ ባስልዮስም ቁጥሩ ከሰለስቱ ምእት ነው ደረሶም ተመልሶም እንደ ሆነ በደዌም በዕርግናም ምክንያት ቀርቶ እንደሆነ የቀረበት ምክንያት ከዚህ በኃላ መምህርን ካወጡበት ሳያገቡ ትቶ መሄድ ፈሊጥ አይደለምና መምህን ካወጣበት አግብቶ ሰለሦስተ ነገር ይሄዳል መጀመሪያ እንዲህ ካለ ሰው ጋራ ቢጫወቱ መንፈሳዊ ነገር ይገኛልና ብሎ ሁለተኛ በጆሮ የሰሙትን በዐይን ቢያዩት ይረዳልና ብሎ ሦስተኛ የመንፈስ ቅዱስን ነውን ወይስ ሰይጣን ተጫውቶብኝ ይሆን ብሎ ስለ ሄደ ግን እንዳየው ሆኖ አላገኘውም በወርቅ ወንበር ተቀምጦ በወርቅ አትራኖስ የወርቅ ወንጌል አቀርግቶ ካባ ላንቃ ለብሶ ኪፋር ጠምጥሞ መነነሳንሱን ቢያዩት የሐር መያዣውን በያዩት የወርቅ መነሳንስ ይዞ ሲያስተምር አግኝታል፡፡ ወተሐዘቦ ልቡ ለኤፍሬም ከመ ሥጋዊ ውእቱ እንዲል፡፡
እስመ ሚስጥራትን ይትከሠታ ለትሑታ እስመ ውስተ ምይንት ነፍስ ኢተኀድር ጥበብ አንዲል፡፡ ወይሬእዩ ርእሶሙ ከመ መነፈስ እንተ ህልፈት ይላል ለመንፈስ ቅዱ ሁለት ግብ አለውን ወይስ ሰይጣን ተጫውቶብኝ ይሆን እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ዐራት ነገር አይቶ ይረዳል፡፡ መጀመሪያ ካፋ ነጸብራቅ እሳት እየወጣ ሕዝቡንም ሲዋሃዳቸው ያያል ይህም ትምህርቱ ነው፡፡ ሁለተኛ እርብ መጥታ በራሱ ላይ ስታርፍበት ሦስተኛ ተሐዋስያን ከልብሱ ላይ እያረፋ እንደቆሎ ሲረግፍ ያያል፡፡ ይህን መናፍቃን ፍጡር ፈጣሪ ይመስላ ያቃጥላልን ብለው እንቃወማለን ይላሉ አይፈርስም ለከዊነ እሳት ደርሶ ነበርና ያቃጥላል ዐራተኛ ስሙን ያያውቅ ሀገሩን ያይጠይቅ ኤፍሬም ሶርያዊ ኤፍሬም ለብሐዊ ብላችሁ ጥሩልኝ ከማእዘነ ቤተ ክርስቲያን ባንዱ ቆሞ ይጸልይላችኋል ብሎ አስጠርቶ በአስተርጓሚ ሲጫወቱ ጨዋታው ባይከተትለት አባቴ ጸልይና ያንተ ቋንቋ ለእኔ ይገለጥልኝ፡፡

ጸልዮ የባስልዮስ ቋንቋ ቅርዕ ነው ለኤፍሬም የኤፍሬም ቋንቋ ሱርስት ነው ለባስልዮስ ለገልጾላቸው ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አሰናብተኝ ሊሂድ አለው፡፡ መች ልትሄድ አምጥሃላ ልትኖር ነው እንጂ ብሎ ሕዝባዊ ነው ቢሉ ዲቁና ዲያቆን ነው ቢሉ ቅስና ሽሞ ከሀገረ ስብከቱ ሀገር ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው፡፡ በሰልዮስም ይህን መልበሱ ስለ ክብረ ወንጌል ነው፤ ዛሬ ካህናት አክሊል ደፍተው ኩፋር ጠምጥመው ካባ ላንቃ ለብሰው ስጋውን ደሙን እንዲያከብሩ እንዲለውጡ እርሱስ በውስጥ የሚለብሰው ማቅ ነበር፡፡ ከዚህ በኃላ እም አዝማደ ነገስታት ይላታል ከአዋልደ ነገስታት ወገን የምትሆን አንዲት ሴት ነበረች ኃጢያቷን እየፃፈች የምታኖር፡፡ ስለምን ቢሉ ለመንገር ብታፍር፡፡ አንድም ቢበዛ፡፡ አንድ ቀን መጥታ እንደተጠቀለለ ይዛ አባቴ በዚህ ያለው ይፋቅልሽ በለኝ አለችው፡፡ ይፋቅልሽ አላት ገልጣ ብታይ አንዲት ቀርታ አየች ዘዕጽብ ለነጊር ለገቢርም ይላታል ይህችሳ አለችው ይህስ ለቅዱስ ኤፍሬም ቢቻል እንጂ ለእኔ አይቻለኝም አላት፡፡ አሁን ለእርሱ የማቻለው ሆኖ አደለም ቅዱሳን የራሳቸው ክብር ኪገለጥ የወንድማቸው ክብር ቢገለጥ ይወዳሉና፡፡ ዳግመኛም ስጥመጣ ስትሄድ ድካም ያለባት ነውና ቀኖና ይሁናት ብሎ ነው ሄዳ አባቴ በዚህ ያለው ኃጥያትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችው

ይህስ ለሊቀ ጳጳሱ ለቅዱስ ባሰልዮስ ቢቻለው እንጂ ለእኔ አይቻለኝም አላት አሁን በእርሱ የማይቻለው ሆኖ አይደለም፡፡ ቅዱሳን የራሳቸው ክብር ኪገለጥ የወንደማቸው ክብር ቢገለጥ ይወዳሉና፡፡ ዳግመኛም ስትሔድ ስትመጣ ድካም ያለባት ነውና ቀኖና ይሁናት ብሎ፡፡ ስለሄድሽ ግን እንደቀደመው በህይወተ ስጋ አታገኝውም ሙቶ ሊቀብሩት ይዘውት ሲሄዱ ታገኝያለሽ ሳትጠራጠሪ ከአስክሬኑ ላይ ጣይው ይፋቅልሻል፡፡ ብትሄድ ሙቶ ሊቀብሩት የዘውት ሲሄዱ አገኘች አትጠራጠር ካስከሬኑ ላይ ብትጥለው ተፍቆላታል ይህም የካህናትን ማዕርግ ደግነት ይጠይቃል፡፡ በህይወተ ስጋ ሳሉ ከሞቱም በኃላ አጢያት እንዲያስተሰርዮ ስምኦን ዘአምድ የያዕቆብ ዘንጽቢን ደቀ መዝሙር ነው አብሮት ተምሯል ሊጠይቀው መጣ ሰላም ለኪ ኦ እግዝእትየ ቅድስት ድንግል እያለ ሲያስተምር ሰማሁ፡፡ ኦ እግዝእትየ ከማን አገኘኸው መምህራችን አልነገረን አለው፡፡ ነግሮናል እንጂ አልነገረንም ይመስክር ተባብለው ከመቃብሩ ላይ ቢሄዱ አስሩ ጣቶቹ እንደ ፋና እያበሩ ተነስቶ በህይወትየ እብለኪ ሰላም ለኪ ኦ ቅድስት ድንግል ከመ ስምኦን ዘአምድ፡፡ ወድህረ ሞት የሰ ኩሎሙ አዕፅምትየ ይብሉኪ ወይወድሱኪ ሰላም ለኪ ኦ እግዝእትየ ድንግል ከመ ኤፍሬም ሶርያዊ ብሎ መስክሮለታል፡፡

ይህም የቅዱስ ኤፍሬም ጸጋው ክብሩ ነው፡፡ ከሞተ በኋላ የሚናገረውን አውቆ ለማመስገን ሶርያዊ በሀገሩ ያሰኘው እስከዚህ ነው፡፡ ለብሐዊ በተግባሩ ቢረሌ በርጠብ ብርጭዎ ኩዝ ካቦ እየሰራ የዐመት ልብሱን የዕለት ምግቡን እያስቀረ ይመፀውት ነበር ሲመፀውትም መስላሴ በመላእክት በፃድቃን በሰማዕታት ስም አይመፀውትም በእመቤታችን ስም ይመፀውት ነበር ንቋቸውን አጥቅቷቸውን ነውን ሰለምነው ቢሎ ንቋቸም አጥቅ ቷቸውም አይደለም የእመቤታችን ፍቅር ባያደርሰው ነው፡፡ እመቤታችንን ከመውደዱ የተነሳ የእመቤቴ ምስጋናዋ እንደሰማይ ኮከብ እንደ ባህር አሸዋ በዝቶልኝ እንደልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤው ጠግቤው እያለ ሲመኝ ይኖር ነበር፡፡ የሹትን መግለጽ እግዚአብሔር ልማዱ ነውና፡፡ ገልጾለት ፼ ካ4 ሺህ ድርሰት ደርሷል አኃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ እስኪል ድረስ፡፡ የሚጸልየውም ጸሎት ከሉቃስ ወንጌል ወበሳድስን ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን አውጥቶ ፷4 ፷4 ጊዜ ይጸልይ ነበር፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ዕለቱ ሰኑይ ጊዜው ነግህ ነው፡፡ የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል የብርሃን ይዘረጋል ከዚያ ላይ ሁና ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም ትለዋለች፡፡ እሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል፡፡ ወድሰኒ ትለዋለች እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ ሰማያውያን ወምድራውያን፡፡ ምድራውያን ጻድቃን ሰማእታት ሰማያውያን መላእክት አንቺን ለማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል አላት፡፡ በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ ተናገር አለችው፡፡ በተረቱበት መርታት ልማድ ነውና፡፡ እፎኑ ይከውነኒ ዝንቱ እንዘ እየአምር ብእሴ ብትለው፡፡ መልአኩ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽ ላእለኪ ብሏት ነበርና፡፡ ከዚህ በኋላ በርክኒ ይላታል፡፡ በረከተ ወልድየ ወአብሁ መንፈስ ቅዱስ ይኀድር በላእሌከ ትለዋለች፡፡ ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል፡፡ ሲያመሰግናትም ደቀ መዝሙር ቅኔ ቆጥሮ እንዲቀኝ ድርሰት አስቦ እንዲጽፍ አይደለም፡፡ ብልህ ደቀ መዝሙር ያጠናውን ቀለም ከመምህሩ ፊት ሰተት አድርጎ እንዲያደርስ እንደዚያ ነው፡፡ ስታደርሰውም ከሰባት ከፍላ አስደርዋለች፡፡ ስለምን ቢሉ በሰባቱ ዕለታት መመስገን ፈቃድዋ ቢሆን፡፡ አንድም ሰባቱ ዕለታት ምሳሌዋ ናቸውና በዕለቱ እሁድ ትመሰላለች፡፡ በዕለተ እሁድ አስራወ ፍጥረታት አራቱ በህርያት ተገኝተዋል፡፡ ከሷም ለዘኮነ ምክንያተ ፍጥረት በፍላዌሁ እንዲለው አስራወ ፍጥረት ጌታ ተገኝቷልና፡፡ በዕለተ ሰኑይ ትመሰላለች፡፡ በዕለተ ሰኑይ ከዚህ እስከ ብሩህ ሰማይ መልቶ የነበረውን ውሃ ከሶስት ከፍሎታል፡፡ አንዱን እጅ ከላይ ሰቅሎታል ሐኖስ ነው፡፡ አንዱን እጅ በዙርያው ወስኖታል፡፡ አንዱን እጅ አጽንቶ የብርሀን ማህደር አድርጎታል ጠፈር ነው ጠፈር የእመቤታችን ብርሃን የጌታ ምሳሌ፡፡ ይህማ የጠፈር ምሳሌ ሆነች እንጂ መቼ የዕለቲቱ ምሳሌ ሆነቻ ብሎ የዕለቲቱን የእሷ ጠፈር የእርሷ የተነሳው ስጋ ብርሃን የጌታ ምሳሌ፡፡ በዕለተ ሰሉስ ትመስላለች፡፡

በዕተ ሰሉስ ለታብቁል ምድር ሀመልማለ ሳእር ዘይዘራዕ በዘርዑ ወበበ ዘመዱ በበ አርአያሁ ወበበ አምሰሊሁ ባለ ጊዜ በእጁ የሚለቀሙ አትክልት በማጭድ የሚታጨዱ አዝእርት በምሳር የሚቆረጡ እፀዋት ለስጋውያን ምግብ የሚሆኑ ተገኝተዋል ከእሷም የመንፈሳዊያን ምግብ የሚሆን ጌታ ተገኝቷልና፡፡ በዕለተ ረቡዕ ትመሰላለች በዕለተ ረቡዕ ለይቁሙ ብርሃናት በቀጸ ሰማይ ባለ ጊዜ ለስጋው ያን ምግብ ጠየሚሆኑ ፀሃይ ጨረቃ ከዋክብት ተገኝተዋል፡፡ ከእሷም ለመንፈሳዊያን ምግብ የሚሆን ጌታ ተገኝቷልና፡፡ በዕለተ ሐሙስ ትመሰላለች በዕለተ ሐሙስ ለታወጽእ ባህር ዘቦ መንፈሰ ህይወት ባለ ጊዜ በልባቸው የሚሳቡ በእግቸው የሚሽከረከሩ በክንፋቸው የሚበሩ የደመ ነፍስ ህያዋን ሁነው የሚኖሩ ፍጥረታት ተገኝተዋል፡፡ በረው በረው የሄዱ አሉ ከዚም የቀሩ አሉ፡፡ በረው በረው የሄዱት የኢጥሙቃን ከዚያው የቀረት የጥሙቃን ምሳሌ፡፡ ያስወባርኮሙ ለክልኤሆሙ በአሃቲ በረከት ይላል ብሎ ብላባቸው የሚሳቡ የሰብአ ዓለም በእግራቸው የሚሳብ ከትሩፋት በደትሩፋት የሚሄዱ ባህታውያን በክንፋቸው የሚበሩ ተመስጦ ያላቸው የሰማዕታት ምሳሌ፡፡ ዕለቲቱ የሱዋ ባህር የጥምቀት ምሳሌ፡፡ በዕለተ አርብ ትመሰላለች በዕለተ አርብ በኩረ ፍጥረት አዳም ተገኝቷል፡፡ ዳግማዊ አዳም ጌታም ከእሳ ተገኝቷልና፡፡ በዕለተ ቀዳሚት ትመሰላለች፡፡ በዕለተ ቀዳሚት ስጋዊ እረፍት ተገኝቷል፡፡ ወእረፈ እግዚእነ እምኩሉ ዘአኃዘ ይግበር እንዲል ከሷም የመንፈሳውያን እረፍት ጌታ ተገኝቷልና ውዳሴ ዘሰኑይ ውዳሴ በአኑይ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ መርያም ዘይትነበብ በዕለተ ሰኑይ ቡል በአንድ ነው ቃለ ጸሃፊ ነው፡፡ እሱ ግን ምስጋናዋን ፈቀደ እግዚእ ብሎ ይጀምራል፡፡ በእለተ ሰኑይ የሚነበብ የሚጸለይ የሚተረጎም አምላክን የወለደች የእመቤታችን ምስጋናዋ ይህ ነው ::
‹‹ፈቀደ እግዚእ ያግዕዞ ለአዳም ኁዙነ ወትኩዘ ልብ፡፡››
እምስት ሺህ ከ5፻ ዘመን በግብርና ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው ዘንድ ወደደ፡፡ ህዙነ ልብ ትኩዘ ልብ ሲል ነው፡፡ ተምያጠ ወተውላጠ ህላዌያት ጽጌያት ወፍያት ትሩፋት ስመ ወግብረ ወልድ እንዲል፡፡ ወክብረ ወልድም ይላል፡፡ አንድም ያዘነ የተከዘ ሊያድነው ወደደ አዳምን የቤተ ፊት ልማድ አላገኘውም፡፡ ቤተ ፈት በዚህ ጊዜ እበላ እጠጣ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ተድላ ደስታ አደርግ ነበር እያለ ያእናል እርሱ ግን አትብላ ያለኝን እጸ በለስ በልቼ ከፈጣሪዬ ትእዛዝ ወጣሁ ብሉ ነውና፡፡ በአልቦቱ ካልእ ኅሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ እንዲል አንድም ጌታ ያዘነ የተከዘ ሆኖ አዳምን ነጻ ሊያወጣው ወደደ፡፡ ተከዘት ነፍስየ እስከ ለሞት እንዲል አመስግነኝ ብትለው ምነው ወደ ሌላ ሄደ ቢሉ፡፡ ወደ ሌላ መለሄዱም አይደል አዳምን አስከትላው መጥታ ነበር እና ቢያየው አነሳው፡፡ አንድም ነገር ከስሩ ውሃ ከጥሩ እንዲሉ አዳም አባቷ ነውና፡፡ ከጥንት ጀምሮ ተርኮ ለመናገር ይሏል፡፡ ያስ ቢሆን ስለመን ፈቀደ እግዚእ አለ ቢሉ መክበሪያዋን ሲሻ ከዚያ ሁሉ ታኦፊላ ሊቃስን ዜና ሐዋርያትን ፅፈሕ ስደድልኝ ቢለው እም ጊዜ እርገሩ ለእግዚእነ እናዳለ መክበሪያቸው ሲሻ፡፡
‹‹ወያግብኦ ኀበ ዘትካት መንበሩ፡፡››
ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ወደደ ክብር ቢሊህ ልዩነት ቦታ ቡሉ ገነት ፍጡር ከሆነ ያለ ቦታ መኖር አይቻለውምና ከዚያውም ዘንድ ካለመደው የለመደውን ቢሰጡት ደስ ይለዋልና ይህማ ለሰማይና ለምድር ምን ቦታ አላቸው ቦታቸው እርሱ አይደለምን አሀዜ ዓለም በእራሁ ኩሉ እሁዝ ውስጥ እዴሁ ይጸውር ድደ ወነብር ጠፈር እንዲል ለሰማይና ለምድር ምን ቦታ አላቸው ቦታቸው እሱ አይደለምን ቢሉ የዕርቅ ምልክት ነው ንጉስ የተጣላውን የሳናፊልህን አትታጠቅ እንዲህ ካለ ቦታ አትውጣ ብሎ ወስኖ ያግዘዋል በታረቀው ጊዜ ርስቱን ጉልበቱን ቤቱን ንብረቱን ይመልስለታል እንደዚህም ሁሉ የዕርቅ ምልክት ነው፡፡
‹‹ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡››
5 ሺሕ ከ5፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ እመቤታችን ንጽህት በድንግልና ጸጋው ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን ቅድስት አለ ንጽህት ጽንዕት ክብርት ልዩ ሲል ነው ንጽህትም አለ ሌሎች ሴቶ ከነቢብ ከቢር ቢነጹ ከኃሊዮ ዓየነጹም ርሷም ነቡብ ከገቢር ከሀልዮ ንጽህት ናትና፡፡ ወኢርኩሰት በምንትኒ እንዘፈጠራ ድንግል በህልናሃ ወድንግል በሥጋሃ አንዲል፡፡ ጽንዕትም አለ ሌሎች ሴቶች ቢጸኒ ለጊዜው ነው ኋላ ግን ተፈትሆ አለባቸው፡፡ እርሷ ግን ቅድመ ጸኒስ ቅድመ ወሊድ፤ ጊዜ ወሊድ ድህረ ወሊድ ጽንዕት ናትና ክብርትም አለ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን ሰማዕታትን ወለዱ ብለን ነው እርሷ ግን ወላዲተ አምላክ ብለን ነውና ልዩም አለ እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የምትገኝ ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡ ዓይኑ ዐ ቢሆን አእመንሮው ለብዎውን ሳይብን አሳድሪብን፡፡ አላፋው አ ቢሆን ለምኚልን ማለት ነው፡፡ ልመናስ ከዚያ በኋላ እንኳን በእሷ ሌሎችን የለባቸውም በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡ ማን ተናግሮታል ቢሉ ኤፍሬም ተናግሮታል ይኽማ እንዳይሆን በግብጻውያን መጽሐፋቸውን በቃላቸው አይገኝምእሳ ብሎ ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያ ተናግሮታል አንድም የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል
‹‹ሰረቀ በስጋ እምድንግል ዘእንበለ ዘርአ ብእሲ ወአድሀነነ፡፡››
ብረሃን ብሎ የሚመጣ ነውና እንደ አርእስት ሰረቅ ብሎ አነሳ ፈቀደ ብሎ ነበርና ወዶም አልቀረብ ዘር ምክንያት ሳይሆነው ከድንገል በስጋ ተወለደ፡፡ ተወልዶም አዳነን፡፡ በስጋ አለ በመለኮቱ አትወልደውምና፡፡ አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ስርዓተ ትስብእቱ እንዲል፡፡ ልደቱ ለዘርያላደረገው እንደበለ ዘርእ ያደረገው ስለምን ነው ቢሉ ቀዳማዊ ልደሩን ለመግለጽ 5ሺህ ከ5፻ ዘመን ኢፈጸም ከእመቤታችን ያለ አባት መወለዱ ቅድመ ዓለም አብ ያለ እናት እንደ ተወለደ ይጠየቃልና፡፡ ልደት ቀዳማዊ ተዓውቀ ወደኃራዊ እንዲል፡፡ ዳግመኛም በዘርዕ በሩካቤ ተዋልዶ ቢሆን እርቅ ቢእሲ ባሉት ነበርና፡፡ ሶበሰ ተወለደ በሩካቤ ብእሲ ውቢእሲት ዘከማየ ብዙኃን እምተሃዘብዎ ወዕምረ ሰይዎ ሀሰት እንዲል፡፡ ያውስ ቢሆን ተፈትሆ ካላት ያላደረገው ተከሌላት ያደረገው ስለምን ነው በሉ ትንቢቱ መሳሌው ሊፈጸም፡፡ ተንቢት ናሁ ደንግል ትጸንስ ልትወልድ ወልደ ተብሎ ተነግሯል ምሳሌው አዳም ከህቱም ምድር ተገኝቷል፡፡ ጌም በህቱም ማኅጸን ለመወለዱ ምሣሌ፡፡ ሄዋን በህቱም ገቦ ተገኝታለች ጌታም በህቱም ማኅጸን ለመወለዱ ምሣሌ፡፡ ቤዛ ይስሃቅ በግዕ ከእህቱ ጉንድ ተገኝቷል ቤዛ አለም ክርስቶስን በእህቱ ማህጸን ለመወለዱ ምሳሌ፡፡ ጽምዐ እስራኤልን ያበረደ ውሃ ከህቱም እብን ተገኝቷል ጽምዐ ነፍሳትን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታን በህቱም ማህጸን ለመገኘቱ ምሣሌ ጽምዐ ሶምሶንን ያበረደ ውሃ በህቱም መንሰከ አድግ ተኝቷል ጽንዐ ኃጢያትን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታን በህቱም ማህጸን ለመገኘቱ ምሳሌ ትንቢቱን አውቆ አናግሯል ምሳሌውንም አንዲህ አውቆ አስመስሏል ፍጻሜው እንደምነው ቢሉ ከመ ትኩን መራሀተ ለሀይማኖት አባይ አንጂ ይላታል ብትወለደው ማህተመ ደንግልናዋ እንዳለተለወጠ ሰው ሲሆን አምላክነቱ ላለመለመጡ ድንግል ወሰብእ ሲባል ለመኖሩ ምሣሌ ነውና፡፡ ‹‹ሌሄዋ አንተ አስኃታ ከይሲ›› ከይሲ ባሳታት በሄዋን ምነው ከይሲ አለ ዲያብሎስ አይደለም ያሳታት ቢሉ በልሳኑ ከይሲ ተሰውሮ ነውና አንደም በማህደሩ ከይሲ አለው ህዳሪ በማህደር ማህደርን በህዳሪ መጥራት ልምድ ነውና አንድም በግብሩ ከይሲ አለው እባብ በመርዙ እንዲጎዳ ዲያብሎም በግብሩ በነገሩ ይጎዳልና፡፡
‹‹ፍትሀ ላእሊሀ እግዚአብሔር እንዘ ይብል ብዙህ አብዝኖ ለህማምኪ ወለጸአርኪ፡፡››
ጻርሽን ጋርሽን ምጥሽን አበዛዋለሁ ብሎ ከፈረደባት በኋላ በህማም ለዲ ወለድኪ ይኩን ምግባ እኪ ህበ ምትኪ አንዲል፡፡
‹‹ዘምረ ልቡ ኅበ ፍቅረ ስብእ ወአግአዛ፡፡››
ሰውን ወደደና ዋዌውን ታግሶ (አግአዛ) ነጻ አደረጋት ፍቅር አሀቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ በአብጸሆ እስከ ለሞት እንዲል ሄዋን ምክንያተ ስህተት ናት ከሲኦል አልወጣችም የሚሉ መናፍቃን ነበሩና በገአዛ አላባቸው አንድም አስከትላት መጥታ ነበርና ቢያያት አነሳት፡፡
‹‹ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡››
ሄዋንን ነጻ ካደረ ልጅስ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጻጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን እየሱስ ክርስቶስ ቃል ዘተሰብዐ ፈቃደ ሰምረ ያልኩት ሰው የሆ ነው እየሱስ ክርስቶስ ነው ይህም ስም ብቻ የመለኮት ብቻ የትስብ እናት ስም አይደለም ከሁለት አካል አንድ አካል ሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ቢሆን ከሁለት ባህርይ በሆን የወጣት ስም ነው እንጂ፡፡ ወእነግር አነሂ ከመ ይመፍትው እስምዮ በቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ ዘእምበለት ትስእብት ወኢ ለትስብእት ዘንበለ መለኮት ክርስቶስ የሰመይ ወእም ቅድመ ትስጉት አልቦ አይሰምዮ በዝንቱ ስም ልቃለ እግዚአብሐየር ክርስቶስ አንዲል፡፡
‹‹ ማህደረ ላእሌነ ፡፡››
ተሰብአና ኃደረ እንደ አለቀና እንደ ጠበቃ ይጠባበቃሉ ኃደረ ያለውን ይዘው ኀድረት እንዳይሉበት ተሰበአ አለባቸው፡፡ ተሰብአ የለውንም ይዘው ተለወጠ እንዳይሉበት አልነሣም ምትሐት ሥጋ በቅድምና ነበረ ባሕርዮን አግዝፎ ታየ የሚሉ መናፍቃን አሉና ላዕሌነ አለባቸው፡፡ ወውስቴትነ ይላል በጽርዕ ምላሹ፡፡ እንደ መስኖ ውሃ ገብቶ ወጣ የሚሉ መናፍቃን አሉና ስጋንም ነፍስንም እንደተዋሃደ ለመጠየቅ ላእሌነ ወውስቴትነ አለባቸው፡፡
‹‹ ወርኢነ ስብሀቲሁ ከመ ስብሀተ አሐድ ዋህድ ለአብሁ፡፡››
ለአባቱ እንደ አንድ ልጅ የሚሆን ክብሩን አየንለት፡፡ ለአባቱ አንድ ልጅ የሆነ ደጅ አፍ የመሰለው ማጀት የጎረስው ሁሉ ገንዘቡ ነው ለእርሱም የአብ ገንዘብ ሁሉ ገንዘቡ ነውና እስመ ኩሉ ዘቦ ለአቡየ ዚአየ ውእቱ እንዲል፡፡ አንድም ለአባቱ እንደ አንድ ልጅነቱ የሚሆን ክብሩን አየንለት ወይሰገድ ከመ ዋህድ እንዲል አንድም ያባቱን ጌትነት በደብረ ሲና እንዳየ የእርሱንም ጌትነት በደብረ ታቦር አየንለት አንድም አባቴ ኤልያስ አድሮ አንድ ምውት ኤልሳእ አንድሮ ሁለት ምውት ሲያስነሳ እንዳየነው፡፡
እሱም ስጋን ተዋህዶ የአራት ቀን ሬሳ አልአዛርን ሲያስነሳ አየነው የብሉይንም ለአብ የሐዲሱን ለወልድ ሰጥቶ አድሎ መናገር ልማድ ነው እንጂ፡፡ ሁሉም በሁሉ አሉ ያውስ ቢሆብ ወዴት ነበርና ርኢነ አለ ቢሉ የብረሉይን የእነሙሴን ዓይን አድርጎ፡፡ የሃዲሱን የእነጴጥሮስ ዓይን አደርጎ ከዚያ ሁሉ አባ ህርያቆስ ንህነ እሙንቱ እለ በላዕነ ምስሌሁ እምድኀረ ትንሣኤሁ አንዳለ፡፡ የሓዋርያትን መብል መብል አደርጎ፡፡
‹‹ ሠምራ ይሣዐለን፡፡››
ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ ሦስት ጊዜ ፈቀደ ሠምረ እለ ለአዳም ለሔዋን ለሕፃናቱ፡፡ ለሥጋ ለነፍስ ለደመ ነፍስ እንደ ካሰ ለማጠየቅ
‹‹ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡››
ይቅር ይለን ዘንድ ከወደደ ለ3ጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን አንዳነሣን ለምኚልን፡፡
‹‹ርእየ ኢሳይያስ ነቢይ በመንፈስ ትንቢት የምስጢር ለዓመኑኤል፡፡››
ነቢዮ ኢሳያስ ትንቢት በሚገልጽ በመንፈስ ቅዱስ የዐደማኑኤልን ምሥጢር አየ አጸና፡፡
‹‹ ወበእንተዝ ጸርሐ አንዘ ይብል፡፡›› ስዚህ ነገር አሰምቶ ተናገረ፡፡ ዐማኑኤል መለት ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው አዝ ስም ዐቢይ ጥቀ ወአይደሉ ፈሊጦቶ አንዲል፡፡ ጸርሐ አለ ጮሆ የተናገሩት ከሩቅ እንዲሰማ ነገሩ ጽንፍ እሰከ ጽንፍ ይደርሰልና፡፡ ጸርሐ አለ አንጂ ተናገረ ሲል ነው፡፡
‹‹ ሐፃን ተወልደ ለነ፡፡››
ሕፃን ተወለደልን፡፡
‹‹ውልድ ተውሃበ ለነ፡፡››
ወልድ ለሕማም ለሞት ተሰጠልን አንድም ወልድ ተውሀበ ለነ ለኩነተ ሥጋ ተሰጠልን ወሕፃን ተወልደ ለነ ሕጻንም ሆኖ ተወለደልን፡፡ ለመለኮት የአካልም የክብርም ሕፀፅ ነበረበት ሥጋ ምላት ሆነው የሚሉ መናፍቃን ነበሩና ለነ አለባቸው ለርሱ ቢሆን ሎቱ ይል ነበር፡፡ ይህም ደበአርዮስ ያሳይበታል፡፡
‹‹ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡››
ወልድ ዘበላዕሉ ሕጸን ዘበታህቱ ከሚባል ልጅሽ እመቤታችን ጽንዕጽ በድንግልና ጸጋውን ክብሩን አንዲያሣ ለምኚልን፡፡
‹‹ ተፈሣሕ ወተሐሠይ ኦ ዘመደ ዕጓለ እመሕያው፡፡››
ባሕርየ ዕጓለ እመሕያው በውሰጥ በአፍአ በነፍስሰ በሥጋ ደስ የበልህ፡፡
እሰመ አፍቀሮ እግዚብሔር ለዓለም፡፡
እግዚአብሔር ሰውን ወዶታልና፡፡
‹‹ ወመጠወ ወልዶ ዋህደ፡፡››
ልጁን ለሕማም ለሞት እስከ መስጠት ደርሶ፡፡ አንድም ወዶ ምን አደረገለት፡፡ ትለኝ እንደሆነ ተቀዳሙ ተከታይ የሌለው ልጁን ለሕማም ለሞት አሳልፎ እግዚአብሔር ለዓም፡፡ እስከ ወልዶ ዋሕደ መጠወ ወወሀበ ቤዛ ኩሉ እንዲል፡፡
‹‹ ከመ ይሕየው ኩሉ ዘየ አምን ቦቱ እስከ ለዓለም ››
ይሕየው እስከ ለዓለም ኩሉ እሰከ ለዓለም ዘየአምን እስከ ለዓለም ብሎ ይገጥሟል፡፡ ኩሉ እስከ ለዓለም እስከ ምጽአት ድረስ የሚነሣ ትውልድ ሁሉ፡፡ ዘየአምን እስከ ለዓለም እስከ ምጽአት ድረስ የሚያምንበት አለ ከዚያ በኋላ ያመኑት እምነት ኤጠቅምምና፡፡ ከዚያ በኋላስ አይሁድስ እንኳ እፎኑ ርእር ታመጽእ አሚነ እንዲል እ ኮነ ወልደ ዕጓለ እመሕያው ወለቅዲሳን ኮነት ርስቱ ይላሉ አይጠቀሙበትም እንጂ፡፡ ይሕየው እስከ ለዓም ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው ኢተመይጠ ቋዕ እስከ አመ ነትገ ማየ አይኀ፡፡ ኢወለደት ሜልኮል እሰከ አመ ሞተት እንዲል፡፡
‹‹ፈነወ ለነ መዝራዕቶ ልዑለ›› ልዑል ክንዱን ረቂቅ ክንዱን ሰደደልን ፈነወም ቢል በሥጋ ነው እንጂ በመለኮቱ አይደለም እፎኑ የፌንዎ በመለኮቱ ዘእንበለ ዳዕሙ በትስብእቱ ዘነሥኦ በአምሳሌ ላዕከ ይፌንዎ በአምሳለ ላእከ እንዲል፡፡ ክንድ አለው የሰው ኀይሉ በክንዱ እንዲታወቅ የአብም ኀይሉ በወልድ ታውቋልና፡፡ አንድም ክንድ ከአካል ሳይለይ የወደቀውን ዕቃ አንሥቶ ይመለሳል እርሱመ ከአብ አንድነት ሳየለይ አዳምን አድኗል፡፡ አንድም በከንድ የራቀውን ያቀርቡባል የቀረበውን ያርቁበታል በርሱም ጸድቃንን ንሁ ኃቤየ ብሎ ያቅርብበታል ኃጥአንን ሑሩ እምኔየ ብሎ ያረቅበታልና፡፡
‹‹ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡››
እዱ መዝራዕቱ ከሚባለው ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
ዘሀ ሎ፡፡
እምቅመ ዓለም የነበው፡፡
ወይዘሉ፡፡
ዓምን አሳልፎ የሚኖረው፡፡
አመጸአ፡፡
ለኪነት ሥጋ የመጣው፡፡
‹‹ ወካዕበ የመጽእ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእነበለ ውላጤ፡፡››
ዳግመኛ ዓለሙን ለማሳለፍ የሚመጣው፡፡ ካንች ሳይለወጥ ሰው የሆነው አምላካዊ ቃል ኢየሱስ ክርሰቶስ፡፡
‹‹ ኮነ ፍጹመ ሰብአ፡፡››
ፍጽም ሰው ሆነ፡፡ ሰው የሆነውን ሰው ሆነ ማለት መንድር ነው ቢሉ ፍጹመ ለማለት ደገመው፡፡ አንድም ዘሀሎ፡፡ እምቅድመ ዓለም የነበረው ወይሄሉ፡፡ ዓለሙን አሳልፎ የሚኖረው ነው፡፡ ዘመጽአ፡፡ ዓለሙን አሳልፎ የሚኖረው ለኪነተ ሥጋ የመጣው ነው፡፡
‹‹ ወከዕበ የመጽእ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ዘተሰብአ ዘእንበለ ውላጤ፡፡››
ለኩነተ ሥጋ የመጣው፡፡ ዳግመኛ ዓለሙን ለማሳለፍ የሚመጣው ነው፡፡ ደግመኛ ዓለሙን ለማሳለፍ የሚመጣው፡፡ ካንች ሳይለወጥ ሰው የሆነው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ ፍጹመ ሰብአ፡፡ ፍጸም ሆነ፡፡ ትቅስ ወኢተዋሐደ በመንፈቀ ህላዌ በኢኮነ ካልአ እንስሳ ዘበአንትጎ፡፡ አላምሉዕ ወፍጹም ውእቱ በአሐዱ ሀላዌ የገብር ዘክልኤቱ ህላዌያት እንዲል፡፡ ከዚህ ነፍስ አልነሣም፡፡
ምትሐት ኀድት፡፡ ተለወጠ የሙሉ መናፍቃን አሉና ለዚህ ያመታል፡፡
‹‹ ኢተበዓደ ወኢተፈልጠ በኪሉ ግብሩ ወልድ ዋሕድ፡፡››
አሁን ነፍስ አልነሣም ምትሐት ላሉት ይመልሳል፡፡ ተቀዳሙ ተካታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ በሥራው ሁሉ ከኛ አልተለየም፡፡
‹‹አላ አሐዱ ራእይ፡፡››
አንድ ግብር ነው እንጂ፡፡
‹‹ወአሐዱ ህላዌ፡፡››
አንድ ባሕርይ ነው እንጂ፡፡ ወአሐዱ፡፡
አንድም ነው እንጂ፡፡
ሠስት ጊዜ አሐዱ አሐዱ አሐዱ አለ በሦስት ወገን የመስለናል በኀይለ ዘርዕ በኀይለ ንባብ በኀይለ እንስሳ፡፡
‹‹ መለኮት ዘእግዚአብሔር ቃል፡፡››
አካላዊ ቃል አንድም አሁን ጎድረት ላለው ይመልሳል፡፡ ተቀዳሜ ተከታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ በሥራው ሁሉ ከነሣው ሥጋ አልተለየም፡፡
‹‹ አላ አሐዱ ራእይ፡፡››
አንድ ግብር ነው አንጂ፡፡
ወ1ዱ ህላዌ አንድ ባሕርይነው እንጂ፡፡
‹‹ ወአሐዱ መለኮት፡፡››
አንድ አካል ነው እንጂ፡፡
እስመ 3ቱ ኁልቁ መለኮቱ እንዲል፡፡ እንድም ተለወጠ ላሉት ይመልሳል፡፡ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ ሰውም ቢሆን ከአብ ከባሕርይ አባቱ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ አለተለየም፡፡
እላ አሐዱ ራእይ፡፡
አንድ ኀብረ መልክእ ነው እንጂ፡፡ ወአሐዱ ህላዌ፡፡ አንድ ባሕርይ ነው አንጂ፡፡ ወአሐዱ መለኮት፡፡ አንድ አገዛዝ ነው አንጂ፡፡ ውስተ ኩሉ በሐውረት መለኮቱ እንዲል፡፡
‹‹ ዘእግዚአብሔር ቃል፡››
አካላዊ ቃል፡፡
‹‹ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡››
ይቆየን የዕለተ ሰኞ ክፍል 2 በሚከጥለው ሳምንት ይቀጥላል:: ............ቸር ያቆየን!!!!!

Saturday, August 7, 2010

ውዳሴ ማርያም አንድምታ በዕለተ ሰንበት እሁድ ክፍል 1

ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን::
ሰንበት አይሁድ አለችና ከዚያች ሲለይ ሰንበተ ክርስቲያን አለ :ያውስ በከንቱ ነውን ወበዛቲ ዕለት እሙነ ተፈጸመ እንዲል ሁለቱን ቀን የሚያከብር የሆነ እንደሆነ ዓርብ ከሰዓት ይወጣል እሁድ በሰዓት ይወርዳል::አንዱን ቀን የሚያከብር እንደሆነ ቅዳሜ ከሰዓት ይወጣል እሁድ ከሰዓት ይወርዳል: እንዲህ እያለ ሲኖር ጌታ የሚመጣው በዕለተ እሁድ ነውና እንደወጣ ይቀራል: በዚህም ቀን እመቤታችን ከወትሮው ጊዜዋ ቀደም ብላ መጥታ ለምንት ኢወደስከኒ በዛቲ ዕለት አለችው ከወትሮው ጊዜዋ ቀደም ብላ ከመጣች ስለምን ለምንት ኢወደስከኒ አለችው ቢሉ የህሊናውን አውቃ: እሱም በገድል ተቀጥቅጦ ነዋሪ ስለሆነ ጥቂት ወይን ጠጥቶ ዕረፍት ሽቶ ነበርና: ጳውሎስ ጢሞትዮስን ህዳጠ ወይነ ቶስሕ በእንተ ሕማመ ከብድከ ወበእንተ ደዌከ ዘዘልፍ እንዳለው:ዛቲ ዕለት ዓባይ ወክብርት አላት: ዛቲ ዕለት ተዓቢ እምኩሎን ውዳሴያት አለችው ከዚህ በኋላ ባርክኒ ይላታል በረከተ ወልድየ ወአቡየ ወመንፈስቅዱስ ይህድር በላዕሌከ ትለዋለች: ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል በዚህም ቀን በቤተ መቅደስ ባሉ ንዋያት በመሶብ ወርቅ በማዕጠንተ ወርቅ በበትረ አሮን እየመሰለ ሲያመሰግናት አድሯል ::
"ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት እምአንስት:አንቲ ውእቱ ዳግሚት ቀመር እንተ ትሰመይ ቅድስተ ቅዱሳን: ወውስቴታ ጽላተ ኪዳን:"
ንዕድ ክብርት ሆይ ከሴቶች ተለይተሽ የሥላሴ ባለሟል ተባልሽ : ከተለዩ የተለየሽ ከከበሩ የከበርሽ ቅዱሳን ኪሩቤል የተሳሉብሽ ቅዱሳን ካህናት የሚያመሰግኑሽ ሁለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ: ህግ የተጻፈባት ጽላት ያለብሽ ሕጉን ኪዳን ይለዋል ብትጠብቁት ይጠብቃችኋል ብሎ ተከይዶበታልና::
"10ቱ ቃላት እለ ተጽሕፋ በአጻብዒሁ ለእግዚአብሔር: ቀዲሙ ዜነወነ በየውጣ እንተ ይእቲ ቀዳሜ ስሙ ለመድሃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ::"
ኪዳንም ያልሁት በአፃብዐ እግዚአብሄር የተጻፉ ዐሥሩ ቃላት ናቸው በግብር አምላካዊ ስለተገኙ በአፃብዐ እግዚአብሄር አለ: ከስመ ሥጋዌም የሚቀድም ስሙን በየውጣ ነገረን: ከስመ ስጋዌ የሚቀድም ስሙን : ኢታምልክ ባዕደ አምላክ ዘእንበሌየ ብሎ በዮድ ፊደል ነገረን አለ: ዮድ ለአሌ ዐሥረኛ እንደሆነች ኢታምልም ለኢትፍቱ ዐሥረና ናትና: አንድም ከስመ ሥጋዌው የሚበልጥ አሙን በየውጣ ነገረን አለ:ቀዳሜ ፍጥረት ብሄሞት ቀዳሚሆሙ ለአህዛብ አማሌቅ እንዲል: የውጣ በሃገራቸው ዕዝል ቅጽል የላትም አንድ ጭራ ናት: ዐሠርቱም በሃገራችን ዕዝል ቅጽል የላትም አንድ ጭራ ናትና: አንድም ዋሕድ ቃለ እግዚአብሔር በአፃብዐ መንፈስቅዱስ በማህጸኑዋ እንዲቀረጽ ዐሠርቱ ቃላትን በጽላቱ ጽፎ በማኖሩ ነገረን:ታሪክ:- እስራኤል ከግብጽ ከወጡ በኋላ ሙሴ አሮንና ሖርን ከተማ ጠባቂ አድርጎ ኢያሱን አስከትሎ ደብረሲና ሄዶ ስድስት ቀ ቃል ለቃል ይነጋገረዋል: ሠላሳ ዐራት ቀን በልቦናው የሳለበትን እየነገረ ያጽፈዋል: ከዚህም በኋላ ሙሴ ቢዘገይባቸው እስራኤል ከአሮን ዘንድ ሄደው አሮን አሮን ግበር ለነ አማልክተ እለ የሐውር ቅድሜነ ወእለ ይፀብዑ ፀረነ እስመ ዝኩሰ ሙሴ ዘአውጻነ እምድረ ግብጽ ኢነአምር ከመ ምንተ ኮነ :አመሌ አመሌ ሲል ደብረ ሲና ያየው እሳትም በልቶት እንደሆነ ወደ ኤርትራ ተመልሶ ሄዶ አስጥማው ቀርቶም እንደሆነ ሙሴ የሆነውን አናቅምና ጣዖት ስራልን አሉት: እሱም እምቢ ብላቸው እስራኤል ቁጡአን ናቸው በደንጊያ ወግረው ይገድሉኛል: ይሁንም ብላቸው ፈጣሪዬ ይጣላኛል ብሎ እስራኤል ሃብት ወዳጆች ናቸው ከዛሬ ነገ ሲሉ ወንድሜ ይመጣልኛል ከነገር እድናለው ብሎ ሴቶችንም ወንዶችንም ከግብጽ ያወጣችሁትን ገንዘባችሁን አምጡ አላቸው: ሰይጣን አነሳስቷቸዋል እና እንዋል እንደር ሳይሉ ዕለቱን አመጡለት ጉድጓዽ አስምሶ እሳት አስነድዶ ከዚያ ላይ አስጣለው: ከዚህ በኋላ አንድ ቀንዱ የወርቅ አንድ ቀንዱ የብር ጅራቱ የሃር የሆነ ምስል መቶ ቆመ:ይህስ ምትሃት ይመስላል ብሎ ተድበልብሎ ወጣ እሱ ቅርጽ አውጥቶ አሰርቶታል::
ከዚህ በኋላ በፍና ተሳልቆ ጌሰም በዓለ እግዚእ ብሎ አዋጅ ነገረ : ከዚህ በኋላ መስዋዕቱን በልተው ሲዘፍኑ ሲያጨበጭቡ: ሙሴ ሙሴ አበሱኒ እስራኤል ሕዝብከ:አለው ጸብ ተጀመረ ህዝብየ ይላቸው የነበረ ሕዝብከ አለው አባት ልጁን ሲጣላ ያ ልጅሽ እንዲህ አደረገ እንዲል:ሰንኪያስ ወርደህ ሥራ ቅፃ አለው: ከዚህ በኋላ ዓሥሩን ቃላት በጽላት ጽፎ ሰጠው ያን ተቀብሎ እያሱን አስከትሎ ሲሄድ እስራኤል ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ይዘፍናሉ ያጨበጭባሉ: የአርበኛ የሰልፈኛ ድምጽ አይደል አለው;ቢደርስ ከዚያ ጣዖቱን አቁመው ተረፈ መስዋዕቱን በልተው ሲሰግዱ አየ ቢደነግጥ ከእጁ ወድቆ ጽላቱ ተሰበረ: ዛሬ ከቄስ እጅ ጥና ወድቆ እንዲሰበር አንድም በጽላቱ ጣዖቱን መታው ጣዖቱም ጽላቱም ተሰበረ ከዚህ በኋላ ወርቁን አስፈጭቶ ከፈሳሽ ባህር አስበጥብጦ ጠጡ አላቸው: ፍቅረ ጣዖት ያደረበት ከከንፈሩ ከግንባሩ እንደ ለምጽ ተቀረጸበት: ይህን ምልክት አድርጎ ሌዋውያንን ከበር አቁሞ በሏቸው አትማሯቸው: አባት ልጁን ልጅ አባቱን ወንድም ወንድሙን አይማረው ብሎ 3000ሺህ ሰዎች አስፈጅቷል: አንፈስክዎ ለእግዚአብሔር እስኪላቸው ድረስ: ከዚህ በኋላ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት ቀር ከመ ቀዳምያት አለው: የቀደመውን አስመስለህ አምጣ አለው ይዞ ሄዶ ቃሉ በግብር አምላካዊ ተገኝቷልና ይህውም ምሳሌ ነው: የቀደመው ጽላት የአዳም ሁለት መሆኑ የስጋውና የነፍሱ በግብር አምላካዊ መገኘቱ አዳም እንበለ ዘርዕ ለመገኘቱ ምሳሌ: የኋለኛው ጽላት የእመቤታችን ሁለት መሆኑ የስጋዋና የነፍሷ: ቀር ከመ ቀዳምያት አለው: እመቤታችን በዘር ለመገኘቷ ምሳሌ:ቃሉ የጌታ ምሳሌ በግብር አምላካዊ መገኘቱ: ጌታ እንበለ ዘርዕ ለመገኘቱ ምሳሌ: የቀደመው ጽላት የዕንቁ ነው የኋለኛው ጽላት ዕብነ በረድ ነው::
"ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ውላጤ:ወኮነ አራቄ ለሐዲስ ኪዳን:በውሂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሆሙ ለመሃይምናን ወለሕዝብ ንጹሃን:"
ካንቺ ሳይለወጥ ሰው የሆነ ለወንጌል ሊቀ ካህናት ለመንግስተ ሰማያት አስታራቂ ሆነ: ሐዲስ ኪዳን ወንጌል ብሉይ ኪዳን ኦሪት:ሐዲስ ኪዳን መንግስተ ሰማያት ብሉይ ኪዳን ምድረ ርስት: በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ስጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን አዳናቸው: አንድም በዕለተ ዓርብ በቀኖት የፈሰሰውን ደሙን መላዕክት በአውራ ጣታቸው ተቀብለው እረጭተውታል:ይህንስ ያህል አይደፍሩም ብሎ በጽዋዓ ተቀብለውታል: ዛሬ ቤተክርስቲያን የሚሰራበት ደሙ የፈሰሰበት ቦታ ነው: ታሪክ:- ጳልቃን ጣልቃን የሚባሉ አዕዋፍ አሉ ልጆቻቸውን ይወዳሉተንከባክበው አቅፈው ያኖሩዋቸዋል ልጆቹ ተጫወትን ብለው ፊታቸውን ይጸፉታል ይሰማቸዋል ራሳቸውን ቆርጠው ይገድሏቸዋል ከዚህ በኋላ በሦስተኛው ቀን ከናታቸው ካባታቸው ጎን ቢሉ ደም አውጥተው ቀብተው ያስነሷቸዋል: ጳልቃን ጣልቃን የተባሉ ሥላሴ ናቸው ልጆቻቸውን ተንከባክበው እንዲያኖሩዋቸው በገነት አዳምንና ሄዋንናክብረው አኖሯቸው ተጫወትን ብለው ፊታቸውን እንዲጸፉ አምላክነትን ሲፈልጉ ተገኝተዋል: ራሳቸውንም ቆርጦ እንደመግደል በሞተ ስጋ ሞተ ነፍስ በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ፈርደውባቸዋል በሦስተኛውም ቀንከናታቸው ካባታቸው ጎን ቢሉ ደም አውትተው ቀብተው እንዲያስነሷቸው: አንተ አቡነ ወአንተ እምነ የሚባል ጌታ ከጎኑ ደሙን አፍስሶ ለማዳኑ ምሳሌ " ሰአሊ ለነ ቅድስት"
በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ስጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን ካዳነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን
"ወበእንተዝ ናዓብየኪ ኩልነ ኦ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ: ንጽህት ኩሉ ግዜ:ንስህል ወናንቀዓዱ ሃቤኪ :ከመ ንርከብ ሣህለ በሃበ መፍቀረ ሰብእ:"
መጽሃፍ ላለፈውም ለሚመጣውም አጸፋ ይሰጣል: አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ስለዚህ ነገር ሁላችን እናከብርሻለን እናገንሻለን:ንጽህት ኩሎ ጊዜ ንስህል ኩሎ ጊዜ ብሎ ይገጥማል: ሁልግዜ ንጽህት የምትሆኚ:ሁልጊዜ አይነ ልቦናችንን ወዳንቺ እንሰቅላለን: ሰውን ከሚወድ ሰው ከሚወደው ከርሱ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ::
"ታቦት ዘወርቅ ልቡጥ እምኩለሄ ዘግብር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ: ይትሜሰል ለ ዘእግዚአብሔር ቃል:"
ሸምሸር ሸጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በአፍአ በውስጥ በወርቅ የተለበጠ ታቦት: አካላዊ ቃልን ይመስልልናል አንድም መመሳሰል የጋራ ነው ብሎአካላዊ ቃል ታቦትን ይመስልልናል: ታቦት የእመቤታችን ምሳሌ: (ዕፅ ዘኢይነቅዝ) የአብርሐም:ዘኢይነቅዝ አለው በአምልኮተ ጣዖት አይለወጥምና: አንድም ታቦት የጌታ ምሳሌ ዕፅ ዘኢይነቅዝ የእመቤታችን ዘኢይነቅዝ አከ በሃጥያት አትለወጥምና አንድም ታቦት የጌታ ምሳሌ:ዕፅ ዘኢይነቅዝ የአብ: አሁን ዘግቡር ሲል ያውካል::
"ዘኮነ ሰብአ ዘእንበለ ፍልጠት ወኢውላጤ: መለኮት ንጹህ ዘአልቦ ሙስና:ዘዕሩይ ምስለ አብ: ወቦቱ አብስራ ለንጽህት::"
መለወጥ ሳያገኘው መለየት ሳያገኘው ሰው የሆነ:ንጹህ ከተፈልጦ ከተድህሮ አንድም ንጹህ ካለመመለክ ንጹህ የሚሆን መለወጥ የሌለበት በአብ ዕሪና ያለብባለመለወጡ አለመለወጡአን: ባለመለየቱ አለማለየቷን ነገራት: አንድም በዕጽ ዘኢይነቅዝ አንድም በገብርኤል አድሮ ነገራት::
"ዘእንበለ ዘርዕ ኮነ ከማነ በኪነ ጥበቡ ቅዱስ: ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ርኩስ: ደመረ መለኮቶ:"
ከጥበብ በሚበልጥ ጥበብ ዘር ምክንያት ሳይሆን እንደኛ ሰው ሆነ ከጥበቡ በሚበልጥ ጥበቡ አለ: ዓለሙን ከፈጠረበት ሰው ሆኖ ዓለሙን ያዳነበት ትበብ ይበልጣልና: አንድም በፍጹም ጥበቡ እንደኛ ሰው ሆነ: አደፍ ጉድፍ ሳያገኝሽ ከስጋሽ ስጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆነ: መለኮቱን አዋህዶ::" ሰአሊ ለነ ቅድስት::"
መለኮቱን አዋህዶ ሰው ከሆነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን::ታቦትን ከዚህ ይናገራሉ ሸምሸር ሸጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት አቆልቋዩ ሁለት ክንድ ከስንዝር ቁመቱ ክንድ ከስንዝር አድርገህ ታቦትን ቅረጽ ብሎታል: በአፍአ በውስጥ በወርቅ ለብጠው: አራት ቀለበት ሁለት መሎጊያ አብጅለት ብሎታል:ምስሐልንም ሁለት ክንድ ከስንዝር ሞላልነቱ ርሁቡ ክንድ ከስንዝር ቅረጽ ብሎታል የዚህ ቁመት የለውም ሁለቱን ኪሩቤል እንደሚናተፍ አውራ ዶሮ አስመስለህ ሳላቸውዙርያውን ፈለግ አውጥተህ የማይረጋ ብጽብጽ ወርቅ አፍስስበት አለው ይህውም ምሳሌ ነው: ሁለት ክንድ ከስንዝር ከአዳም እስከ ኖህ ያለው ዘመን ነው:2256 ይሆናል : በ2256 ዘመን አርአያ ድንግል ታቦተ ኖህ ለመገኘቷ ምሳሌ ነው: ክንድ ከስንዝር ቁመት ከኖህ እስከ ሙሴ ያለው ዘመን ነው 1600 ይሆናል: በ1600 ዘመን አርአያ ድንግል ታቦተ ሙሴ ለመገኘቷ ምሳሌ ነው: ክንድ ከስንዝር ርሁብ ከሙሴ ጀምሮ እስከ እመቤታችን ያለው ዘመን ነው: 1600 ይሆናል: በ1600 ዘመን ሐመረ ኖህ እና ታቦተ ሙሴ ምሳሌዋ የሚሆኑ አማናዊት ድንግል ለመገኘቷ ምሳሌ ነው: ታቹ የንጹሃን አበው ሁለት መሎጊያ የፍቅረ ቢጽና የፍቅረ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው: ዐራት ቀለበት በርእይ በሰሚዕ በገሢሥ በአፄንዎ በዚህ ሁሉ ንጽህት ናትና: ዳሩና ዳሩ የሃና የኢያቄም ገቢይቱ (ግበቱ) የርሷ ምሳሌ ሁለቱ ኪሩቤል የመልአከ ዑቃቢና የመልአከ መበስር ምሳለ ነው; በአመት አንድ ቀንሊቀ ካህናቱ ገብቶ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ድምጽ ሰምቶ ይወጣ ነበር: እርሷም በመልአከ ዑቃቢ ተጠብቃ ከመልአከ መበስር ድምጽ ሰምታ ጌታን ጸንሳ ለመገኘቷ ምሳሌ ነው: አንድም የኦሪኒና የሶፍያ ምሳሌ ነው: ባስልዮስን ከነ አትለያቸው ሳላቸው ብላዋለችና:ናንድም የዮሴፍና የሰሎሜ ምሳሌ ነው:በመከራዋ ጊዜ አልተለዩአትምና ፈለግ የልቦናዋ ምሳሌ ብጽብጽ ወርቅ የሁከት መንፈሳዊ ምሳሌ ሁከት መንፈሳዊ ከልቦና አይደለምና::
"መቅደስ ዘይኬልልዋ ኪሩቤል እለ ሥዑላን በሥዕለ እግዚአብሔር:ቃል ዘተሰባ እምኔኪ አንጽሕት ዘእንበለ ውላጤ: ኮነ ሠራዬ ሃጥያት ወደምሳሴ አበሳነ ::"
እግዚአብሔር በፈጠራቸው በኪሩቤል አምሳል ሙሴ የሳላቸው ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ ሙሴ አንቺ ነሽ: አንድም እግዚአብሄር በፈጠራቸው ኪሩቤል አምሳል ሰሎሞን የሳላቸው ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ ሰሎሞን አንቺ ነሽ: አንድም ኦ መቅደስ ዘኮነ ለሊሁ እግዚአብሄር ሊቀ ካህናት እንዲል ጌታ በማህጸን ዘደረብሽ መቅደስ አንቺ ነሽ: ሣይለወጥ ካንቺ ሰው የሆነው አካላዊ ቃል: ስለ ስጋው ስለ ነፍስ ስለ ጊዜው ስለ ዘላለሙ: ይደጋግማል በውስት በአፍአ በነፍስ በስጋ ሃጥያታችንን የሚያስተሰርይልን ሆነ::" ሰአሊ ለነ ቅድስት"
ሃጥያታችንን ከሚያስተሰርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አሜን !!!!!:: ይቆየን የእሁድን ቀጣይ ክፍል በሚቀጥለው እሁድ..........ቸር ያቆየን!

ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 2

5:- ወእቀውም ዮም በትህትና ወበ ፍቅር በዛቲ ዕለት ቅድመ ዝንቱ ምስጢር ግሩም: ዮምና በዛቲ ዕለት አንድ ወገን: ቀድሶ ያቆረበባት ቀን ናት: እንደጠሉኝ ልጥላቸው እንደናቁኝ ልናቃቸው ሳልል በፍቅር በትህትና ጸንቼ ግሩም በሚሆን በስጋው በደሙ ፊት እቆማለው:: ሐተታ:- ስጋው ደሙን ምስጢር አለው ከአምስቱ አዕማደ ምስጢር አንዱ ምስጢረ ቁርባን ነውና:: አንድም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት በልሳነ ነፍስ ያናግራልና:አንድም ሲለወጥ አይታይምና: ለበቁትም ሰዎች ስንኳ ከተለወጠ በኋላ ነው እንጂ ሲለወጥ አይታይምና: አንድም የወድያኛውን ምስጢር ይገልጣልና ግሩም አለ: በሚገባ ቢቀበሉት ግሩም ጸጋ ያሰጣልና: በሚገባ ባይቀበሉት ግሩም ፍዳ ያመጣልና: አንድም ግሩማን መላእክት ከበውት ይቆማሉና አንድም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት ግሩም ምስጢርን ይገልጻልና: አንድም የአምላክ ስጋ የአምላክ ደም አይገርም ማን ይገረም: አንድም የሚወደድ ሲል ነው: ኢትርዓይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ እንዲል አንድም ልዩ ሲል ነው: ግሩም ምክሩ እመጓለ እመ ህያው እንዲል::
ወቅድመ ዝንቱ ማዕድ ወቁርባን ዐ ማእድም ያለው ስጋው ደሙ ነው: ሐተታ:- ማእድ አለው ማእድ ስጋዊን ከበው እንዲመገቡት ይህንም አእሩግ ህጻናት ከበው ይቀበሉታልና: አንድም ለማእድ ስጋዊ ሰው እንዲመረጥለት ለዚህም የበቃና ያልበቃ ይመረጥለታልና አንድም ማዕደ ነፍስ ነውና ቁርባን እንዳለፈው: አንድም ማእድ ጻህል ጽዋው ቁርባን ስጋው ደሙ ነው ::
6:- በአማን ቁርባን ውዕቱ ዘእይክሉ ይጥዐሙ እምኔሁ ግሙናነ መንፈስ ልቦናቸውን ሰውነታቸውን በሃጥያት ያሳደፉ ሰዎች ሊቀበሉት የማይገባቸው መለኮት የተዋሃደው እውነተኛ ቁርባን ነው: ሐተታ:- ማን ይከለክላቸዋል ቢሉ ራሳቸው ፈርደው ይከለከላሉና አንድም ቄሱ ይከለክላቸዋልና አንድም እግዚአብሔር በምልዓት በልቡናቸው አድረው ይከለክላቸዋልና: ህዝቡ ያልበቁ ልዑካኑ የበቁ የሆኑ እንደሆነ የህዝቡን ለልዑካኑ ይደርብላቸዋል: ልዑካኑ ያልበቁ ህዝቡ የበቁ ይሆኑ እንደሆነ የልዑካኑን ለህዝቡ ይደርብላቸዋል ህዝቡም ልዑካኑም ያልበቁም የሆኑ እንደሆነ መልአክ ወስዶ በበርረሃ ለወደቁ ባህታውያን ያቀብላቸዋል: ምግብ ሁኑአቸው የሚኖር ቅሉ ይህ ነው: ያም አያውቅም ይህም አያውቅም ያ እንዳይታበይ ይህ ከቀቢጸ ተስፋ እንዳይደርስ ነው::
አኮ ከመ መስዋእቶሙ ለቀደምት አበው ዘበደመ በግዕ ሐርጌ ወላህም:: በደመ በግዕ በደመ ላህም የቀደሙ ሰዎች ይሰውት እንደነበረ መስዋእት አይደለም: አንድም የቀደሙ ሰዎች በደመ ላህም በደመ በግዕ ይሰዉት እንደነበረ መስዋዕት አይደለም: ሐተታ:-ሃርጌን ለበግ የቀጸሉ እንደሆነ ሙክት በላህም የቀጸሉ እንደሆነ ጊድር ማለት ነው::
7:- አላ እሳት ውዕቱ:: መለኮት የተዋሃደው ቁርባን ነው እንጂ እሳት መለኮት የተዋሃደው ቁርባን ነው እንጂ:እሳት ማህየዊ ለርቱአነ ልብ ለዕለ ይገብሩ ፈቃዶ:: ለና ለ አንድ ወገን እሳትም ብዬ ብላችሁ አንድነቱን ሶስትነቱን አውቀው ህማሙን ሞቱን አምነው ሃጥያታቸውን ለመምህረ ንስሓ ነግረው መምህረ ንስሃ ያዘዘውን ሰርተው በሚገባ ለሚቀበሉ ሰዎች የሚያድን እሳት ነው::ሐተታ:- እሳት በመጠን የሞቁት እንደሆነ የበሉት የጠጡትን ያስማማል: ደዌ ይከፍላል: ይህም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት ይህወተ ስጋ ህይወተ ነፍስ ይሆናል: ደዌ ነፍስ ያርቃልና::
እሳት በላዒ ለአማጽያን ለእለ ይክህዱ ስሞ:: ለና ለ አንድ ወገን ነው እሳት ማህየዊም ብላችሁ ስመ አምላክነቱን ለሚክዱ ሰዎች የሚያቃጥል እሳት ነው:: ሐተታ:- ስመ አምላክነቱን ከካዱ የማን ስጋ የማን ደም ብለው ይቀበሉታል ቢሉ ስመ ቁርባንነቱን ለሚክዱ ሰዎች:: ሐተታ:- ስመ ቁርባንነቱንስ ከካዱ ምን ይረባናል ምን ይጠቅመናል ብለው ይቀበሉታል ቢሉ በግብሩ መካድ አለና::ከሃጥያት ሳይነጹ ቢቀበሉት በፍዳ ላይ ፍዳ የሚያመጣ ስለሆነ እሳት ነበልባሉ ከወረደው ፍህሙ ከመረተው ቀርበው ያለመጠን ቢሞቁት ያቃጥላል ይህም በማይገባ ቢቀበሉት ፍዳ ያመጣልና:: ወይእዜኒ ዘበልዖ ለዝንቱ ህብስት: ወዘሰትዮ ለዝንቱ ጽዋ እንዘ እይደልዎ ደይኖ ወመቅሰፍቶ በልዓ ለርእሱ መንሱትኬ ነሢአ ሥጋሁ በድፍረት ወተመጥዎ ደሙ ዘእንበለ ሃፍረት እንዘቦ ላዕሌሁ ነውረ ሃጥያት እንዲል::ከዚህም ስጋውን ከእሳተ ባቢሎን ደሙን ከማየ ግብጽ ምሳሌ አምጥተው ይናገራሉ: እሳተ ባቢሎን ሰልስቱ ደቂቅን ሳይነካ በአፍአ ያሉ የባቢሎንን ሰዎች አቃጥሎአቸዋል ስጋውም ከሃጥያት ነጽተው የሚቀበሉትን ያድናቸዋል ከሃጥያት ሳይነጹ የሚቀበሉትን ያጠፋቸዋልና ማየ ግብጽ በግብጻውያን ሲለወጥባቸው በእስራኤል አልተለወጠባቸውም ደሙም ከሃጥያት ነጽተው የሚቀበሉትን ያድናቸዋል ከሃጥያት ሳይነጹ የሚቀበሉትን ያጠፋቸዋልና ዛሬም ቀሳውስት ይህን ምሳሌ ይዘው የበደላችሁትን ሳትክሱ የቀማችሁትን ሳትመልሱ ከሃጡያት ሳትነጹ ሳትበቁ ብትቀበሉት ሥጋው ደሙ በነፍስ በስጋ ያስፈርድባችኋል እያሉ አዋጅ ይነግሩበታል::
8:-በአማን እሳት ውዕቱ ዘኢይክሉ ለኪፎቶ እሳታውያን እለ ነደ እሳት እሙንቱ ኪሩቤል ወሱራፌል ከእሳት ከነፋስ የተፈጠሩ ኪሩቤል ሱራፌል ሊይዙት የማይቻላቸው መለኮት የተዋሃደው እውነተኛ ቁርባን ነው ተፈጥሮዋቸው ከእሳት ከነፋስ ነውና:: ወሶበ ኢያእኮትኮ ለዘፈጠርከ እምነፋስ ወነድ ፈጠረ ህየንቴከ ሰንአ ዘማሬ እማይ ወእመሬት እንዲል:: ሐተታ:- ከእለተ ሰሉስ አስቀድሞስ ግብር እም ግብር የተፈጠረ ፍጥረት የለም: የመላእክትም ተፈጥሮ እምሃበ አልቦ ነው: ግብራቸውን ሲያይ እሳት ነፋስ ሃያላን ረቂቃን ፈጣኖች ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው: መላእክትም ሃያላን ረቂቃን ናቸውና: ለተልኮ ይፋጠናሉና: የፈጣሪያቸውን ፈቃድ ይፈጽማሉና::ሐተታ:- እሳት ሰብዓ ሰዶምን ደቂቀ ቆሬን አጥፍቷል ነፋስም ብእሲት ዘማን ጥቅመ ሰናኦርን ሃራ ጰራግሞንን አጥፍቷልና አንድም የባለሟልነት ስማቸው ነው: እገሌ ነደ እሳት ባለሟል ነው እንዲሉ:: ታሪክ:- ዘኢይክሉ ለኪፎቶ አለ ንጉሱ ዖዝያን ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ ይባላል በቀኙ ይቀመጣል: ምነው በቀኜ ትቀመጥብኛለህ ይለዋል ወካህን ይነብር በየማነ ንጉሥ እንጂ ይለኛል ይለዋል:: ከልብሰ መግስቱ ልብሰ ክህነቱ ይበልጣል ምነው ከኔ የበለጠ ልብስ ትለብሳለህ ይለዋል ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ እንጂ ይለኛል ይለዋል:: ፍርዱን ይገስበታል ምነው ፍርዴን ትገስብኛል ይለዋል እምነ መንግስት የአቢ ክህነት እንጂ ይለኛል ይለዋል አድርጎ ቤተ መንግስትም እያረካከሰ ቤተ ክህነትን እያነጋገሰ እየጠቃቀሰ ቢያውከው በዚያም በዚያም ቢሉ ቀንቶበት ከቤተ መንግስትማ ቤተ ክህነት ከበለጠ እኔስ ባባቴ ከቤተ መንግስት ብወለድ በናቴ ከቤተ ክህነት እውለድ የለምን ብሎ ማእጠንተ ወርቁን ይዞ ልብሰ ተክህኖውን ለብሶ ሊያጥን ገባ: ሲያጥን ጢሱ ቢያርፍበት ከግንባሩ ለምጽ ተቀረጸበት በሻሽ ሸፈነው: ከሻሹ ላይ ወጣበት ለምጻሙን በእስራኤል ስንኳንስ በቤተ መቅደስ በከተማ አያኖሩትምና: እሱን አውጥተው ልጁን አንግሰዋል በዘመኑ የነበረ ነቢይ ኢሣያስ ነው ፈርቶ ሳይገስጸው ቢቀር ለምጽ ወቶበት ሃብተ ትንቢት ተነስቶት 3 አመት ከመንፈቅ ያህል ኖሯል ወእምዝ በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉስ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ብሩህ ወነዋህ እንዲል: ዖዚያን በሞተበት ወራት ጌታ በመንበረ ጸባኦት እንዳለ ሆኖ ለኢሳያስ ታየው ያ ታፍረው ታከብረው የነበረው ንጉስ ሞተ አልፈ እኔ ግን እልፈት ውላጤ የለብኝም ሲል ሊያድነው ቢሻ መነ እፌኑ ሃበ ህዝብየ እስራኤል ሁሉ ራሱ ጠበቀ አንገቱን ቀበረ ወደወገኖቼ ወደ እስራኤል በመምህርነት ማንን ልስደድ አለ:: እስመ ማዕከለ ህዝብ ዘርኩስ ከናፍሪሆሙ ሃሎኩ አነ እስራኤል ለምጽ ይጸየፋሉ: ደግሞም ትንቢት ተነስቶብኛል እንጂ እኔ አልፈራም ነበር አለው: ወተፈነወ አሃዱ እምሱራፌል ወነስአ ፍህመ በጉጠት ወአልከፎ ከናፍሪሁ ወይቤ አእተትኩ ለከ ሃጥያተከ እንዲል መልአኩን ከአለመ መላእክት ፍህሙን በጉጠት ወስደህ አጉርሰው አለው:: ሃጥያተከ ቢል ለምጹን አራቅሁልህ ሃጥያትከ ቢል ትንቢቱን መለስኩልህ ሲል ነው::
ከዚህ በኋላ ለምጹ ድኖለት ትንቢቱ ተመልሶለት እንደገና አስተምሯልና: ይህም ምሳሌ ነው መልአኩ የቀሳውስት ጉጠት የስልጣነ እግዚአብሄር እሳያስ የምእመናን ለምጽ የፍዳ የመርገም ፍህም የስጋ ወደሙ :: አንድም ከናፍረ ኢሳያስ የምእመናን መልአኩ የዲያቆን ጉጠት የእርፈ መስቀል ፍህም የደሙ ምሳሌ:: መላእክት ስጋውን ደሙን የሚይዙበት ስልጣን የላቸውምና: ዘኢይክሉ አለ: ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት የሚያሰኘው ቅሉ ይሄ ነው: አባ መቃርዮስ እንዳየው ስለ ንጽህናው መልአኩ የቄሱን እጅ ይዞ ለማርቆስ ዘዮናኒ ግብጻዊ ሲያቀብለው አይቷል::
9:-ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ: ኦ ቃለ አክብሮ ቃለ አህስሮ ቃለ አራህርሆ ይሆናል: ቃል አክብሮ ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ ብሎ የሚያመጣው ነው: ቃለ አራህርሆ ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ቃለ አህስሮ ኦ ሃናንያ ኦ አብዳን ሰብአ ገላትያ ነው:: በእንተዝ ያለፈውን አጠፈ እንደገና ብሎ መጽሃፍ ያለፈውንም የሚመጣውንም ማጠፍ ልማድ ነውና የሚመጣውን አጠፈ እመቤታችን ሆይ እናከብርሻለን እናገንሻለን:: ሐተታ:- እኛ እሷን የምናከብራት የምናገናት ሆነን አይደለም ክብርሽን ገናንነትሽን እንናገራለን ሲል ነው::
እስመ ወልድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ህይወት ዘበአማን:: እውነተኛውን ምግብ እውነተኛውን መጠጥ አስገኝተሽልናልና ስላስገኘሽልን:: ሐተታ:- ዘበአማን አለ ከመስዋዕተ ኦሪት ሲለይ ያ ስጋዊ ይህ መንፈሳዊ ያ አፍአዊ ይህ ውሳጣዊ ያ ምድራዊ ይህ ሰማያዊ ነውና:: አንድም የዚህ አለም ምግብ ጥዋት በልቶ ለማታ ማታ በልቶ ለጠዋት ያሻል ይህ ግን በሚገባ ከተቀበሉት በሃጥያት ካላሳደፉት ህማሙን ሞቱን ለማዘከር ነው እንጂአንድ ግዜ ከተቀበሉት በሌላ ግዜ አያሻምና:: አንድም የዚህ አለም ምግብ ሃሰር ይሆንል ይለወጥል በሱ ግን ይህ ሁሉ የለበትምና አንድም የዚህ አለም ምግብ ሞትን ያስከትላል ይህ ግን የዘላለም ህይወት ይሆናል አንድም ከማናዊት እመቤታችን ስለተገኘ መብልአ ጽድቅ ዘበአማን ውስቴ ህይወት ዘበአማን አለ:: ይቆየን .......ቸር ያቆየን!!!!!!

Friday, August 6, 2010

ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 1

1:- አኮቴተ ቁርባን ዘእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘደርሰ በመንፈስቅዱስ አባ ሕርያቆስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሃገረ ብህንሳ ጸሎታ ወበረከታ የሃሉ ምስለ ኩሎሙ ህዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን ::
ሕርያቆስ ማለት ህሩይ ማለት ነው : ለሹመት መርጠውታልና: አንድም ረቂቅ ማለት ነው ምሥጢረ ሥላሴን ይናገራልና : ከሊቃውንትስ ምሥጢረ ሥልሴን የማይናገር የለም ብሎ ከሁሉ ይልቅ እሱ አምልቶ አስፍቶ አጉልቶ ይናገራልና አንድም ፀሐይ ማለት ነው: አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስቅዱስ ፀሐይ ብሎ ጽፏልና : አንድም ብርሃን ማለት ነው: የምዕመናንን ልቦና በትምህርቱ ብሩህ ያደርጋልና : ዘአብርሃ መንበረ ማርቆስ በብርሃን እንዲል :አንድም ንብ ማለት ነው: ንብ የማይቀምሰው አበባ የለመ እሱም የማይጠቅሰው ሊቅ የለም:ይህም እንደምን ነው ቢሉ:ሐዋርያት የተማረ ግብረ ገብ ይሾም ብለው ሥራት ሰርተዋል: ይህስ አይደለም ሁለቱን አስተባብሮ የያዘ አይገኝም ብሎ የተማረ ከሆነ ይሾም ብለዋል::በትምህርቱ መናፍቃንን ተከራክሮ ይመልሳልና ብለው ግብረ ገብም ከሆነ ይሾም ብለዋል:በጸሎቱ ይጠብቃል: በትሩፋቱ ያጸድቃል:ትምህርቱን ውሎ አድሮ ያደርገዋልና ብለው ሾሙት :ይህም አባ ህርያቆስ ያልተማረ ግብረ ገብ ነው :ቢማርም ለጸሎት ለቅዳሴ ያህል ነበር:በብህንሳ በ10000 መነኮሳት በ10000 መነኮሳይያት ተሹሟል በብዙም መሾም ልማድ ነው::
አባ ሆርና አባ ኤስድሮስ በ1000 አባ አሞን በ3000 አባ ጳኩሚስ በ6000 አባ ሰራብዮን በ10000 ተሾሙ:ይህችም ብህንሳ ቅድመ ትሰይም አርጋድያ ወድህረ መኑፍ ይላል: ብዙ ግዜ ስመ ተፋልሶ አግኝቷታል :በፊት አርጋድያ ኋላም መኑፍ ተብላለች ዛሬም ብህንሳ ትባላለች:ሴትና ወንድ ያልተለየባት ገዳም ናት:እንደ ዘጌ እንደ ቆራጣ እንደ ቀንጠፋሜ እርሱም ግብረ ገብ ነውና ሥራት ቢያጸናባቸው ይጣሉታል:ያልተማረ ነውና ይንቁታል: ከመጠምጠም መማር ይቅደም እንዲሉ ከመሾም መማር አይቀድምምን እያሉ; እሱ ግን ወእቀውም ዮም በትህትና ወበፍቅር ብሎ እንዲያመጣው: እንደጠሉኝ ልጥላቸው እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር እና በትህትና ጸንቶ ያስተምራቸው ነበር::
ከዕለታት ባንዳቸው በምን ምክንያት እንሻረው አሉ:ቀድሰህ አቁርበን ብለን በዚህ ምክንያት እንሻረው ብለው መክረው ቀድሰህ አቁርበን አሉት: የሱ ግን ተምኔቱ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤቴ ምስጋና እንደባህር አሸዋ እንደ ሰማይ ኮከብ በዝቶልኝ እንደምግብ ተመግበው እንደ መጠጥ ጠጥቼው እንደ ልብስ ለብሼው እያለ ይመኝ ነበር:ቅዳሴ ገብቶ ሥርዓቱን ጨርሶ ከፍሬ ቅዳሴው ሲደርስ ከሊቃውንት ቅዳሴ የሚያስቸግር የማንን እናውጣለት እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ የለመኗትን የማትነሳ የነገሯትን የማትረሳ እመቤት ገልጻለት ጐሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ ብሎ ወይእዜኒ ንሰብሐ እስኪል ድረስ ሰተት አድርጎ ተናግሮታል: የሚንቁት የሚጠሉት ይህ የነገሩትን ቀለም እንኳን አከናውኖ መናገር የማይችል ዛሬስ እንግዳ ድርሰት እደርሳለው ብሎ አገኝ አጣውን የቆጥ የባጡን ይቀባጥራል: ብለው አደነቁበት የሚወዱት የሚያከብሩት ከመንፈስቅዱስ ነው እንጂ እንዲ ያለ ምሥጢር ከእሩቅ ብዕሲ ይገኛልን ብለው አደነቁለት: ወዲያው የሚወዱት የሚያከብሩት ጽፈን ደጉሰን አንይዘውምን አሉ: የሚንቁት የሚጠሉት ደግሞ ማን ተናገረው ብለን እንይዘዋለን አሉ እንደ ሊማዱ አድርገን አንይዘውም አሉ:: ለሃገራቸው እንግዳ ድርሰት የተደረሰ እንደሆነ ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ይጥሉታል: ከእሳት ደህና የወጣ እንደሆነ ከውሃ ይጥሉታል ከውሃ የወጣ እንደሆነ ከህሙም ላይ ይጥሉታል ድውይ የፈወሰ እንደሆነ ደገኛ ድርሰት ነው ብለው ይይዙታል::
ይህንንም ቅዳሴ ማርያም ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ላይ ጣሉት ከእሳት ደህና ወጣ: ከውሃ ጣሉት ከውሃ ደህና ወጣ: ከህሙም ላይ ጣሉት ድውይ ፈወሰ: ይልቁንም ሙት አስነስቷል:: ደገኛ ድርሰት ነው ብለው ጽፈው ደጉሰው ይዘውታል:በጥራዝም 14ኛ አድርገው ጠርዘውታል: ከ14ቱ ቅዳሴም ተአምራት ያልተደረገበት የለም: የቀደሰበት ምን ቀን ነው ቢሉ: ከእመቤታችን ከ 33ቱ በዓላት ባንዱ ቀን ነው: አንድ ባህታዊ ከባለሟልነት የተነሳ ከ33ቱ በዓላት ማንን ትወጃለሽ ብሎ እመቤታችንን ጠየቃት:ኪዳነምህረትን ልደታን አስተርአዮን ፍልሰታን አለችው: ከሊህ ከ4ቱስ ማንን ትወጃለሽ ቢላት ከጸባብ ወደ ሰፊ: ከጨለማ ወደ ብርሃን: የወጣውበት ነውና ልደቴን እወዳለው አለችው: ቀድሞ እነ ሳልወለድ እናትና አባቴን መባችሁን አንቀበልም ብለው አዝነው ተክዘው ነበር: የነሱ ሃዘን ሃዘኔ ነውና እነን ከወለዱ በኋላ መባቸውን ተቀብለዋቸው ደስ ብሎዋቸዋል: የነሱ ደስታ ደስታዬ ነውና እንዳለችው የልደታ እለት ነው የቀደሰው:: እሱስ ማንን ሊቀድስ ኖሯል ቢሉ ከቅዳሴ ሐዋርያት ሌላ አያቅም ነበርና ቅዳሴ ሐዋርያትን: ይህስ አይደለም ለእመቤታችን ቅዳሴ ሐዋርያት ምኗ ነው: ምን ቢቸግር ተበድሮ ጋሬዳ እንዲሉ ቅዳሴ እግዚእን ሊቀድስ ነበር ስሟን ባያነሳ እምድንግል ተወሊዶ ከመ ፈቃድከ ይፈጽም ብሎ በምሥጢር ያነሳታል::
ከባህር ወዲህስ ማን አምጥቶልናል ቢሉቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ መደባይ ታብር በሚባል ቦታ ይኖር ነበር እመቤታችን ቅዱስ ኤፍሬምን ከሶርያ አባ ሕርያቆስን ከብህንሳ በደመና ጠቅሳ ያረድ ካለበት አድርሳ አንተ ውዳሴየን አንተ ቅዳሴየን ነግራችሁት በዜማ ያድርስ ብላቸው እነሱም ነግረውት በዜማ አድርሶታል:: ከዚሁ አያይዞ 13ቱንም ቅዳሴ በዜማ ደርሷል: ይህም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል::ከተከዜስ ወዲህ ማን አምጥቶልናል ቢሉ ሳሙኤል ትውልደ ጌዴዎን ዘገበዘ አክሱም ይለዋል እሱ አምጥቶልናል እሱም ይሄን እየደገመ ሲሄድ ክንድ ከስንዝር ከመረት መጥቆ ይሄድ ነበር: ከዕለታትም በአንዳቸው ውሃውን ቢባርከው ህብስት ሆኖለት ተመግቦ ምዕመናንን መግቧቸዋል:: እመቤታችንም የፍቅር ምልክት ሁለት ንዋያት ሰታዋለች ነጭ እጣን እና እንቁ ነው: ከዛም አያይዛ ውዳሴየን ከቅዳሴዬ ጋራ አንድ አድርጎ የሚደግመውን ሰው አንተ ከገባህበት ውሳጤ መንጦላዕት አገባዋለው:ብላ ተስፋውን ነግራዋለች:: ይሀውም ሊታወቅ ዛሬ በዋልድባ ያጠና በቃሉ: ያላጠና በመጽሃፍ ቅዳሴ ማርያም ሳይደግም የሚውል የለም:ይህም ተስፋ ውዳሴዋን ከቅዳሴዋ ጋር አንድ አድርጎ ለምደግም ሰው ሁሉ ነው:እንጂ ለሱ ብቻ አይደለም:ዳንድ ባህታዊ ከምስጋናሽ ሁሉ ማንን ትወጃለሽ ብሎ ቢጠይቃት ልጄ ዳዊትን አቡነ ዘበሰማያትን ቢደግሙለት እንዲወድ እኔም ውዳሴዬን ቅዳሴዬን ቢደግሙልኝ ወዳለው ብላዋለች ::
አባ ሕርያቆስ ተሹሞ ሳለ ብዙ ድርሳንን ደርሷል ብዙ ተግሳጽ ጽፏል ከብዙውም አንዱ ይህ ቅዳሴ ነው እረፍቱ በጥቅምት 2 ነው::
ልመናዋ ክብሯ በኛ ይደርብንና ህብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርጎ አክብሮ ለውጦ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ደመ ወለደ እግዚአብሔር በሚያደርግበት ግዜ በብህንሳ ኤጲስ ቆጶስ የተሾመ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት እመቤታችንን ያመሰገነበት ምስጋና ይህ ነው:: ቁርባን ቀሳውስት ሥጋውን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርገው ወደ መንበር የሚያቀርቡበት አኰተት የሚለውጡት የሚያከብሩት አንድም በክብር በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ አንድም ቁርባን የሚቀበሉት የሚያቀብሉት አኰተት የሚለውጡት የሚያከብሩት ልመናው ክብሩ በኛ ይደርብንና በብህንሳ ኤጲስ ቆጶስ የተሾመ አባ ሕርያቆስ በመንፈስቅዱስ ተገልጾለት የተናገረው ቅዳሴ ይህ ነው: ጸሎታ ወበረከታ ቢል ተመስጋኝቱን ሲያይ: ክብሯ ልመናዋ ይደርብንና ጸሎቱ ወበረከቱ ቢል አመስጋኙን ሲያይ ነው::
2:- ይ:ካ: እግዚአብሔር ምስለ ኰልክሙ ቄሱ:-እግዚአብሄር በሁላችሁም አድሮባችሁ ይኑር ይበል::
ይ:ሕ: ምስለ መንፈስከ ህዝቡም እንደቃልህ ይደረግልን ይበሉ::
ይ:ካ: አእኩትዎ ለአምላክነ :-ቄሱ ፈጣርያችንን አመስግኑት ይበል
ይ:ሕ: ርቱዕ ይደሉ :- ህዝቡም ዕውነት ነው ይገባል ይበሉ
ይ:ካ: ብነ ሃበ እግዚአብሔር አምላክነ
ህዝቡም በፈጣርያችን በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋ አለን ይበሉ::
3:- መጽሃፍ ከመጽሃፍ ማያያዝ ልማድ ነው: አባቷ ዳዊት ለንጉሰ ሰማይ ወምድር ምስጋና ላቅርብ ባለ ግዜ ጐሥዐ ብሎ ተናግሮ ነበርና እሱም ለንግስተ ሰማይ ወምድር ምስጋና ላቅርብ ባለ ግዜ ጐሥዐ አለ አንድም ለአባቷ ለዳዊት የገለጸ መንፈስቅዱስ ምሥጢር ከምስጢር አያይዞለት ጐሥዐ አለ ወአየድዕ ይላል በልብ መደብ ቁሞ ወአነ አየድዕ ይላል በቃለ መደብ ቁሞ ልቦናዬ በጎ ነገርን አውጥቶ ተናገረ::አንድም ልቦናየ ስንቡል መንፈስቅዱስን ተቀብሎ በጎ ነገርን ገሳ ሐተታ:-በሃገራቸው የተመገቡት ምግብ ያልተስማማቸው እንደሆነ ዑድ ሰንደል የሚባል ሽቱ አለ ያንን ተመግበው በጎ በጎ ነገር ገሣው ይላሉና ያጎሥዓኒ እንዲል ትግሬ ሐተታ:- ሶስት ግዜ ጐሥዐ ጐሥዐ ጐሥዐ ብሎ መላልሶ ተናገረ ስለምን ቢሉ በንጽሃ ስጋ በንጽሃ ነፍስ በንጽሃ ልቦና መዓረግ አምሳል አንድም ወጣንያን ማዕከላውያንን ፍጹማን የሚያመሰግኗት ስለሆነ: አንድም በዚህ አለም በገነት በመንግስሠማያት ያሉ ጻድቃንየሚያመሰግኗት ስለሆነ: ከዚህስ አስቀድሞ መንግስተ ሰማይ የገባ የለም ብሎ ኋላ መንግስተ ሰማያት የሚገቡ ጻድቃን የሚያመሰግኗት ሲለሆነ: አንድም ሊቃውንት በሚስጥረ ሥላሴ መጀመር ልማዳቸው ነው: ሦስት ግዜ ደጋግሞ መናገሩ የሦስትነት: ቃሉ አለመለወጡ የአንድነት:ምሳሌ ነው:አንድም ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ የሚል ነውና ሦስት አርዕስት ተናገረ ለሦስቱም ያመጣል::
4:-ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ለማርያም:- አባቷ ዳዊት ወአነ አየድዕ ግብርየ ለንጉሥ ብሎ ነበርና ለዚያ ዋዌ እኔም የእመቤታችንን ምስጋና እናገራለው አለ ሐተታ:- መጀመርያ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ አለ በቅድስና ወበንጽህና ስርጉት አንቲ የሚል ነውና ለዚያ አርዕስት ነው::
አኮ በአብዝኖ በማብዛት አይደለም : አላ በአውህዶ በማሳነስ ነው እንጂ ሐተታ:-የእመቤታችን ምስጋና ከምስጋና ቢበዛ እንጂ ያንሳልን? መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን አይደለችምን ቢሉ እውነት ነው የእመቤታችን ምስጋና ሰማይና ምድር ብራና አብህርት ቀለም ዕጽው ብርዕ አዕባን መድመድ: መላዕክት ደቂቀ አዳም ጸሃፍት ቢሆኑ ባልተፈጸመም ነበር:እንደቅድስናዋ እንደንጽህናዋ አይደለም ሲል እንዲህ አለ ከዚያ ሁሉ ቅዱስ ቄርሎስ የቴዎዶስዮስን እህቶች የአርቃድያ የመሪናን ምስጋናቸውን ተናግሮ ዝውዳሴንዘተናገርነ ይውህደ እምክብርክን እንዳለ አንድም ንባብን በማብዛት ምሥጢሩን በማሳነስ አይደለም: ንባቡን በማሳነስ ምሥጢሩን በማብዛት ነው እንጂ::
ወአነ አይድዕ ውዳሴሃ ለድንግል:- እኔም የእመቤታችንን ምስጋና እናገራለው ሐተታ:-ሁለተኛ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ድንግል አኮ ስፋጣን ዘናዘዙኪ አላ መላእክተ ሰማይ ሐወጹኪ በከመ ተብህለ ካህናት ወሊቃነ ካህናት ወደሱኪ የሚል ነውና::
አኮ በአንሆ በቃለ ዝንጋዔ:- ዝንጋዔን የሚያመጣ ዝንጋዔን የሚያስከትል ነገርን በማብዛት አይደለም: ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ: ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ:እንዲሉ ነገር ከበዛ ዘንድ ከምን ተነስቶ ከዚህ ደረሰ ይባላልና ነው::
አላ በአሕፅሮ:-በማሳጠር በመጠቅለል ነው እንጂ ሲሰበር ይሰንጠር ሲረዝም ይጠር እንዲሉ:
ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ ለድንግል:- የድንልን ገናንነቷን እናገራለው ሐተታ:- ሦስተኛ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ማርያም ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ብሎ የሚያመጣ ነውና: ይህስ አይደለም አርዕስት ተቀዳደመ ለፊተኛው አርቆ ለኋለኛው አቅርቦ አይሰጥም ብሎ መጽአ ሃቤኪ ቃል ብሎ የሚያመጣ ነውና:: ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ : ወአነ አይድዕ ቅዳሴሃ : ወአነ አይድዕ ዕበያቲሃ ብሎ ሦስት ጊዜ መላልዞ ተናገረ::
ኦ ማርያም በእንትዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ኦ ድንግል ምልዕተ ውዳሴ: ኦ ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሃተ የሚል ነውና: አንድም አባቷ ዳዊት ቀደሰ ማህደሮ ልዕል:መሰረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን እስመ ሓረያ እግዚአብሄር ለጽዮን ብሎ ሦስት ግዜ መላልሶ አመስግኗታል:: ይቆየን የዚህ ክፍል ሁለት ነገ ይቀጥላል ..............ችቸር ያቆየን!!!!!

ውዳሴ ማርያም አንድምታ ዘቀዳም :- ክፍል 1

ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት
በክብር ትቀድማለችና:: አንድም በዕለተ ሰንበት አይሁድ የሚል አብነት ይገኛል አይሁድ በብሉይ የሚያከብሯት ሲል ነው :: በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች :: የብርሃን ድባብ ይዘረጋል የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል :: ከዚያ ላይ ሁና ሰላም ለከ ኦፍቁርየ ኤፍሬም ትለዋለች :: እርሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል:: ወድሰኒ ትለዋለች ክርክር አልቋልና :: ባርክኒ ይላታል :: በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስቅዱስ ይህድር በላዕሌከ ትለዋለች :: ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል ::ውዳሴ ዘቀዳሚት ዉዳሴ በቀዳሚት ዉዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ይላል ቃለ ጸሐፊ ነው :: እርሱ ግን ንጽህት ወብርህት ብሎ ይጀምራል ::
" ንጽህት ወብርህት"
ንጽህት ነሽ ብርህት ነሽ ::
" ወቅድስት በኩሉ::"
በአፍኣ በውስጥ ንጽህት ነሽ : እርሷ የምትለወጥ ሁና አይደለም : እርሱ እየቀደመ እየበቃ ማየቱን መናገር ነው ::
" እንተ ሐቀፈቶ ለእግዚእ በእራሃ :"
ጌታን በማሃል እጅሽ የያዝሺው : ህጻናትን አናት ይወርድላቸዋልና ብለው በማሃል እጃቸው እንዲይዟቸው :: አንድም በክንድሽ የያዝሽው ::
" ወኩሉ ፍጥረት ይትፌሥሑ ምስሌሃ "
ፍጥረት ሁሉ ካንቺ ጋር እንዳንቺ ደስ ይላቸዋል :: እንዘ ይጸርሁ ወይበሉ
" ሰአሊ ለነ ቅድስት "
እያሉ አንድም ተፈስሒ ኦ ምልዕተ ጸጋ ::ምልዕተ ክብር ሆይ ( ተፈሥሒ) ደስ ይበልሽ እያሉ ::
" ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገር ተፈሥሒ እግዚአብሔር ምስሌኪ :"
እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነስቶ ካንቺ ጋር አንድ ባህርይ ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ( ተፈሥሒ) ደስ ይበልሽ ::
" ናስተበፅዕ ዕበየኪ ኦ ግርምት ድንግል "
ግርምት ድንግል ክብርሺን ገናንነትሽን ዕፁብ ዕፁብ እያልን እናመሰግናለን :: ግርምትነትቷ በአይሁድ በመናፍቃን በአጋንንት ዘንድ ነው ::
" ወንፌኑ ለኪ ፍሥሐ ምስለ ገብርኤል መልአክ :"
ከመልአኩ ጋራ እንደ መልአኩ ምስጋና እናቀርባለን :: ምስጋናውን ፍስሐ አለው : ተፈሥሒ ተፈሥሒ እያለ ነውና ::
" እስመ እምፍሬ ከርሥኪ ኮነ መድሃኒተ ዘመድነ :"
ከማህፀንሽ ፍሬ የባህሪያችን ድህነት ተገኝቷልና አንድም የማህፀንሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ የባህሪያችን ድህነት ሆኗልና ::
" ወአቅረበነ ሃበ እግዚአብሔር አቡሁ :"
ከአባቱ ጋራ አስታረቀን " ሰአሊ ለነ ቅድስት "
ካባቱ ጋራ ካስታረቀን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን ::
" ከመ ከብካብ ዘአልቦ ጥልቀት :"
እንደ ሰርግ ቤት አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ሆነሽ ቢያገኝሽ :
" መንፈስቅዱስ ሃደረ ላዕሌኪ "
መንፈስቅዱስ አድሮብሻልና :
" ወሃይለ ልዑል ጸለለኪ:"
ሃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ለብሷልና አንድም መንፈስቅዱስ ከሦስቱ ግብራት ከልክሎሻልና ሃይለ ልዑል ወልድም ከሦስቱ ግብራት ከልሎሻልና
" ኦ ማርያም አማን ወለድኪ ቃለ ወልድ አብ ዘይነብር ለዓለም :"
ለዘላለም ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃልን ወለድሽልን :
"መጽአ ወአድሃነነ እምሃጢያት:"
ሰው ሆኖ ከሃጢያት አዳነን አንድም ከሃጥያታችን ፍዳ ያዳነን " ሰአሊ ለነ ቅድስት "
ሰው ሆኖ ከሃጥያታችን ፍዳ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን ::
" አንቲ ውእቱ ዘመድ ዘእምሥርወ ዳዊት:"
ከዳዊት ሥርው የተገኘሽ ባህርይ አንቺ ነሽ :ሥር ወደላይም ወደታችም ያድጋል ወደላይ ቢሉ ዕሴይ ወደታች ቢሉ ኢያቄም መገናኛው ዳዊት ::
" ወለድኪ ለነ በሥጋ መድሃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ :"
መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ወልደሽዋልና :
" ዋህድ ቃል ዘእምአብ ዘእምቅድመ ዓለም ህልው :"
ቅድመ ዓለም የነበረ ከአብ ባህርይ ዘእምባህርይ አካል ዘእምአካል የተወለደ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል :
" ሃብአ ርእሶ :"
ባህርዩን በስጋ ቢሰውር:
" ወነስአ እምኔኪ አርኣያ ገብር :"
ከአንቺ አርአያ ገብርን ቢነሳ መድሃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልደሽልናልና : አንድም ቅድመ ዓለም ህቡዕ የሚሆን አካላዊ ቃል ህብዓ ርእሶ ባህርዩን በስጋ ሠወረ :ካንቺም ሃየሰ ወረሰ ከብረ ተለዓለ ነገሠ መባልን ገንዘብ አደረገ : " ሰአሊ ለነ ቅድስት "
ሃየሰ ወረሰ ከብረ ተለዓለ ነገሰ ከሚባል ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን ::
" ኮንኪ ዳግሚተ ሰማይ ዲበ ምድር :"
ከምድር በላይ ያለሽ ሁለተኛ ሰማይ አንቺ ነሽ : አንድም ከምድር በላይ ያለች የጠፈር ባልንጀራ ሆንሽ :
" ኦወላዲተ አምላክ ዘእንበለ ርኩስ:ሠረቀ ለነ እምኔኪ ፀሐየ ጽድቅ:ዘእንበለ ዘርዕ ወኢሙስና : ሰአሊ ለነ ቅድስት :"
አደፍ ጉድፍ ሳይኖርብሽ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ፀሐየ ጽድቅ ጌታ ካንቺ ተወልዷልና ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው እንደተናገሩ : ዘር ምክንያት ሳይሆንሽ መለወጥ ሳያገኝሽ ወልደሽዋልና : ዘር ምክንያት ሳይሆንሽ ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን ::
"አንቲ ውእቱ ደብተራ እንተ ተሰመይኪ ቅድስተ ቅዱሳን:ወውስቴታ ጽላተ ኪዳን:መሶበ ወርቅ እንተ መና ህቡዕ:ዘውእቱ ወልደ እግዚአብሔር መጽአ ወሃደረ ሃበ ማርያም ድንግል "
ከተለዩ የተለየሽ ከከበሩ የከበርሽ ደብተራ አንቺ ነሽ :ሕግ የተጻፈበት ኪዳን ያለብሽ: መና ያለበት መሶበ ወርቅ ያለብሽ:ይህውም ሰው ሆኖ በማህጸንሽ ያደረው ወልደ እግዚአብሔር ነው : ደብተራ የእመቤታችን ምሳሌ ቅድስት የነፍሷ ምሳሌ ቅዱሳን የ4ቱ ባህርያት ምሳሌ ታቦት የመንፈስቅዱስ ጽላት የልቦናዋ ቃሉ በመንፈስቅዱስ የተገለጸላት ምሥጢር :: አንድም ቅዱሳን የሥጋዋና የነፍሷን : ቅድስት የልቦናዋ : ታቦት የማህጸኗ ጽላት : የትስብእት ቃሉ የመለኮት ምስሌ :
" ተሰብአ እምኔሃ ቃለ አብ : ወወለደቶ ውስተ ዓለም ለንጉሠ ስብሐት : መጽአ ወአድሃነነ :ትትፌሣህ ገነት እመ በግዕ ነባቢ :"
አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆነ :የክብር ባለቤት እርሱን በዚህ ዓለም ወለደችው : ሰው ሆኖ ያዳነን : የነባቢ በግዕ እናቱ ደስ ይላታል ኢነባብያን አባግዕ አሉና ከዚያ ሲለይ በግዕ ነባቢ አለ : አንድም 7ቱን አጽራሐ መስቀል የተናገረውን ሲል በግዕ ነባቢ አለ :
" ወልደ አብ ዘይነብር ለዓለም : መጽአ ወአድሃነነ እምሃጥያት : ሰአሊ ለነ ቅድስት :"
ለዘላለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃል ሰው ሆኖ ከሃጥያት ያዳነን አንድም ከሃጥያታችን ፍዳ ያዳነን :ሰው ሆኖ ከሃጥያታችን ፍዳ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን:: ይቆየን የቅዳሜን ክፍል 2 በሚቀጥለው ሳምንት እንመለስበታለን.............ቸር ያቆየን !!!!!

Tuesday, May 18, 2010

ቅዱስ ያሬድ

በግንቦት 11 ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ አረፈ::ይህ ቅዱስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነጹት አብያተ ክርስቲያናት ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው: እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተከበበ እና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት ::
የዚህ ቅዱስ አባት አዳም የእናቱም ስም ታውክሊያ ሲባሉ :በ512 ዓ ም በአክሱም ከተማ ተወለደ:: እናት እና አባቱም ልጃቸውን ለማስተማር ወደ ዘመዳቸው አባ ጌዴዎን ልከው እንዲማር አደረጉት : ይህም አባት አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊያስተምረው በጀመረ ግዜ መቀበልም ማጥናትም ተሳነው እስከ ብዙ ዘመንም መዝሙረ ዳዊትን ሲማር ኖረ ነገር ግን ከልቡ ማጥናትን እምቢ አለው:መምህሩም አብዝቶ ደበደበው ባሳመመውም ግዜ መታገስ ተሳነው ከአባቶቹ ቤትም ወቶ ዕብነ ሃኪም ወደተቀበረበት ገዳም ሄደ : በውስጡም የወርቅ የብር የልብስ መቀመጫዎች የተመሉ ናቸው: ከአንዲትም ዛፍ አጠገብ ደረሰ ከዚያም አረፈ ትልም ወደ ዛፏ ሲወጣ አየ :ወደ ዛፊቱም እኩሌታ ደርሶ ወደ ምድር ይወድቃል :ሁለተኛም ተመልሶ ወደ ላይ ይወጣል መጀመርያ ወደ ደረሰበት ሲደርስ ይወድቃል:ሲወጣ ሲወድቅ ብዙ ግዜ ያደርጋል : ወደ ሌላ ቦታም አይሄድም
ከዚህም በኋላ በብዙ ጥረት በብዙ ትጋት በብዙ ድካም በዚያ ከዛፏ ላይ ወጣ:ከዚያችም ከዛፏ ላይ ተቀምጦ በላ :ቅዱስ ያሬድም ወደዚያ ዛፍ ላይ ይወጣ ዘንድ እንደሚተጋ ብዙ ግዜም ከላይ ሳይደርስ ከመካከል እንደሚወድቅ ከዚያም በኋላ በጭንቅ ወደ አሰበው እንደደረሰ የፈለገውንም እንዳገኘ የትሉን ትጋት ባየ ግዜ ሰውነቱን ግርፋቱን እንደምን አትታገሺም ህማሙንስ እንደምን አትችይም አላት መታገስንስ አብዝተሽ ኖሮ ቢሆን እግዚአብሄር በገለጠልሽ ነበር ይንንም ብሎ አለቀሰ ወደ መምህሩ ወደ ጌዲዮን ተመለሰ አባት ሆይ ይቅር በለን እንደቀድሞ ንገረኝ አስተምረኝም አለው:መምህሩ ጌዲዮንም እንዳልከው ይሁን አለው 150ውን መዝሙረ ዳዊት:መሃልየ ነብያትን :መሃልየ መሃልይን :የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ምስጋና ነገረው:81ዱ መጻህፍትን ትርጓሜ የሌሎች መጽሃፍትን ቁትር እና የመሳሰሉትን መጽሃፍተ ሊቃውንት ሁሉ በአንድ ቀን አጥንቶ ፈጸመ::
ከዚህ በኋላ በብዙ ለቅሶ ወደ እግዚአብሄር በለመነ ግዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ግዜ የብሉይ እና የሃዲስ መጽሃፍትን ተምሮ ፈጸመና ዲቁና ተሾመ:በዚያም ወራት እንደዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማህሌት የለም ነበር በትሁት እንጂ :: እግዚአብሄርም መታሰቢያ ሊያቆምለት በወደደ ግዜ ከኤዶም ገነት 3 አእዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ እየሩሳሌም ሰማያዊት ከእነሱ ጋር አወጡት በዚያም 24ቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማህሌት ተማረ::
ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ግዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በ3 ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ:ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ :የፅዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም እንዴት እንደሚሰራት የድንኳንን አሰራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ:: ይህቺም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት:የቃሉንም ድምጽ በሰሙ ግዜ ንጉሱም ንግስቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋር የመንግስት ታላላቆች እና ህዝቡ ሁሉ ወደ እርሱ ሮጡ:ሲሰሙትም ዋሉ ከዚህም በኋላ ከአመት እስከ አመት በየክፍለ ዘመኑ በክረምት እና በበጋ:በመጸው እና በጸደይ:በአጽዋማት እና በባእላት :በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በአል በነብያት እና በሃዋርያት በጻድቃን እና በሰማእታት በደናግልም በአል የሚሆን አድርጎ በሶስቱ ዜማው ሰራ :ይህውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው::
የሰው ንግግር የአእዋፍ የእንሥሳትና የአራዊት ጩሀት ከነዚህ ከሶስቱ ዜማ አይወጣም :በአንዲት እለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉስ ገበረመስቀል እግር በታች ቆሞ ሲዘምር ንጉሱም የያሬድን ድምጽ እያዳመጠ ልቡ ተመስጦ የብረት ዘንጉን ወይም መቋምያውን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውሃ ፈሰሰ ያሬድም መሃሌቱን እስከሚፈጽም አልተሰማውም ነበር ንጉሱም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለከውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው ንጉስም በማለለት ግዜ ወደ ገዳም ሄጄ እመነኩስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሱም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋር እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሃላውን አሰበ እያዘነም አሰናበተው ከዚ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ በተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበርሽ እና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍ ያልሽ የብርሃን መውጫ የህይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና (አንቀጸ ብርሃን) እስከመጨረሻ በተናገረ ግዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ::
ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን ሃገር ሄዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ስጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ እግዚአብሄር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚ በኋላ ግንቦት 11 ቀን በሰሜን ተራራ አሁን ቅዱስ ያሬድ ገዳም ባለበት ቦታ ተሰወረ :የአባታችን የአምሳለ ሱራፌል የሊቁ ማህሌታይ የቅዱስ ያሬድ ጸሎቱ በረከቱ ረድኤቱ በኛ በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ በሃገራችን በኢትዮጵያ ላይ ለዘላለም በእውነት ይደርብን !!!!!አሜን..........................ቸር ያቆየን!

Saturday, May 15, 2010

የበረሃ አባቶች መልዕክት (ከገዳም የመጣ መልዕክት)

1:- ይድረስ ለኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች:-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን:
በእግዚአብሄር ቸርነት: በእመቤታችን አማላጅነት: በመላእክት ተራዳይነት: በቅዱሳን ፀሎት: እስከዛሬ በህይወት ሳንጥፋ ላቆየን አምላክ ምስጋና ይግባውና ቀሪ ህይወታችንንም በሰላም በጤና በፍቅር ያቆየን ዘንድ የቸሩ ፈጣርያችን ቸርነት አይለየን እያልኩ ይህችን አጭር እና አብይ መልዕክት አስተላልፋለው እና እግዚአብሄር ቢፈቅድ ሁላችንም በአንድ ላይ ሆነን ለራሳችንም ፍጹም ሰላምን አግኝተን ለሌላው እንድንተርፍ እና ለሃገራችንም እግዚአብሄር ፍጹም ምህረቱን እንዲያወርድልን መንግስተ ሰማያትንም እንዲያወርሰን ሁላችንም ንስሃ እንግባ እላለው!!!!!!!
ንሰሃ ማለት:- ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ ማለት ነው:
ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ ማለት ከሃጥያት ርቆ የእግዚአብሄርን መንገድ ተከትሎ መሄድ ሲሆን: ንስሃ ለመግባት ደግሞ ከልጅነት እስከ እውቀት የሰራነውን ሃጥያት ወደ ካህናት ቀርበን ራሳችንን ገልጸን አንድም ሳናስቀር የበደልነውን ተናዘን ቀኖናችንን መውሰድ ነው:ከዛም የዕለት ኑሮዋችንን እግዚአብሄርን በማስቀደም ማከናወን የሚገባንን ማከናወን ነው::!!!!!!!
2:- ይድረስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ማህበሮች እና የጽዋ ማህበሮች:-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን:
በእግዚአብሄር ቸርነት: በእመቤታችን አማላጅነት: በመላእክት ተራዳይነት: በቅዱሳን ፀሎት:የቤተ ክርስቲያናችን ማህበራት ዛሬ ላይ ደርሳቹ ለምዕመኑ የሃይሞኖትን ፍቅርን እና ጣዕምን እንዲያድርበት አልፎም ቤተ ክርስቲያኖቻችንን እንዲረዱ እንድታደርጉ ለረዳቹ እግዚአብሄር ምስጋና ይሁንና: የበለጠ ደግሞ እግዚአብሄር ፈቅዶ ምዕመኑን ንሰሃ እንዲገባ የበለጠ የእለት የእለት መልዕክታቹ እንዲሆን በእግዚአብሄር ስም እጠይቃለው: ሲጀመርም የመንፈሳዊ ማህበራት የመጀመሪያ አላማ ሰዉን ንሰሃ አስገብቶ በሃይማኖት አጽንቶ ፍጻሜ እንዲያምር ሲሆን ከዛ በመቀጠል ይሆናል እንግዲ ሌላው ሌላው መልእክት መተላለፍ ያለበት እና ሁላችንም ንሰሃ ገብተን እግዚአብሄርን ለመለመን ይርዳን !!!!!!!
3:- ይድረስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወንጌል ሰባክያን እና ዘማርያን:-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን:
በእግዚአብሄር ቸርነት: በእመቤታችን አማላጅነት: በመላእክት ተራዳይነት: በቅዱሳን ፀሎት:የሃዋርያትን:የ72 አርድእትን የተለያዩ የቀደሙ ቅዱሳን አባቶችን ፈለግ ተከትላቹ ለምእመኑ የክርስቶስን ወንጌል እንድትሰብኩ እና ሰዉ በሙሉ ስለ አማናዊው ክርስቶስ እንዲያውቅ እንድታስተምሩ ለረዳችሁ ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁንና: የትኛውም ሰባኪያን ወይም መዘምራን የመጀመርያው አላማው ቤተክርስቲያናችንን ማገልገል ሲሆን ምእመኑንም ወደ ንሰሃ የመምራት ሃላፊነት አለበት:እናም ምእመኑን በተደጋጋሚ ንሰሃ ማስገባት:ስለ ንሰሃ መስበክ የመጀመርያ አርዕስታቹ እንዲሆን በቸሩ እግዚአብሄር ስም እጠይቃለው!!!!!!!
4:- ይድረስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች:-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን:
በእግዚአብሄር ቸርነት: በእመቤታችን አማላጅነት: በመላእክት ተራዳይነት: በቅዱሳን ፀሎት: ስልጣነ ሃዋርያትንም የያዛቹ አይንተ እግዚአብሄር ካህናት ለህዝበ ክርስቲያኑ እረኛ እንድትሆኑ ለራዳቹ ለእግዚአብሄር ምስጋና ይድረስና: ቸሩ ፈጣርያችን እግዚአብሄር እረኛ እንድትሆኑ አድርጎ የረዳችሁን አምላክን ለማገልገል ዘወትር የማትሰንፉ የክርስቶስ አይኖች እኔ ሳይገባኝ የምለምናቹ እውነተኛ እረኛ በጠፋበት በዚህ ሰአት ነገ ዛሬ ሳትሉ እውነተኛ እረኛ እንድትሆኑን ለልጆቻቹ ወደ ንሰሃ መቅረብን የተቻላችሁን እንድታደርጉል ዘወትር በምጠሩት በቸሩ እግዚአብሄር ስም እጠይቃለው !!!!!!!

ማጠቃለያ:- እግዚአብሄር አምላክ ህይወታችንን ሳይወስድ እድሜ ለንሰሃ እየሰጠን መሆኑን አውቀን ከሃጥያት ርቀን አባቶቻችን በተጓዙበት መንገድ ተጉዘን ህይወታችን አምሮ እና ሰምሮ ኋላም ፍጹም መንግስተሰማያትን ለመውረስ ነገ ዛሬ ሳንል ንስሃ እንግባ !!!!!!!
ይህንንም ጽሁፍ ማነው የጻፈው ከየት ነው የመጣው ከሚለው ምንድን ነው የሚለው ላይ አተኩረን እናንብብ:
ወስበሃት ለእግዚአብሄር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!!!!!!!
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ ህዝቦቿንም ይጠብቅልን!!!!

Thursday, May 6, 2010

ልደታ ለማርያም :- ክፍል 2

ከዚያም በሁአላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም እለቱን ራእይ አይተው ነገር አግንተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት:ወፍ የተባለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:ነጭነቱ ንጽሃ ባህሪው ነው:ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ:የኢያቄምን ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው:7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው:ምልአቱ:ስፍሃቱ:ርቀቱ:ልእልናው:ዕበዩ መንግስቱ ናቸው:ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው::ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱአ ንጽህናዋ:ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቱአ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሱአ ነው:ይህንኑም ራእይ ያዩት ሃምሌ 30 ዕለት ነው::
እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን:ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም:ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ:ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሱአን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ተፀነሰች(በኦሪት ስርአት እሁድ ዕለት ባል እና ሚስት መገናኘት ልማድ ነበርና):እመቤታችን የተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ:ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት:የሃናም የአጎቱአ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቹአ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት:እርሱአም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት:አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርን:እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማሁአቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሱአ ናት አላቸው በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ::
""እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::""
እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም የተወለደችበት እለት በአባት እናቱአ ቤት ፍስሃ ደስታ ተደረገበት ቤቱንም ብርሃን መላው በስምንተኛውም ቀን ""ማርያም"" ብለው አወጡላት::ስለምን ማርያም ብለው አወጡላት ቢሉ:እነሆ በዚ አለም ከሚመገቡት ሁሉ ምግብ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን "ማር" ነው:በገነትም በህይወት የተዘጋጁ ጻድቃን ቅዱሳን "ያም" የሚባል ምግብ አላቸው ::ከዚ ሁሉ የበለጥሽ የከበርሽ ነሽ ሲሉ ስለዚህ "ማርያም" ብለው አወጡላት::የእመቤታችን ማርያም ስም ተነቦ ሳይተረጎም ይቀር ዘንድ አይገባምና:-""ማ"" ማለት ማህደረ መለኮት: ""ር"" ማለት ርግብየ ይቤላ: ""ያ"" ማለት ያንቀዓዱ ኃቤኪ ኩሉ ፍጥረት:""ም"" ማለት ምስሃል ወምስጋድ ወምስትሥራየ ኃጥያት ማለት ነው::አንድም "ማርያም" ማለት ልዩ ከጣዖት:ክብርት እምፍጥረታት:ንጽህት እምሃጥያት:መልክ ከደም ግባት የተሰጣት ማለት ነው:ዳግመኛም "ማርያም" ማለት ተፈስሂ ቤተ ይሁዳ ወተሃሠዪ ቤተ እስራኤል ማለት ነው::
አንድም "ማርያም" ማለት መርህ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው:ይህስ እንዴት ነው ቢሉ:እነሆ ዛሬ በዚህ አለም ለዕውር መሪ በትር እንዲሰጡት ሁሉ እርሱአም በፍቅሩአ:በጣዕመ ፍቅሩአ የሰውን ሁሉ ኃጥያት:ክፋት ፍቃ ከልጁአ ከወዳጁአ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስለሆነች ስለዚህ መርህ ለመንግስተ ሰማያት አሉአት::አንድም ማርያም ማለት ሰረገላ ፀሃይ ማለት ነው:አንድም ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሄር ወሰብእ ማለት ነው:አንድም ማርያም ማለት ውብህት(ስጥውት) ማለት ነው::
በዚህ በግንቦት አንድ ቀን እመቤታችን አለምን ልታስምር ከቅድስት ሃና እና ከቅዱስ እያቄም በብዙ ልመና ተገኘች::
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሩአ ጣዕሙአ በረከቱአ ረድኤቱአ አማላጅነቱአ በእውነት በኛ አማላጅነቱአን በምናምን ልጆቹአ ላይ ይደርብን::
""አለም ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት አይድንም""...................ቸር ያቆየን!!!

ልደታ ለማርያም :- ክፍል 1

ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር:እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ:ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ:አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን:አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት:እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት:እሱአም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም:ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሄር በምህረቱ አይቱአቹአል በሳህሉ መግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዱአ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው:እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሱአም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:ከዛም ፀንሳ በ9 ወሩአ ሴት ልጅ ወለደች:ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት:ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት:ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት:ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት;ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት:ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት:ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች::
ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆተረላቸውምና አልተፃፈም:ይህቺም ሃና በስራት በቅጣት አደገች:ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው(መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት::እነዚህ ቅዱሳን እያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ:ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ:ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ:እያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ:አትናቀኝ:ፀሎተን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ:ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:ሃናም በበኩሉአ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች: እንዲ ብለው ስይዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቹአ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኅኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች:እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን:ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስለት ገቡ::
ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላቹ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው:የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እናቶች እና አባቶች በረከት ይደርብን!!!!!.........ይቆየን

Wednesday, May 5, 2010

አቡነ ዘርዓ ብሩክ

የጻድቁ አባታችን የዘርዓ ብሩክ አባት እና እናት የተባረኩ ከቅዱሳን ወገን የሚሆኑ ነበሩ የአባታቸው ስምም ቅዱስ ደመ ክርስቶስ ሲባል እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርያም ሞገሳ ትባላለች ጻድቁ አባታችን ገና በናታቸው ማህጸን እያሉ ነበር ብዙ ተአምራት የሚያደርጉት እግዚአብሄር መርጡአቸዋልና በሁአላም ከክርስቶስ ልደት በሁአላ በስምንተኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በነሃሴ 27 ጻድቁ አባታችን ተወለዱ በ40ኛ ቀናቸውም ተጠምቀው በካህናት አፍ "ጸጋ ክርስቶስ" ተባሉ ከዛም ቤተሰቦቻቸው በጥሩ እድገት አሳደጉአቸው 7 አመትም በሞላቸው ግዜ በልጅነቴ የዚን አለም ክፋቱን እንዳላይ ብለው ቢጸልዩ አይናቸው ታውሩአል:ቤተሰቦቻቸውም የዚን አለም ትምህርት ሊያስተምሩአቸው አስተማሪ ጋር ቢወስዱአቸው ታመው ተመልሰዋል:የእግዚአብሄር ፈቃድ አይደለምና ነገር ግን የሚያስፈልጋቸውን እውቀት ፈጣሪ አምላክ ራሱ ገልጾላቸዋል:: ክህነትን እስከ ጵጵስና እራሱ መድሃኒአለም ክርስቶስ ሰቶአቸዋል:12 አመትም በሞላቸው ግዜ አይናቸው በርቶላቸው ታላላቅ ተጋድሎን ማድረግ ጀመሩ : የሃጥያት ማሰርያን ያስሩና ይፈቱ ዘንድ ጵጵስናን በሾማቸው ግዜ እግዚአብሄር ያወጣላቸው ሁለተኛ ስም "ዘርዓ ብሩክ" ይባል ነበር 3ኛውም ስማቸው ደግሞ "ጸጋ እየሱስ"ይባላል::
ጻድቁ አባታችን በዚ አለም በህይወተ ስጋ ሳሉ አቡቀለምሲስ እንደሚባል እንደ ዮሃንስ ወልደነጎድጉአድ እግዚአብሄር እሱ ወዳለበት ወደ ሰማይ አውጥቶ በገነት መካከል ያኖራቸው ነበር:: እግዚአብሄር አምላክ ለወዳጁ ለብጹዕ አባታችን ዘርዓ ብሩክ በጎ ነገር እንዳደረገለትና ያለ ድምጽ የሰማይ ደጆችን አልፎ የእሳት ባህርን ተሻግሮ ፈራሽ በስባሽ ሲሆን እንደ ህያዋን መላእክት በፍጥነት ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአድማስ እስከ አድማስ ይደርስ ዘንድ 12 ክንፍን ሰጣቸው:መላእክትም ለሌሎች ቅዱሳን ያልተሰጠ ይህንን ስልጣን አይተው ለምድራዊ ሰው ይህ ነገር እንዴት ይቻላል እያሉ አደነቁ: ከዛም በሁአላ ጻድቁ አባታችን ከፈጣሪ ዘንድ የመላእክትን አስኬማ,የሾህ አክሊል አምሳያ የሆነውን መንፈሳዊ ቆብን,ሰማያዊ ቅናትን እና የደረት ልብስን(ስጋ ማርያም) ተቀብሎ በጾም እና በጸሎት በልመና እና በስግደት እግዚአብሄርን ሲያገለግል ኖረ ከዛም በላይ ወንጌልን እጅግ ብዙ በማስተማር ደከመ ከኢትዮጵያም አልፎ ግብጽ ድረስ ገባ የእስክንድርያውን ሊቀ ፓፓስ አባ ዮሃነስን አገኘውና እርስ በርስ ሰላምታን ተለዋውጠው እጅ ተነሳሱ ከዛም ተመልሶ ወደ ሃገሩ መጣ ከዛም ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመላለሰ ወንጌልን አስተማረ እጅግ ስጋን በሚያስጨንቅ ትጋትም የኢትዮጵያን ህዝብ ማርልኝ እያለ እያለቀሰ ይጸልይ ነበር: አንድ ቀን አባታችን በንጉስ ጭፍሮች ተይዘው ሲሄዱ ዳዊታቸውን ለግዮን ወንዝ አደራ ሰተዋት ከ5 አመት በሁአላ ሲመለሱ ግዮን ሆይ ዳዊቴን ግሺ መልሺሊን ቢሉአት አንድም የውሃ ጠብታ ሳይኖርባት ዳዊታቸውን ብትመልስላቸው ለደቀ መዝሙራቸው ዘሩፋኤል አሳዩትና ግዮንንም "ግሽ አባይ" ብለውታል እስካሁንም በዚሁ ስም የሚጠራው ከዚ በመነሳት ነው::
ከዚህም ሌላ ጻድቁ አባታችን በዚሁ ወንዝ አካባቢ ለ 30 አመት ሲጸልዩ ፈጣሪ አምላክ ጸሎታቸውን ሰምቶ እጅግ ልዩ የሆነ ቃል ኪዳን ሰቶአቸዋል:በስተመጨረሻም የሚያርፉበት እለት በደረሰ ሰአት መልአከ ሞት መቶ እስኪደነግጥ እና ወደ ሁአላው እስኪያፈገፍግ ድረስ ነው ነው እግዚአብሄር ጸጋውንና ክብሩን ያበዛላቸው: በስተመጨረሻም ጥር በገባ በ13 ቀን በ482 አመታቸው ስጋቸው ከነፍሳቸው ተለይታ ገነትን ወርሰዋል::ምንጭ ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክ የጻድቁ አባታችን ገድለ ዜና እንኩአን በዚች በምታህል ጽሁፍ አይደለም የገድላቸውም መጽሃፍም አልበቃውም እንደው እግዚአብሄር አምላክ ከበረከታቸው እንዲያሳትፈን አስቤ ይችን ጥቂት የገድላቸውን ዜና ከገድላቸው መጽሃፍ ላይ አስቀመጥኩ:ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን እኛንም በኚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከታቸውንም ያድለን አሜን... ........ቸር ያቆየን !!!!!

Sunday, May 2, 2010

አባ መቃርስ

አባ መቃርስ በግብጽ ደቡብ መኑፍ ከሚባል አውራጃ ሳሱይር ከሚባል መንደር ከሚኖሩ ሰዎች ወገን ነው:ወላጆቹም ደጎች እውነተኞች ነበሩ አባቱም አብርሃም እናቱም ሳራ ይባላሉ:እናቱም እንደ ኤልሳቤጥ እና ሳራ በእግዚአብሄር ትዛዝ ጸንታ የምትኖር ናት አባቱም በፈሪአ እግዚአብሄር ሆኖ ንጽህናውን እና ቅድስናውን ጠብቆ ሁል ግዜ ቤተ ክርስቲያንን በማግልገል ፀንቶ ይኖራል:እግዚአብሄርም በላያቸው በረከቱን አሳድሮ በስራቸው ሁሉ ከፍ ከፍ አደረጋቸው:ለድሆችም የሚመጸውቱ ለሰው ሁሉ የሚራሩ ናቸው:በፆም በፀሎት ተወስነው እንዲ ባለ ገድል ሲኖሩ ግን ልጅ አልነበራቸውም ለአብርሃምም በለሊት ራእይ ከእግዚአብሄር ዘንድ በልጅ አምሳል ተገለጠለት በአለም ሁሉ የሚታወቅ ብዙ መንፈሳውያን ልጆችን የሚወልድ ልጅን ይሰጠው ዘንድ እግዚአብሄር እንደወደደ ነገረው:ከዚም በሁአላ ይህ የከበረ ልጅ መቃርስን እግዚአብሄር ሰጠው ትርጉአመውም ብፁእ ማለት ነው በላዩም የእግዚአብሄር ፀጋ አደረበት:ለወላጆቹም ይታዘዝ እና ያገለግል ነበር ባደገ ግዜ ያጋቡትም ዘንድ አሰቡ እርሱ ግን ያን አይሻም ነበር ፈቃዳቸውን ይፈፅም ዘንድ ግድ ብለው አጋቡት:ወደ ሙሽራይቱም በገባ ግዜ ራሱን እንደታመመ ሰው አደረገ እንዲሁም ሆኖ ብዙ ቀን ኖረ:ከዚአም በሁአላ አባቱን ተወኝ ወደ ገዳም ልሂድ ከበሽታዬ ትንሽ ጤናን ባገኝ አለው:እግዚአብሄር ወደ ሚወደው ስራ ይመራው ዘንድ ሁል ግዜ በፆም እና በፀሎት ሆኖ ይለምነው ነበር:ከዚህም በሁአላ ወደ አስቀጥስ በረሃ ሄደ ከበረሃው በገባ ግዜ ራዕይን አየ:ስድስት ክንፍ ያለው ኪሩብ እጅና እግሩን ይዞ ወደ ተራራው ላይ እንደሚያወጣው እና የአስቀጥንስ በረሃ ምስራቁአን ምዕራቡአን የዚአችን በረሃ አራት መአዘኑአን አሳይቶ እነሆ ይችን በረሃ መላዋን ላንተ እና ለልጆችህ እርስት አድርጎ እግዚአብሄር ሰቶሃል አለው:ከበረሃውም በተመለሰ ግዜ ያቺ ብላተና ሚስቱ ታማ አገኛት ጥቂት ቆይታ በድንግልናዋ እንዳለች አረፈች:የክብር ባለቤት እግዚአብሄርን አመሰገነ:ከጥቂት ከኖች በሁአላ እናት አባቱም አረፉ:የተውለትንም ገንዘብ በሙሉ ለድሆች እና ለጦም አዳሪዎች ሰጠ:የሳሱይር ሰዎች ግን እውነተኛነቱን እና ቅድስናውን አይተው ቅስና አሾሙት:ከከተማውም ውጪ ቤት ሰሩለት ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን ይቀበሉ ዘንድ ወደ እሱ ይሄዱ ነበር:
በዚአች አገርም አንዲት ድንግል ብላቴና ነበረች ከአንድ ጎልማሳ ጋርም አመንዝራ ፀነሰች ጎልማሳውም አባትሽ ድንግልናሽን ማን አጠፋው ብሎ ሲጠይቅሽ መቃርስ የሚባለው ባህታዊ ቄስ እሱ ስለ ደፈረኝ ነው በይው ብሎ መከራት ፅንሱአም በታወቀ ግዜ አባቱአ ይህን አሳፋሪ ስራ ባንቺ ላይ የሰራብሽ ማነው ብሎ ጠየቃት:እሱአም በአንዲት ቀን መቃርስ ወደሚባለው ቄስ ሄጄ ሳለው በሃይል ይዞኝ ከኔ ጋር ተኛ እናም ከሱ ፀነስኩ ብላ መለሰችለት:ወላጆቹአም በሰሙ ግዜ እጅግ ተቆጡ ከብዙ ሰዎችም ጋራ ወደ ቅዱስ መቃርስ ሄደው ይዘው ከበአቱ አወጡት እሱ ግን ምን እንደሆነ አላወቀም ነበር:ለመሞት እስኪቃረብም አጽንተው ደበደቡት እሱም ሃጥያቴ ምንድን ናትና ነው እናንተ ያለ ርህራሄ ትደበድቡኛላቹና እያለ ይጠይቃቸው ነበር:ከዚህ በሁአላ በፍም የጠቆሩ ገሎችን ባንገቱ ላይ በገመድ አንጠልጥለው ወዲያ እና ወዲ እየጎተቱ የልጃችንን ድንግልና ያጠፋ ይህ ነው እያሉ እንደ እብድ በላዩ ይጮሁ ጀመር:የዚያን ግዜ መላዕክት እንደሰው ተገልጠው የሚያሰቃዩትን ሰዎች ይህ ተጋዳይ ምን አደረገ አሉአቸው እነሱም በልጃቸው ላይ የሃፍረትን ስራ እንደሰራ አድርገው መልሰው ነገሩአቸው እነዚያ መላዕክትም ይህ ነገር ሃሰት ነው እኛ ይህን ሰው ከታናሽነቱ ጀምሮ እንከዚ ቀን እናውቀዋለን:እሱ የተመረጠ ፃድቅ ሰው ነውና አሉአቸው:የታሰረበትንም ፈተው ከላዩ ላይ ገሎቹን ጣሉ እነዚያ ክፉዎች ግን ዋስ እስከሚሰጠን ድረስ አንለቀውም አሉ እጅ ስራውን የሚሸጥለት አንድ ሰው መጣ ለልጅቱአም በየግዜው ምግቡአን ሊሰጣት ዋስ ሆነው ከዚያ በሁአላ አሰናብተው ወደ በአቱ ተመልሶ ገባ ከዚያች ቀን ጀምሮ ራሱን በራሱ መቃርስ ሆይ"እነሆ እንግዲ ባለ ሚስት እና ባለ ልጅ ሆነሃል ለሊት እና ቀን መስራት ይገባሃል" እያለ ያቺ ሃሰተኛ ልጅ የምትወልድበት ግዜ እስኪደርስ ድረስ እንቅቦችን ቅርጫቶችን እየሰራ ለዚያ ወዳጅ ለሆነውና ለሚያገለግለው ወንድም ይሰጠውና ያም ሰው እየሸጠ ለዚያች ሃሰተኛ ልጅ እየሰጠ ኖረ::
የምትወልድበት ቀን ሲደርስ እጅግ አስጨነቃት በታላቅ ሲቃይ ውስጥ አራት ቀኖች ያህል ኖረች ለሞትም ተቃረበች እንቱአም ካንቺ የሆነው ምንድን ነው የተሰራ ስራ አለና ንገሪኝ አለቻት እሱአም በ እግዚአብሄር አገልጋይ ላይ ዋሽቻለውና ያመነዘርኩት ከእከሌ ጎልማሳ ጋር ሲሆን በ እውነት ሞት ይገባኛል አለቻት:አባት እና እናቱአም በሰሙ ግዜ ደንግጠው እጅግ አዘኑ የሃገር ሰዎችም ሁሉ ተሰበሰቡ በርሱ ላይ የሰሩትን በደል ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ ቅዱስ መቃርስ ሄደው ለመኑት ያን ግዜ በበረሃ ያየውን ያንን ራዕይ አስታውሶ ይቅር አላቸው ቀድሶም ቅዱስ ስጋውንንና ክቡር ደሙን አቀበላቸው:ክንፉ ስድስት የሆነ ኪሩብ ደግሞ ተገለጠለት ትርጉአመውም የልብ ሚዛን ወደተባለ ወደ አስቀጥስ በረሃ እጁን ይዞ መርቶ አደረሰው:ቅዱስ መቃርስም ያንን ኪሩብ ጌታዬ ሆይ በውስጡ የምኖርበትን ቦታ ወስንልኝ አለው ያ ኪሩብም አልወስንልህም የ እግዚአብሄርንም ትዛዝ አትተላለፍ እነሆ ይህ በረሃ ሁለመናው ላነተ ተሰቱአል እና ወደ ፈለክበት ሄደህ ተቀመጥ ብሎ መለሰለት:ቅዱስ መቃርስም የቅዱሳን ሮማውያን የመክሲሞስና የደማቴዎስ ቦታ ወደ ሆነው ከውስጠኛው በረሃ ገብቶ ኖረ:እነሱም በመጥኡ ግዜ ከርሱ አቅራቢያ ኖረዋልና ከረፍታቸው በሁአላ ግን ሄዶ በዚያ ቦታ እንዲኖር የ እግዚአብሄር መልአክ አዘዘው:ይህውም ዛሬ የሱ ገዳም የሆነው መላእኩ ይህ ገዳም በመክሲሞስ እና በደማቴዎስ በስማቸው ይጠራልሥላለው እስከዚች ቀን ደብረ ብርስም ተብሎ ይጠራል ትርጉአመውም የሮም ገዳም ማለት ነው:የከበረ አባ መቃርስም ታናሽ በአት ሰራ በውስጡአም ሆኖ ያለ ማቁአረጥ በጾም በፀሎት በስግደትም በመትጋት ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ሰይጣናትም ተገልጠው የሚመጡበትን እና በቀንም በለሊትም በግልጽ የሚዋጉት ሆኑ:በጾም እና በጸሎት ሲጋደል ሰይጣናት እየተዋጉት እርፍትን ስላላገኘ በልቡም እንዲ አሰበ በአለም ውስጥ ሳለው የቅዱስ አባ እንጦንዮስን ዜና ሰምቻለው የምንኩስናን ስራት ያስተምረኝ እና ይመራን ዘንድ ተነስቼ ወደሱ ልሂድ የረከሱ ሰይጣናት የመከሩትን ምክራቸውን እገለብጥ ዘንደ እሱ እውቀትን እና ማስተዋልን ይሰጠኛልና አለ ያን ግዜም ተነስቶ ጸሎት አድርጎ ወደ አረጋዊ አባ እንጦንዮስ ዘንድ እስከሚደርስ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ተጉአዘ አባ እንጦንዮስም ከሩቅ ባየው ግዜ እነሆ ተንኮል ሽንገላ የሌለበት ክርስቲያን አለው በታላቅ ደስታም ተቀብሎ ሳመው:አባት ለልጁ እንደሚገልጥ ሃሳቡን ሁሉ ገለጠለት ይህ አረጋዊ አባ እንጦንዮስም የመቃርስን ራሱን ስሞ ልጄ ሆይ በዮናኒ ቁአንቁአ እንደ ስምህ ትርጉአሜ አንተ ብጹእ ትባላለህ ስራህንና ወደኔ መምጥትህን ፈጣሪ እግዚአብሄር ገልጦልኛል እና ስለዚህ መመጥትህን የምጠባበቅ ህንኩ አለው::
ከዚም በሁአላ ለአባ መቃርስ የከበረች የምንኩስናን ስራት አስተማረው መሰራት በሚገባ በብዙ ነገርም አጸናው ሰይጣናት የሚዋጉት መሆናቸውን እነሱም በስውር በፈቲው ጦር እንዲሁም ጥፋት በሆኑ ስራዎች ሁሉ ይዋጉሃል:አንተ ፍፁም ልትሆን አንተም እስከሞት ደርሰህ ታገስ አሁንም እግዚአብሄር ወደ ወሰነልህ ቦታ ሄደህ ስራህን እየሰራህ በውስጡም ታገስ ብሎ ገለጠለት:ከአባ እንጦንዮስ ዘንድ የምኩስናን ስራት እየተማረ ጥቂት ቀኖች ከኖረ በሁአላ ከተባረከ ኤጲስ ቆጶስ ከአባ ሰራብዮን ጋራ በተማራቸው ህያዋን በሚያደርጉ ትምህርቶች እና ስራቶች ፈጽሞ ደስ እያለው ወደ በአቱ ተመለሰ:
አባ መቃርስም በአባቴ በአባ እንጦንዮስም ዘንድ በነበርኩባቸው ቀኖች ሲተኛ ከቶ አላየውትም አለ:አባ መቃርስም በምንኩስና ስራት ተጠምዶ እየተጋደለ ብዙ ግዜ ኖረ ያ ኪሩብ መላእክም በግልጽ ይጎበኘው ነበር:በአንዲት ቀንም እንዲ የሚለውን ቃል ከሰማይ ሰማ ቃሌን እና ትእዛዘን ሰምተህ ወደዚህ መተህ በዚ ቦታ ውስጥ ስለኖርክ እነሆ ቁጥር የሌላቸውን የብዙ ብዙ ወገኖችን ከነገዶች ከሃገሮች በቁአንቁአ ከተለያዩ ህዝቦች እሰበስባለው እነሱም በዚ ቦታ ያገለግሉኛል የከበረ ስሜንም ያመሰግናሉ በበጎ ስራቸው እና ትሩፋታቸው ደስ ያሰኙኛል አንተም ተቀበላቸው እውነተኛ የድነት መንገድም ምራቸው ይሄንንም ቃል በሰማ ግዜ ተበረታታ ልቡም ፀና በለሊቲም በጸሎት ግዜ ቆሞ ሳለ የክብር ባለቤት ጌታችን ጆሮውን ከፍቶለት ሰይጣናት ሲማከሩ ሰማቸው እንዲህም አሉ ይህን ሰው በዚ በረሃ እንዲኖር ብንተወው የብዙ ብዙ ወገኖችን ይመራቸዋል እንሱም በዚ በረሃ ውስጥ ነዋሪዎች ሆነው የሰማይዋን ሃገር ያደርጉታል እንሱ ለዘላለም ጸንቶ በሚኖር ህይወት ይተማመናሉና እኛንም በሚቀጣ ጸሎታቸው ቀጥተው አሰቃይተው ያሳድዱናልና ከዚ ቦታ ልናሳድደው እስኪ እንችል እንደሆነ ኑ ዛሬ ብሱ ላይ እንሰብሰብ ሲሉ ሰማቸው አባ መቃርስም ይህንን በሰማ ግዜ ልቡ ጸና በሰይጣናት ላይም ተበረታታ የሰይጣናት ምክራቸውን እስከሚሰማ ጆሮውን የከፈተለት እግዚአብሄርን አመሰገን:ደካማነታቸውንም አወቀ ::
ከዚ በሁአላ ይዋጉት ዘንድ ሰይጣናት በርሱ ላይ ተሰበሰቡ በደጁ እሳትን እያነደዱ ከሳቱ እያነሱ ወደ በአቱ ይጨምሩ ጀመር ያቺ እሳት ግን በጸሎቱ የሚጠፋ ሆነች ከዚ በሁአላ እንሣዊ በሆነ ስራ በፍትወት(ዝሙት)ጦር ተውጉት በዚም ታገሰ:ትካዘን አለማዊ ክብር መውደድን ትቢትን መመካትን ታካችነትን ስድብን ሃይማኖት ማጣትን ከእግዚአብሄር ዘንድ ተስፋ መኩረጥን በልቡ አሳደሩበት ከዚ ሁሉ በሚበዛ ተዋጉት የከበረ አባት አባ እንጦንዮስ እንደነገረው በኝህም አጥፊዎች በሆኑ ስራዎች ሰይጣናት እየተዋጉት ረጅም ግዜ ከኖረ በሁአላ ዳግመኛ ወደ አባት እንጦንዮስ ተነስቶ ሄደ ይህም አባት ገና ከሩቅ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ በልቡ ሽንገላ በእውነት የሌለበት ክርስቲያን ነው ልጆቼ ይህን የከበረ ሰው ታዩታላቹን እሱ ለብዙ ወገኖች የቀና የጽድቅ በትር እና ረጅም አላማ ይሆን ዘንድ አለውና:ከአሸናፊ እግዚአብሄር አፍ የተገኘ ጣፋጭ ፍሬም ይሆናልና አለ:ወደ ቅዱስ አባ እንጦንዮስም በቀረበ ግዜ በምድር ላይ ሰገደለት በፍጥነትም ቀና አድርጎ ሳመው ፊቱ እንደበሽተኛ ፊት ተለውጦ አይቶታልና ይህውም ሰይጣናት አብዝተው ስለተዋጉት ነው:ከዚያም ጸሎት አድርገው በአንድነት ተቀመጡ አባት እንጦንዮስ ደስታ በተመላ ቃል ልጄ መቃርስ በደና አለህን? አለው ቅዱስ መቃርስም እነሆ ከኔ የሆነውን ሁሉ እግዚአብሄር ቀድሞ ገልጦልሃል ብሎ መለሰለት:እሱም ያን ግዜ አስተማረው አጽናናው እንዲህም ብሎ መከረው:መንፈሳዊ ጥበብን ለሚሹ ለብዙ ወገኖች መምህራን እንድትሆን ይህቺውም ምንኩስና ናት ከጠላታችን በላያችን የሚመጣብንን መከራ ሁሉ ልንታገስ ለኛ የሚገባ ነው ልጄ መቃርስ ሆይ ውሃ ለመቅዳት ስትሄድ እግዚአብሄር የነገረህን ያንን ቃል አስብ አለው:ቅዱስ መቃርስም ሰምቶ እጅግ አደነቀ የተሰወሩ ስራዎቹ በከበረ አባት ለ እንጦንዮስ የተገለጡለት እንደሆኑ አወቀ በርሱ ዘንድም እየተማረና በረከትን እየተቀበለ ብዙ ቀኖች ኖረ ከዚያም የከበረች አስኬማን ያለብሰው ዘንድ ፈለገ አባ እንጦዮስም በላዩ ጸለየ እርሱአን አስኬማይቱን አለበሰው ስለዚ የከበረ እንጦንዮስ አባት ተባለ::
ዳግመኛም ወደዚህ ወደኔ መመጣትን ቸል አትበል እኔ ከጥቂት ቀኖች በሁላ ወደ እግዚአብሄር ሄዳለውና አለው አባ መቃርስም ይህንን ነገር በሰማ ግዜ ተነስቶ ሰገደለት መንፈሳዊ በረከቱን ይቀበል ዘንድ ከርሱም ዘንድ እንዲኖር ለመነው እሱም ተቀመጥ አለና ተቀመጠ:ዳግመኛም አባ እንጦንዮስ ከጥቂት ቀኖች በሁአላ ሰይጣናት በኔ ላይ እንዳደረጉት በግልጥ ከተዋጉህ በሁአላ ከዚ ከክፉ ሃሳብ ውጊአ እግዚአብሄር ያሳርፍሃል እና በርትተህ ታገስ:እስከ እድሜህ ፍጻሜ ካነተ ጋር ሆኖ እንዲረዳህ እግዚአብሄር ያደረገውን ጠባቂሂን መልአክ እንዳታሳዝነው ተጠበቅ አለው:ከዚ በሁአላ አባ እንጦንዮስ ለአባ መቃርስ በትሩን ሰጠው በመንፈሳዊ ሰላምታ ተሰናብቶት አረፈ:ሲጋውንም ማንም በማያቀው ስውር ቦታ ቀበረው:የከበረ አባ መቃርስም ወደ በአቱ ተመልሶ በአስቀጥስ ገዳም ተቀመጠ ዜናውም በአራቱ መአዘን ተሰማ እግዚአብሄርም በጆቹ አስደናቂዎች ተአምራትን አደረገ::
ከዚህ በሁአላ የከበረ አባ መቃርስ ተመልሶ ከርሱ አስቀድሞ በዚያ አስቄጥስ በርሃ ውስጥ ሰው እንዳለ ያይ ዘንድ ወደ በረሃ ውስጥ ዘልቆ ገባ:ራቁታቸውን የሆኑ ሁለት ሰዎች አይቶ ፈራ የሰይጣን ሚትሃት መስሎታልና 'እልቦት' 'ቦሪቦን' ብሎ በህቡ የ እግዚአብሄር ስም ጸለየ ይህም አቡነ ዘበሰማያት ማለት ነው:እንሱም በስሙ ጠርተው መቃርስ ሆይ አትፍራ አሉት እርሱም በበረሃ የሚኖሩ ቅዱሳን እንደሆኑ አውቆ ወደነሱ ቀርቦ እጅ ነሳቸው እነሱም በአለም ስላሉ ሰዎች ስለ ስራቸው ጠየቁት እርሱም በቸርነቱ እግዚአብሄር በሁሉም ላይ አለ ብሎ መለሰላቸው:እርሱም ደግሞ የክረምት ቅዝቃዘ ይቀዘቅዛቸው እንደሆነ የበጋውን ትኩሳት ያያልባቸው እንደሆነ ጠየቃቸው እነሱም በዚ በረሃ እግዚአብሄር 40 አመት ጠብቆናል የክረምት ቅዝቃዜ ሳይቀዘቅዘን የበጋ ትኩሳት ሳያቃጥለን ኖረናል ብለው መለሱለት:ደግሞ እነደናንተ መሆነ እንዴት እችላለው አላቸው እነሱም ወደ በአትህ ተመልሰህ ስለሃጥያትህ አልቅስ አንተም እንደኛ ትሆናለህ አሉት:ከነሱም በረከትን ተቀብሎ ወደ በአቱ ተመለሰ::
በርሱ ዘንድ መነኮሳት በበዙ ግዜ ጉድጉአድ ቆፍረው መታጠቢያ ሰሩለት ሊታጠብ በወረደ ግዜ ሊገሉት ሰይጣናት ጉድጉአዱን በላዩ ላይ አፈረሱት መነኮሳትም መተው ከጉድጉአዱ አወጡት:እግዚአብሄርም ከዚ አለም መከራ ያሳርፈው በወደደ ግዜ ሁልግዜ የሚጎበኘውን ኪሩብን ወደ እርሱ ላከ እርሱም እኔ ወዳንተ መጥቼ ወስድሃለው እና ተዘጋጅ አለው ከዚያ በሁአላ አባ እንጦንንንና የቅዱሳንን አንድነት መሃበርን ሰማያውያን የሆኑ የመላእክት ሰራዊትን በ እግዚአብሄር እጅ ነፍሱን እስከሰጠ ድረስ ያይ ነበር:መላ የእድሜው ዘመንም 97 ሆነ መጋቢት 27 ቀንም ከዚ ከአላፊው አለም ወደማያልፈው አለም ነፍሱ ሄደች: የቅዱስ መቃርስ ነፍስ ወደ ሰማይ ስታርግ እንዳየ በዚ ነገር ደቀ መዝሙሩ አባ በብኑዳ ምስክር ሆነ:ሰይጣናትን እንደሰማቸው እየተከተሉ መቃርስ ሆይ አሸነፍከን አሸነፍከን እያሉ ሲጮሁ እስካሁን ገና ነኝ አላቸው ወደ ገነት ሲገባ መቃሪ ሆይ አሸነፍከን ብለው በታላቅ ድምጽ ጮሁ የክብር ባለቤት ፈታሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመስገን ስሙም ይባረክ ከእጃቹ ያዳነኝ አላቸው:ብሎ መስክሮአል:የስጋውም ፍልሰትም እንደዚ ሆነ እሱ በህይወት ሳለ ስጋውን እንዳይሰውሩ ልጆቹን አዙአቸው ነበር የሃገሩ የሳሱይርም ሰዎች መተው ለደቀ መዝሙሩ ለዮሃንስ ገንዘብ ሰጡ ይንንም ስለገንዘብ ፍቅር ይመክረው እና ይገስጸው የነበረ ገንዘብ ከመውደድ ተጠበቅ የሚለው ነው:እርሱም መርቶ የቅዱስ አባ መቃርስን ስጋ አሳያቸው ወደ ሃገራቸው ሳሱይር ወሰዱ እስከ አረብ መንግስት 160 ዘመን በዚያ ኖረ ደቀ መዝሙሩ ዮሃነስ ግን ገንዘብ ስለመውደዱ ዝልጉስ ሆነ::
ከዚያም በሁአል ልጆቹ መነኮሳት ወደ ሃገሩ ወደ ሳሱይር ሄዱ የከበረ አባት የአባ መቃርስን ስጋ ሊወስዱ ፈለጉ:የሃገሩ ሰዎችም ከመኮንኑ ጋር ተነስተው ከለከሉአቸው በዚያችም ለሊት የከበረ አባ መቃርስ ለመኮንኑ ተገልጦ ተወኝ ከሊጆቸ ጋር ልሂድ አለው መኮንኑም መነኮሳቱን ጠርቶ የአባታቸውን ስጋ ተሸክመው ይወስዱ ዘንድ ፈቀደላቸው:በዚአን ግዜም ተሸክመው አክብረው ወሰዱት በብዙ ምስጋና በመዘመርም እግዚአብሄርን እያመሰገኑ ነሃሴ 19 ቀን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ::
ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ መቃርስ እና በአባ እንጦንዮስ ፀሎት እና አማላጅነት የምትገኝ በረከት ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች እንዲሁም ከሃገራችን ከኢትዮጵያ ጋር ለዘላለም ይኑር አሜን!!!!!!...................ቸር ያቆየን.

Saturday, May 1, 2010

ተአምረ ጊዮርጊስ

ተአምረ ጊዮርስ 12ኛ ተአምር:- ፀሎቱና በረከቱ ልመናው ለሁላችን በእውነት ለዘላለሙ ይደረግልንና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረገው ተአምር ይህ ነው:: በፍጹም ልቡ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚወድ በግብጽ ሃገር የሚኖር አንድ ሰው ነበረ ከፍቅሩም ብዛት የተነሳ እጅግ ያማረ ቤተ ክርስቲያን አሳነፀ:የእግዚአብሄርንም የህጉን ታቦት ለማስገባት በፈለገ ግዜ አንድ ከሃዲ ንጉስ መጣና ከሚስቱ ጋር ከቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ መኖሪያውን በዚያ አደረገ:ሰውየውም በችኮላ ሄዶ ይህንን ነገር ለሊቀ ጳጳሱ ነገረው ሊቀ ጳጳሱም ተነስቶ ወደ ንጉሱ ሄደና ለምን የማይገባ ስራ ከቤተ ክርስቲያን ገብተህ ስለምን ትቀመጣለህ ቤተ ክርስቲያኒቱ የታነፀችው በሃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ነውና አለው::ንጉሱም ይህንን ንግግር ሰምቶ እጅግ ተቆጣና ያስረው ይገርፈውም ዘንድ ወደደ ሊቀ ጳጳሱም እጅግ አዘነና አይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲ ሲል አዳኘው:"ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ እኔ ሰማዕት ነኝ አትበል:በዚህ በአላዊ ንጉስ ላይ ሃይልህን የማትገልጽ ከሆነ ከማህበረ ሰማዕት ሁሉ ጋራ በእግዚአብሄር ፊት አትቁም":ሊቀ ጳጳሱም ይህንና የመሳሰለውንም ሁሉ እየተናገረ ሳለ ሃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ በግልጽ እያዩት በነጭ ፈረስ ተቀምጦ በሰማይ ላይ እንደ እሳት እያንበለበለ በድንገት ከተፍ ብሎ ወደ ከሃዲው ንጉስ ገባና በጦር ወግቶ ከዙፋኑ ገለበጠው ከቤተ ክርስቶያኑም ሩቅ በሆነ ቦታ ወስዶ በምድር ላይ ዘረረውና በዚያን ግዜ ክፉ ሞት ሞተ:ሚስቱም እንዲሁ:የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቱን ሁሉ በተነው ከቶ ምንም የተረፈ አልነበረም::በዚያም የነበሩ ሰዎች ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ወደቀባችው ፈጽመውም አደነቁ ሊቀ ጳጳሱም ከተደረገው ተአምራት የተነሳ ደነገጠ ፈጽሞም አደነቀ:ከዚህም በሁአላ ሃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ጳጳሱን ከገዘትከኝ ግዝት ፍታኝ አለውና ፈታው::ነዚያን ግዜም በስሙ ከታነፀው ቤተ ክርስቲያን በፍጹም ደስታ በምስጋናና በዝማሬ በሃያሉ ሰማዕት በቅዱስ ጊዮርጊስ እጅ ሃይሉን የገለፀውን እግዚአብሄርን እያመሰገኑ ታቦተ ህጉን አስገቡ::ፀሎቱና በረከቱ አማላጅነቱ ለሁላችን በዕውነት ይደረግልን ለዘላለሙ አሜን!!!!!...........ቸር ያቆየን.

Friday, April 30, 2010

ቅዱስ ጊዮርጊስ

የቅዱስ ጊዮርጊስ አባቱ መስፍን ሲሆን ሲሙም አንስጣስዮስ ይባላል አገሩም ቀጰዶቅያ ሲሆን እናቱም ቴዎብስታ ትባላለች እሱአም ከፍልስጤም አገር ናት ከዛም ትንሽ ሆኖ ሳለ አባቱ አረፈ: 20 አመትም በሆነው ግዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉስ ዱድያኖስ ዘንድ ሄደ:ንጉሱም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲያመልኩ ሰዎችን ሲያስገድዳችው አገኘው:ይህንን አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዘነ በርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድሆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነጻ አወጣቸው:ከዛም በንጉስ ፊት ቆሞ በክብር ባለቤት በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ:ንጉሱም አባበለው ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም:ለመስማት እንኩአን የሚያስጨንቅ ስቃይን አሰቃየው ጌታችን ግን ሁሌም ያጸናዋል ቁስሉንም ያድነዋል:3 ግዜ እንደሚሞት እሱም እንደሚያስነሳው በአራተኛውም የምስክርነት አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው:ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በአለም ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ:በተጋድሎ እና መከራ በመቀበል ሰባት አመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው: ንጉሱም ባለመታዘዙ እና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ስራየኛ አመጣና እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ ሞልቶ አስማቱን ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው:ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር ቅዱሱም ያንን ጽዋ በጌታችን ስም አማትቦ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም:ያ መሰርይም በክብር ባለቤት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ወዲያው ሰማእት ሆኖ አረፈ:ያንንም ተአምር አይተው ብዙዎች ሰዎች በሰማእትነት ሞተው የህይወት አክሊል ተቀበሉ ቁጥራቸውም 30,700 ነፍሳት ናቸው:ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባው ነገስታት ፊት በቆመ ግዜ በዚያም የተቀመጡባቸው ወንበሮች ነበሩ ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸው ወንበሮች እንዲበቅሉና እንዲያብቡ እንዲያፈሩም ታደርጋቸው ዘንድ ካንተ እንሻለን አሉት:በዚአን ግዜም ጸልዮ እንዳሉት አለመለመው ይህንን ድንቅ ስራ አይተው ቁጥር የሌላቸው ብዙ አህዛብ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ:ከዛም ቅዱሱን ወስደው በጎድጉአዳ ምጣድ ውስጥ አበሰሉት:አቃጥለው አሳርረውም ስጋውንንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት:ጌታችንም ነፍሱን ወደ ስጋው መልሱአት ደግሞ አስነሳው:ወደ ነገስታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረ ቁትር የሌላቸው አህዛብ አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማእትነት ሞቱ:ነገስታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታስነሳ አምላክህ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናምናለን በርሱም እናምናለን አሉት ቅዱሱም ጸለየ ከጉድጉአድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶችን ጎልማሶችንም አስነሳላቸው እነዛም በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማሩ የገሃነምንም ወሬ ተናገሩ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው አረፉ: ከሃድያን ነገስታቱ ግን ሙታንን ያስነሳህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ ከዚአም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሳ ከአንዲት ደሃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እሱአም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሄርም መልኣክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ መኣድ አቀረበለት የዚያች መበለትም የቤቱአ ምሰሶ ቅርንጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ ያችም መበለት በተመለሰች ግዜ የቤቱአ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ሲለማእዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደ እኔ መጣ አለች ቅዱሱም እኔ አምላክ አይደለውም የአምላክ ባርያ ነኝ እንጂ አላት እሱአም እንዲ ብላ ለመነችው የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ችርነትህ እንድትደርሰኝ እለምንሃለው እውር ደንቆሮ ድዳ ጎባጣ የሆነ ልጅ አለኝ እና ታድንልኝ ዘንድ እለምንሃለው ስለጌታችን እምነትም አስተማራትና መበስቀል ምልክት አማተበው ያን ግዜም ልጁ አየ ቅዱሱም በሌላ ግዜ እንዲሰማ እንዲናገር እና እንዲሄድ እንዲያገለግለኝም እኔ እሻለው አልት በዚአን ግዜ ንጉሱ በአገሩ መዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያችን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለሱአም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሱአ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቱአ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት ንጉሱም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አስገረፈው በመንኮራኩርም አበራዩት ሞቶም ከከተማ ውጩ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሳው ወደ ነገስታቱም ተመለሰ ንጉሱም አይቶ ደነገጠ ስለህይወቱም አደነቀ ከዚያም በሁአላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግስቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊሲም እየዘበተበት ነገ በጠዋት ለአምልክቶችህ መስዋትን አቀርባለው አንተም ህዝብ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሰዋ እንዲያዩ አለው:ንጉሱም እውነት የሚሰዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግስቱም እልፊኝ አስገብቶ አሳደረው ለጸሎትም ተነሳ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለእስክንድርያ ንግስት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጉምላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እግዚአብሄር አለምን ከፈጠረበት ሰው እስከሆነበት ግዜ የሆነውን ሁሉ ያስረዳት ጀመር ትምህርቱም በልቡአ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች በማግስቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሰዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ አዋጅ ነጋሪ ዞረ የበቱአን ሚሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ እውነት መስሉአት እጅግ እያዘነች ልጁአን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች ቅዱስ ጊዮርጊስም ባያት ግዜ ፈገግ አለ ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዛም ልጁአን ጠርቶ ወደ አጵሎን ሂድ ወደ እኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ስም እዘዘው አለው ያን ግዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ አዘዘው ወደ ጣዎቱ ቦታ ሄዶ አዛዘው በጣዖቱ ያደረ እርኩስ መንፈስም ከማደሪአው ወቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳለበት መቶ እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለውም ብሎ በህዝብ ሁሉ ፊት አመነ ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖታቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋር አጠፋቸው ንጉሱም ከወገኖቹ ጋር አፈረ:ብስጭት እና ቁታንም እንደተመላ ወደ ንግስት ምስቱ ዘንድ ገባ እሱአም አምላካቸው ጽኑ እና ሃያል ነውና ክርስቲያኖችን አትጥላቸው አላልኩህምን አለችው ይህንንም ከሱአ ሰምቶ በርሱአ ላይ እጂግ ተቆጣ ወደ ክብር ባለበት ክርስቶስ እምነት የከበረ ጊዮርጊስ እንደአስገባት አወቀ ከዚም በሁአላ ከከተማ ውጪ እንዲጎትቱአት እና በመጋዝም እንዲሰነጥኩአት አዘዘ የሰማእትነትንም አክሊልንም በመንግስተ ሰማያት ተቀበለች በዚያን ግዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስራ ነገስታቱ ሁሉም ደነገጡ ሃፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከርሱም እንድያርፍ ራሱን በስይፍ ይቆረጥ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉስ ዱድያኖስን መከሩት ያን ግዜም የክብር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ሰንድ አዘዘ ድል አድራጊ ጊዮርጊሲም እጂግ ደስ አለው እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገስታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው ወዲያው እሳት ከሰማይ ወርዶ ከነሰራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገስታት አቃጠላቸው ከዚም በሁአል የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው በምድር መታሰቢያህን የሚያደርጉ ሁሉ እኔ ሃጥያቱን ሁሉ ደመሣለው በመከራም ውስጥ ሆኖ በባህርም ሆነ በየብስ,ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለው ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ ከዚ በሁአላ ከ7አመት ተጋድሎ በሁአላ ሚያዚያ 23 ቀን ራሱን ዘንበል አድሪጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግስተ ሰማያት አክሊላትን ተቀበለ ከአገልጋዮቹም የቀሩት ሲጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደ ሃገሩም ልዳም ወሰዱት ቤተ ክርስቲያንም ሰርተው በውስጡአ አኖሩት ከርሱም ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጠ ለእግዚአብሄርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ ጊዮርጊሲም በረከቱ ረድኤቱ ሃገራችን ኢትዮጵያን እና ህዝቦቹአን ከስጋና ከነፍስ መከራ ይጠብቅልን!!!!!...................ቸር ያቆየን!

Thursday, April 15, 2010

አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

የአባታችን የእስትንፋሰ ክርስቶስ የተወለዱበት ቦታ ዳውንት ፀውን ዓባይ ይባላል:በሰሜን በኩል የእናታቸው ሃገር ደብረ ድባ የቄርሎስ ቦታ ይባላል:የአባታቸውም ሃገር የእግዚአብሄር አብ ደብር አጠገብ ዳውንት(ደብረ አስጋጅ)ይባላል:የአባታቸውም ስም መልዓከ ምክሩ ሲባሉ እናታቸው ደግሞ ወለተ ማርያም ይባላሉ:እነዚ ባል እና ሚስት በህግ ጸንተው የሚኖሩ እንደ ዘካሪያስ እና እንደ ኤልሳቤጥ መልካም ስራን በመስራት እግዚአብሄርን የሚያገለግሉ ነበሩ:ቀድመውም 2 ልጆችን ወልደው ነበር እና ከዛም እመቤታችንን የተባረከ እግዚአብሄርን የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም ልጅ እንድትሰጣቸው ዘወትር ይለምኑአት ነበር: እግዚአብሄርም ፀሎታቸውን ሰምቶ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሚያዚያ 8 ተፀነሱ እና ታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ:ልክ በተወለዱ እለትም ተነስተው በግራቸው ቆመው 3 ግዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ብለው አመሰገኑ:9 ግዜም ሰግዱ:ከዚህም በሁአላ በ40 ቀናቸው ጥምቀትን ተጠምቀው ስማቸውም እስትንፋሰ ክርስቶስ ተባለ:ከዛም ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸው አደጉና አባትየው ዋሻ ውስጥ 60 አመት ወደ ኖረ ቅዱስ ኪራኮስ ወደ ሚባል አባት ወሰደው ትምህርት እንዲያስተምረው ለመኑት:ከዛም ፃድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በአባ ኪራኮስ ተመርቆ ትምህርቱን ጀመረና እንደሌላው ሰው ጊዜ አልፈጀበትም:ወዲአው ይረዳ ነበር ከዛም ፃድቁ አባታችን የተለያዩ የሃይማኖት ትምህርቶችን በፍጥነት ተማረ ከዛም በክርስቶስ ፍቅር በእመቤታችን ፍቅር ልቡ ደማ:በውስጥ በአፍአ ድንግል ስትሆን የህያው የእግዚአብሄር አብ የባህርይ ልጅ ወልድን በጡቶቹአ ወተት አጥብታ ያሳደገችው በሁለት ወገን ድንግል የምትሆን መልካሚቱአ እርግብ እመቤታችን ጽጌ የሚባል ልጁአን እንደምትስም እንዲሁ ጻድቁ አባታችንን ትስመው ነበር:ከዛም አባታችን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ቅኑት እንደገበሬ ፅሙድ እንደበሬ ሆኖ ሳይመነኩስ የምንኩስናን ስራ መስራት ጀመረ:እንደ እሳት ወላፈን ፈጥኖ የሚያልፍ የዚን አለም ጣዕም በመናቅ ህሊናው እንደ እሳት ነደደ አንደበቱም 46ቱን ብሉያትን 35ቱን ሃዲሳትን መጽሃፍ አንባቢ አደረገው ከዚህም ሌላ ቅዱሳት መጽሃፍትን:-150ውን መዝሙረ ዳዊት,ድርሳናትን ውዳሴ ማርያምን,የጻድቃን እና የሰማእታትን መልክአ,አስራ ስምንቱን ተአምረ ማርያም,ተአምረ እየሱስ,የሰኔ ጎሎጎታ,ልፋፈ ጽድቅ,እቀበኒ ክርስቶስ,7ቱ ኪዳናትን,ባርቶስ,እና ገድለ አቡነ ኪሮስ,ጊዮርጊስ,ኤዎስጣቴዎስ,ገብረ መንፈስቅዱስ,ተሰአቱ ቅዱሳን እንዲሁም ሰይፈ ሲላሴን እና ሰይፈ መለኮትን እንዲሁም ሌሎችን ቅዱሳን መጽሃፍቶችን ዘወትር አብዝቶ ይፀልይ ነበር:ጻድቁ አባታችን ጾምና ጸሎትን ትዕግስት አርምሞ ልጉአም ሆኑለት:እግሮቹ በሐዋርያት ወንጌል ጭንጫ ላይ ቆሙ:ቅድስት ንጽህት ድንግል በምትሆን በእመቤታችን በማርያም ፍቅር ገመድ ተጎተተ:የአሸናፊ የእግዚአብሄር ስሙን በመፍራት ሰውነቱን ይገስጻል:በጻድቃን እና በሰማእታት ጎዳና ሰውነቱን ያሮጠዋል:ከዛም አባ ኪራኮስ አባታችንን መርቆ ወደ አባቱ ሰደደው:ከዛም አባትየው ስሙ ማርቆስ ወደሚባል ጳጳስ ክህነት ይሰጠው ዘንድ ወሰደው ከዛም ጳጳሱ ባርኮ ዲቁና ሾመው እና ወደ ሃገራቸው ዳውንት ተመለሱ:ከዛም በእመቤታችን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በድቁና ያገለግል ጀመር አባቱን እና እናቱንም በማገልገል እስከ 14 አመቱ ድረስ ተቀመጠ በሁአላም በ 14 አመቱ አለምን ንቆ ይመንን ዘንድ ለቤተሰቦቹ ነገራቸው አባቱም ቤተ ክርስቲያን ሄዶ አልቅሶ ቢጸልይ "ይመነኩስ ዘንድ ይሂድ ስልጣኑ እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ይላል ስም አጠራሩ እስከ አለም ዳርቻ ይደርሳል"የሚል ቃል ከሰማይ ሰማና በፍቅርና በሰላም አሰናበቱት:ከዛም አባታችን በ14 አመቱ ብዙ ገዳማትን እየጎበኘ ወደ ደብረ ሃይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞአ ደረሰ:ከዛም እንደገዳም ስርአት 3 አመት ተፈተነና ከዛም ምንኩስናን ለበሰ ከዛም ከብዙ ተጋድሎ በሁአላ ድቁና ወደ ሾመው ጳጳስ ሄዶ ቅስናን ተቀበለ ከጥቂት ቀንም በሁአላ ቁምስናን እና ኤጲስቆጶስነትንም ሾመው:ከዛም አባታችን "ጌታችን ሰውነቱን በገራህተ መስቀል የጣለ ነፍሱን ያገኛታል:ስለኔ ሰውነቱን በገራህተ መስቀል ይጣል"ያለውን አስቦ በጾም በጸሎት በትርህምት በስግደት ኖረ:ከዛም እንደ 12 ሃዋርያት አጋንንትን እያወጣ:ድውያንን ይፈውስ ለምጻምን ያነጻ ጀመር:ከዛም የአባታችን ተአምር በምድረ ኢትዮጵያ ተሰማ ህዝቡም እሱን ያይ ዘንድ ካለበት ይመጣል:ከዛም አባታችን ኢትዮጵያን እየተዘዋወረ ያስተምር ይጸልይ ጀመር በሁአላም በ33 አመቱ ወደ ደብረ ድባ መቶ ሚያዚያ 9 ቀን ምንኩስናን ተቀበለ በዚያች ቀንም አስኬማን,ቅናትን,ቀሚስን,መታጠቂያን,መስቀልን,በትርን ጭራንና ስእልን ተቀብሎ ሲጸልይ ዋለ:ከዛም እንዳስለመደው በየ ሃገሩ እየተዘዋወረ እያስተማረና ድውይን እየፈወሰ ሃገሪቱአን አቀና በየግዜውም የሚነሱ ንጉሶች ይመጡና ከአባታችን ዘንድ ይባረኩ ነበር:ብዙ ልጆችም አፍርቶ ነበር በስተመጨረሻም ጌታችን ከእናቱ እና ከብዙ ቅዱሳን ጋር ሆኖ ወደ አባታችን መቶ ብዙ ቃል ኪዳን ሰቱአቸዋል በስተመጨረሻም አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በ ሚያዚያ 9 ቀን አርፉ:: የአባታችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ረድኤት እና በረከት አይለየን አሜን!!!!! ምንጭ ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

Monday, April 12, 2010

ቅድስት እንባመሪና

የቅድስት እንባመሪና እናት ማርያም ትባላለች ገናም ህጻን እያለች ነበር በሞት የተለየቻት ከዛም አባቱአ ለአቅመ ሄዋን እስክትደርስ ድረስ በጎ ትምህርቶችን ሲያስተምራት አሳደጋት በሁአላም ለአቅመ ሄዋን ስደርስ አጋብቱአት እሱ ወደ መነኮሳት መኖሪያ ሄዶ ሊኖር እንደወደደ ሲነግራት እጂግ አልቅሳ "አባቴ ያንተን ነፍስ አድነህ የኔን ነፍስ ማጥፋት እንደት ይሆንልሃል ?" አለችውና አባቱአም እኔ የምሄደው ወደ ወንድ መነኮሳት ነው አንቺን ደግሞ ሴት ነሽ አያስገቡሽም ሲላት እንደወንድ ሱሪ አድርጌ ጸጉሬን ተቆርጬ ወንድ መስዬ ካንተ ጋር ሄዳለው አለችውና :ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሽጠው እና ለደሃ መጽውተው ተያይዘው ገዳም ይገባሉ:: በዚአም ገዳም እጅግ እየተጋደሉ ኖሩ በሁአላም አባቱአ በጸና ታመመና አበ ምኔቱን አስጠርቶ ልጄን አደራ በምንም መልኩ ከገዳም እንዳይወጣብኝ ይልና አበ ምኔቱን አደራ ይለውና ያርፋል: ቅድስት እንባመሪናም ተጋድሎዋን ከቀድሞ እጅግ አብዝታ ትተጋ ጀመር:ከረጅም ግዜ በሁአላም የገዳሙ መነኮሳት ይሄ መነኩሴ ከኛ ጋር ለምንድን ነው ከገዳም ውጪ ለተልኮ የማይወጣው እያሉ አበ ምኔቱን አስጨነቁት በሁአላም አበ ምኔቱ ከመነኮሳቱ ጋር አብሮ ይሰዳት ጀመር የሚሄዱትም የገዳሙን ምግብ በየግዜው ከሚሰበስብላቸው አንድ ሰውዬ ቤት ነበር:እንዳስለመዱት በየግዜው ሲሄዱ አንድ ቀን ምግቡን የሚሰጣቸው ሰውዬ አንዲት ልጅ አለችውና ጎረቤት የሆነ አንድ ጎረምሳ ተደብቆ ይገባና የሰውዬውን ልጅ ድንግልናዋን ያፈርሳል በሁአላም አባትሽ ማነው እንዲ ያደረገሽ ብሎ ከጠየቀሽ እንባመሪና ነው በይ ይላታል:በሁአላም ጊዜ ይሄድና ልጅቱአ ታረግዛለች በሁአላም አባትየው ከማን እንዳረገዘች ሲጠይቃት ከመነኩሴው ከእንባመሪና ነው አለችው:ከዛም ያ ሰውዬ ወደ ገዳሙ ይመጣና ባአደባባይ መነኮሳቱን ይረግማቸው ጀመር ከዛ አበ ምኔቱ መጣና ምን ሆነህ ነው ቢለው ልጄን ያንተ መነኩሴ ደፍረብኝ ሲለው ታድያ ባንድ ሰው ጥፋት እነዚን ሁሉ ቅዱሳን ለምን በአደባባይ ትረግማለህ አለውና እንባመሪናን አስጠራት:መጣችና አቤት አባቴ ስትል ሁሉም ይሰድቡአት ጀመር ለምን እንደሚሰድቡአት ባታቅም ሴጣን የሰራባት ነገር እንዳለ ገብቱአት ዝም አለች በሁአላም ነገሩን ነገሩአት እና አበ ምኔቱ "እንባመሪና ይህ የመነኩሴ አይደለም የአለማውያን ባህሪ አይደለም የሴጣን እንጂ ይህን ለምን አደረክ?"ብሎ ቢጠይቃት እሱአም አባቴ ይቅር በለኝ ወጣትነት አታሎኝ ነው አባቴ ይቅር በለኝ ብላ አበ ምኔቱ እግር ስር ወደቀች በሁአላም አበ ምኔቱ ከገዳሙ አባረራት እና ከገዳሙ ውጪ ሆና ትጋደል ጀመር ያቺም ልጅ ስትወልድ አባቱአ ልጁን አምጥቶ ለእንባመሪና ሰጣት እንባመሪናም ለልጁ የሚሆን ወተት እና ምግብ በአካባቢው ያሉትን እረኞች እየለመነች አሳደገችው:ከ3 አመት በሁአላም መነኮሳቱ አበ ምኔቱን ለመኑት ባይሆን ከባድ ቀኖና ይሰጠውና ወደ ገዳም ይግባ አሉት:አበ ምኔቱም ልመናቸውን ተቀብሎ ከባድ ቀኖና ሰጣት እና ስጨርስ ወደ ገዳሙ ተቀላቀለች ከዛም ገዳሙ ውስጥ ያሉትን ከባድ ስራዎች ያሰራት ጀመር ከዛም በሁአላ ገዳም ውስጥ ጭንቅ የሆኑ ስራዎችን ያሰሩአት ጀመር የመነኮሳቱን ቤት ጠርጋ ተሸክማ ወስዳ ከገዳም ውጪ አውጥታ ትጥላለች:ያም የተወለደ ልጅ አድጎ እዛው መነኮሰ 40 አመትም ከተፈጸመ በሁአላ ቅድስት እንባመሪና 3ቀን ታማ አረፈች:ከዛም የገዳሙ መነኮሳት ተሰብስበው ደውል ደውለው ተሰበሰቡ ሊገንዙአትም ፈልገው ልብሱአን ሲያዎልቁት ሴት ሆና ሲያገኙአት እጅግ አዝነው አበ ምኔቱን አስጠሩት:አበ ምኔቱም የተፈጠረውን አይቶ እጅግ አዝኖ አለቀሰ ያለበደሉአ የሰጣትን ቅኖና እና የተናገራትን ተግሳጽ እያሰበ አምሪሮ ያለቅስ ጀመር:ከዛም ያን የልጅቱአ አባት አስጠርቶ የሆነውን ሁሉ ነገረው ከዛም በድኑአን ተሸክመው አበቱ ይቅር በለኝ እያሉ ዋሉ ማምሻውን ላይ የቅድስት እንባመሪና አስክሬን "እግዚአብሄር ይቅር ይበላቹ" ሲላቸው አውርደዋት በታላቅ ክብር ከስጋዋም ተባርከው ቀበሩአት ከመቃብሩአም እጅግ ብዙ የሆነ ድንቆች ተአምራት ተደረጉ ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚች ጻድቅ ጸሎት ይማረን:የቅድስት እንባመሪና በረከት አይለየን አሜን.......ቸር ያቆየን!!!!!ምንጭ መጽሃፈ ስንክሳር ነሃሴ 15

Saturday, April 10, 2010

ቅድስት ማርያም ግብጻዊት

የኢየሩሳሌም ሊቀፓፓስ ሳፍሮኒዮስ እንደጻፈው:- ቅድስት ማርያም ግብጻዊት የተወለደችው በግብጽ ሲሆን ገና የ12 አመት ልጅ እያለች ነበር ወደ እስክንድርያ በመሄድ ድንግልናዋን ያፈረሰችው:ከዚያም የዝሙት ፍቅር አድርባት:ለ17 አመት ያህል ሰዎችን በሚያቃጥል የሃጥያት እሳት ታስፈጃቸው ነበር ዝሙት እያሰራች:ብዙዎችንም ታስት ነበር:ዝሙት ከመውደድ የተነሳ ገንዝብ እንኩአን ልስጥሽ ሲሉ አትቀበልም ነበር:በእግዚአብሄርም አታምንም ነበር በዛው ፋንታ እንደፈለገች ትሆን ነበር:በልቡአ ከዚ ሲራዬ ማንም አይከለክለኝም ትል ነበር::አንድ ቀን ሊቢያውያን እና ግብጻውያን ወደ ባህር እየተቻኮሉ ሲሄዱ አይታ ወዴት እንደሚሄዱ ብጠይቃቸው የከበረ የጌታችንን መስቀል በዓል ለማክበር ወደ እየሩሳሌም እንደሚሄዱ ሲነግሩአት እና የሚሄደው ሰው ብዙ መሆኑን ሲታይ: ብዙ ዘመዶችን አገኛለው ብላ ከነሱ ጋር ለመሄድ ተነሳች:ለጉዞዋ ወይም ለምግብ የሚሆን አንድም ገንዘብ አልያዘችም ነበር:በሁአላም በሰውነቱአ ማማር ብዙዎችን በዝሙት ምክንያት አጠመደች ወደ ተቀደሰ ቦታ የሚሄዱቱን ሰዎች በማሳት ዋና የሰይጣን መረብ ሆና ነበር:በዚህም ስራዋ እየተኩራራች ለሰው ሁሉ ትናገር ነበር:የሃጥያተኛን ሞት የማይወድ እግዚአብሄር መመለሱአን እየጠበቀ ይታገሳት ነበር:በመጨረሻም እየሩሳሌም ደርሰው ከበዓሉ በፊት እንደለመደችው እንደውም በከፋ መልኩ ዝሙትን አብዝታ ትሰራ እና ሰውንም ታስት ነበር:የበዓሉ ዕለት ጠዋት ብዙ ተሳላሚዎች ጌታችን መቃብር ላይ ወደ ተሰራችው ቤተ-ክርስቲያን ሊሳለሙ ሲሄዱ አየችና እዛ ሄደው ምን እንደሚያደርጉ ለማወቅ ፊላጎት አደረባት እናም ህዝቡ በሚገቡበት በር እየተጋፋች ለመግባት ትሞክር ጀመር በሁአላም በሩ ጋር ስትደርስ የሆነ ሃይል ሲገፋት ይታወቃት ጀመር ለሎቹን ሰዎች ስታይ በቀላሉ ይገባሉ እና መጀመሪያ ላይ ምንድን ነው እያለች ትስቅ ነበር ደጋግማ ስትሞክር አልቻለችም በሁአላም ዝም ብላ በሩ ላይ ቆመች እንደገናም ደጋግማ ሞከረች በሁአላም ሲደክማት ግዜ እልፍ ብላ ከበሩ አጠገብ ቆመች በህሊናዋም በብዙ መከራ ምን እንደሆነ ታስብ ጀመር: ቅዱስ መስቀሉን ለማየት እሱአ ያልቻለችበትን ምክኒያት ታስብ ጀመር:የድህነት ቃል የልቦናዋን አይኖች ነካቸው እና እንዳልገባ የከለከለኝ የራሱአ የግል ሃጥያት መሆኑን ተረዳች:በሁአላም በማልቀስ እና ደረቱአን እየደቃች ከውስጣዊ ልቡአ ማዘን ጀመረች:"ለምን አልገባም? እንዳልገባ የከለከለኝ የኃጢአቴ ብዛት ነው?" እያለች ደጋግማ እራሱአን ትጠይቅ ጀመር:ያን ግዜ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማሪያምን ስዕል ከበሩ ላይ አየችና ሄዳ ስዕሉአ ፊት ቆማ የስዕሉአን ግርማና ውበት ባየች ግዜ ያለፈ የራሱአ ሃጥያት ወለል ብሎ ታያት እና አፈረች በሁአላም በብዙ ለቅሶ ስዕሉአ ስር ወድቃ "ከንግዲ በሁአላ ጌታየን አገለግል እና ያንቺ ባርያ እሆን ዘንድ እድል አገኝ ይሆን ?" እያለች ታለቅስ እና ትለምን ጀመር:ጌታችንንም ካለችበት ስቃይና መከራ እንዲያድናት እና በመንገዱ እንዲመራት ለመነችው:"ቅዱስ መስቀሉን ካየው በሁአላ አለም እና ደስታዋን እንደምክድ ቃል ገባለው" ብላ ቃል ገባች:ከጸለየችም በሁአላ የመተማመን ስሜት ተሰማትና ወደ መስቀሉ ቦታ ወደሚያስገባው ቦታ ሄደች ከዚያም ያለችግር ገባች በሁአላም መስቀሉ ጋር ደርሳ በመንቀጥቅጥ እና በብዙ እምባ ሳመች የእግዚአብሄርን ሚስጥር እና ንስሃን እንዴት እንደሚቀበል አየች:ከዚያም ወታ ቃል ወደ ገባችበት ወደ እመቤታችን ስዕል ጋር ሄዳ "የሃጥአንን ንሰሃ ባንቺ አማላጅነት የሚቀበል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን:የከበርሽ እመቤቴ ሆይ ኃጥእት እኔ ምን እላለው?"አለችና "አሁን የገባውትን ቃል እፈጽም ዘንድ ግዜው ነው እጄን ይዘሽ ወደ ንስሃ ምሪኝ" አለች:ያን ግዜ የእመቤታችን ስእል አፍ አውጥታ "ዮርዳኖስን ብትሻገሪ እረፍት ታገኛለሽ" አለቻት:ከዛም እመቤቴ ሆይ አትተዪኝ ብላ አለቀሰች እና ከዚያ ተነስታ ወደ በረሃው ጉዞ ጀመረች ከመንገዶኞቹም አንዱ እህቴ ሆይ እንኪ ብሎ 3 ሳንቲም ሰጣት እና በነሱ ለመንገዱአ የሚሆን ዳቦ ገዝታ እያለቀሰች ከከተማው ወጣች:መንገድ ላይም መሸባትና የዮሃነስ መጥምቅ ቤት-ክርስቲያን አግኝታ እዛው ስታለቅስ አደረች:ጠዋትም አስቀድሳ እመቤታችንንም አንቺ ተከተይኝ እያለች ጉዞዋን ጀመረች ጀልባም ፈልጋ ዮርዳኖስን ተሻገረች ከዚአም ወደ አንድ በረሃ ደረሰች:በዚአም እህልም ሰውም ሳታገኝ ለ47 አመታት እየተጋደለች ወደሱ የሚመለሱትን ከሚቀበል ፈጣሪ ጋር ኖረች: ከ47 አመትም በሁአላ ቅዱስ ዞሲማሲን አግኝታ ሲላሳለፈችው እና ስለነበራት ህይወት አጫወተችው:ከዛም ለመጀመሪያው 17 አመታት የነበረባትን ፈተና እንዲ አለችው ""አባት ዞሲማስ ሆይ 17 አመት በዚ በረሃ ከአራዊት ከክፉ ምኞት እና ከክፉ ህሊና ጋር ስታገል ኖርኩ:ያለፈ ህይወቴንና ያሳለፍኩትን ደስታ እያሰብኩ እፈተን ነበር:ከረሃብ እና ከውሃ ጥም እንዲሁም ከጸሃይ ሃሩር የተነሳ በጣም ተሰቃይቻለው: ብዙ ግዜ እታመምና ለሞት እደርስ ነበር:ጌታዬም እንዲረዳኝ እለምነው ነበር ህሊናየን መጀመሪያ ወደ ተቀበለችኝ እመቤቴም ስዕል እሄድና እማጸናት ነበር ከዛም በሁአላ በ4ቱ ማእዘን የሚያበራ ብርሃን አይ ነበር""እያለችና ሌላም ሌላም ትነግረው ነበር:ከዛም ቅድስት ማሪያም ግብጻዊት በብዙ ተጋድሎ ሰይጣንን ድል ነስታ ቅዱስ ዞሲማሲን በሚቀጥለው አመት ወደዚ በረሃ ስትመጣ የጌታችንን ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን በእለተ "ፀሎተ-ሃሙስ" ይዘህልኝ በዮርዳኖስ ባህር ዳር እንገናኝ አለችው ና ተመልሳ ወደ በረሃው ገባች በአመቱን ቅዱስ ዞሲማስ ይዞላት መቶ የዮርዳኖስ ባህርን እየተራመደች ስትመጣ ግዜ አይቶ እግዚአብሄርን እያመሰገነ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን አቀበላት ከዚያም እንደገና ቅዱስ ዞሲማስን አሰናበተችውና በሚቀጥለው አመት እንዲመጣ ነገረችው በሁአላም በአመቱ ሲመጣ አጣት እና እጂግ አለቀሰ በሁአላም ፈልጎ ሬሳዋን አገኘውና ሲሙአን ባለማወቁ ሲጸጸት ጊዜ አንድ ብጣቂ ወረቀት አገኘና አነበባት "" አባት ዞሲማስ ሆይ በጸሎተ ሃሙስ ማታ ከቅዱስ ሚስጥር ከተቀበልኩ በሁአላ ወደ አምላኬ ሄጃለው የደካማይቱን የማርያምን ስጋ በዚ ቦታ ቅበረው ዓፈር ወደ ዓፈር ይመለስ ዘንድ:ስለ እኔም ጸልይልኝ "" በሁአላም ሲሙአን በማወቁ ደስ እያለው እዛው ቀበራት እና ወደ በአቱ ተመለሰ:ቅድስት ማርያም ግብጻዊት ያረፈችው በሚያዚያ 6,522ዓ.ም. ነው:: የዚች ጻድቅ ማርያም ግብጻዊት በረከት አይለየን አሜን.......ቸር ያቆየን!!!